ታማኝ ካድሬነት – የህወሓት ኣባላት ከህዝባቸውና ሃገራቸው ይልቅ ለድርጅታቸው ያላቸው ታማኝነት ይበልጥባቸዋል – አንዶም ገብረስላሴ

ህወሓትና ምርጫ ቦር

ድ የኣንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች መሆናቸው ይታወቃል። ከዚህ ጋር የተያያዘ በሑመራ ያጋጠመን ኣንድ ታማኝ የህወሓት ካድሬና የምርጫ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ትንሽ ላካፍላቹ።

በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ራውያን ቀበሌ ፅህፈት ቤት ከፍተን ታፔላና ባንዴራ ስንተክል ተገኝተን ” ከ5 በላይ ሰዎች ሁናቹ ተሰብስባቹ ስለተገኛቹ መታሰር ኣለባቹ”

 

 

 

 

 

 

 

ብለው ለ23 ሰዓታት ኣስረው ሲለቁን ጉዳዩ ለወረዳው ሃላፊዎች ለማስረዳት ወደ ወረዳው መስተዳድር ፅህፈት ቤት ስንሄድ ከታች በምስሉ የምትመለከቱት ኣቶ ጌታቸው በየነ የሚባለው ሰውየ ኣስተናገደን።

ሰውየው የህወሓት ከፍተኛ ካድሬ ተብሎ የሰለጠነና የወረዳው ፅህፈት ቤት ሃላፊ ሆኖ የተሾመ ነው።

ታድያ ይሄ ኣቶ ጌታቸው በየነ በምርጫ 2002ና በ2007 ዓ/ም የሑመራ ምርጫ ክልል ሃላፊ ሆኖ ያገለገለና ኣሁንም እየሰራ ያለው ታማኝ ካድሬ ነው። የምርጫው ውጤት 100% የሚያደርጉትም እነዚህ ታማኞች ናቸው።

ሰውየው ብንለው ብንለው ጉዳያችን በቀላሉ ሊረዳን ኣልቻለም ኣልያም ኣልፈለገም። እንደምንም ብሎ ለዞኖ ምርጫ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ስለህጉ ጠይቆ ማብራርያ ከተሰጠውና የህግ ክፍተት እንደሌለን ሲያውቅም ኣንገራግሮ ስህተቱ እንደሚያርሙ ገልፆልን ተለያየን።

እነዚ ታማኝ ካድሬዎች ለህዝቡና ለፓርቲዎች በገለልተኝነት ፍትሓዊ ኣገልግሎት ሊሰጡ ኣይፈልጉም ወይም ኣይችሉም።

ሰለማዊ ትግልና ምርጫ የሚባለው ከገዢው ፓርቲ፣ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ ታዛቢዎች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ሚድያው በህወሓት ታማኝ ካድሬዎች የሚመሩ ኣድርጎ የይስሙላ መወዳደር ኣይደለም።

ኣቶ ጌታቸውና መሰሎቻቸው የህወሓት ታማኝ ካድሬዎች የሚመሩት ምርጫ ቦርድ “የሁለት ምክቶች ምክር ኣንታረድ ነው” እንደሚባለው ኣስቀድሞ የሚታወቅ ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ በሰለማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር ማምጣት የሚፈልግ ከሆነ እነዚህ ተቋማት ከኢህኣዴግ እጅ ፈልቅቆ ሊያወጣቸውና በገለልተኛ ሰዎች እንዲመሩ ማድረግ ይጠበቅበታል።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s