በመንፈሳዊነት የከሰረች አገር! – አቻምየለህ ታምሩ

አይናችን ጉድ እያየ ነው። ባህሩ ዘውዴ «ኢትዮጵያ የታምር አገር ናት» ያላት አገር ዛሬ የጉድ አገር ሆናለታለች። በዚች የጉድ አገር ውስጥ የተፈጠርን ሰዎች እግዚያብሔር በጎችን እንዲጠብቁ ያሰማራቸው «የኃይማኖት አባቶች» እረኞቹን አሳልፈው ለገዳዮች በመስጠት ነፍሰ ገዳዮች በምዕመኑ ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስዱ ሲማጸኑ አይናችን እያየ ነው። ከዚህ የጉድ ዘመን በፊት ግን ኢትዮጵያ ብዙ ጀግና መነኮሳት፣ ካህናትንና ቄሶችን አፍርታ ነበር።

ያሁሉ አልፎ እውነተኞቹ የኃይማኖት አባቶችና እረኞች ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቄስ ጉዲና ቱምሳ በተቀመጡበት ወንበር ላይ ዛሬ አስገዳዮቹ ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስና ቄስ ዋቅ ስዩም ኢዶሳ ተተኩበት።

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዘመናቸው የነበረው ወታደራዊ መንግስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን አሳልፈው እንዲሰጡ በርካታ ውትወታና ጫና ቢያደረግባቸውም ለምንም አይነት ጫና ሳይንበረከኩ የተሰጣቸውን የቤተ ክርስትያን አደራ ተወጥተው አልፈዋል። በመጨረሻም በኃይል ቤተ ክርስትያኗን በፖለቲካው ስር ለማድረግ ደርግ እርምጃ ሲጀምር የርሃብ አድማ በማድረግ፤ ገፍቶ ሲመጣም «ሬሳዬን ተራምዳችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን ትደፍራላችሁ» በማለት ጸንተው ስጋቸውን በርሀብ አመንምነውና 25 ኪሎ መዝነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ጀግና ነበሩ።

ቄስ ጉዲና ቱምሳም በደርግ ዘመነ-መንግስት የመካነ-ኢየሱስ ቤተክርስቲያን መሪ በመሆን ሲያስተዳድሩ ደርግ ለሶስት ጊዜያት በተደጋጋሚ ለእስር ዳርጓቸው ከሶስተኛው እስር በኋላ ግን ዱካቸው ሳይገኝ ለ13 ዓመታት ቆይቷል። ቄስ ጉዲና በደርግ በተደጋጋሚ የታሰሩትም ሆነ መጨረሻ ላይ መስዕዋትነትን የተቀበሉት ስለተጨቆኑ ሰዎች ሁሉ ይጨነቁ ስለነበር ነው።

የዛሬዎቹ ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስና ቄስ ዋቅ ስዩም ኢዶሳ ግን ምዕመናኑን ጸረ ሰላም ብለው በመሰየም ወያኔ የማያዳግም እርምጃ ይወሰድባቸው ብለው ጠየቁ። በመንፈሳዊነት የከሰረች አገር!

posted by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s