ሃብታሙ አያሌውና መምህር አብርሃም ሰለሞን ከ600 ቀናት እስራት በኋላ ተፈቱ | እነ አብረሃ ደስታ አልተለቀቁም

ዘ-ሐበሻ) የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የነበረው ወጣቱ ፖለቲከኛ አቶ ሃብታሙ አያሌው ከ እስር መለቀቁ ተሰማ:: ከ እርሱ ጋር አብሮ የታሰረው መምህር አብርሃም ሰለሞንም መፈታቱም ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመልክቷል::

የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች እንዳሉት ፍርድ ቤት ለ2ኛ ጊዜ ባለፈው አርብ እንዲለቀቁ ት ዕዛዝ ቢያስተላልፍም የማረሚያ ቤት ፖሊስ ለመልቀቅ ሲያንገራግር ቆይቶ እስከዛሬ ድረስ በ እስር አቆይቷቸዋል::

ከሃብታሙ አያሌው እና ከአብርሃም ሰለሞን ጋር በነፃ እንዲለቀቁ የተወሰነላቸው የአረናው ፓርቲ አመራር አብርሃ ደስታ; ዳን ኤል ሺበሺና የሽዋስ አሰፋ አልተፈቱም:: እንደ ምንጮቻችን ዘገባ በችሎት መድፈር የተነሳ ከአንድ ዓመት ከሁለት ወር እስከ አንድ ዓመት ከስድስት ወር  የተፈረደባቸው እነ አብርሃ ደስታ ምናልባትም እስከመጪው ሰኔ ድረስ እስር ቤት ሊቆዩ ይችላሉ ተብሏል::

ሃብታሙ አያሌውና መምህር አብርሃም ሰለሞን ዛሬ ከእስር ቤት ከተፈቱ በኋላ የተነሷቸውን ፎቶዎች ይመልከቱ::

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s