እሁድ እረፋድ | ታሪኩ ደሳለኝ

አባት ከ 7 አመት ልጁና ከ3 አመት ሴት ልጁ ጋር ግቢ ውስጥ እየተጫወተ ነው በዚህ መሀል የግቢው በር ይንኳኳል ሴት ልጁን አቅፎ ወደ በሩ ሲያመራ ወንድ ልጁ ሱሪውን ይዞ ተከተለው። በሩን ሲከፍት መሳሪያ የደቀኑ ወታደሮች ከቀበሌው ሊቀመንበር ጋር ቆመው አገኛቸው። አባት ሴት ልጁን ጠበቀ አድርጎ እያቀፈ ወንዱን ልጅ ወደ ኃላ ሸሸት አደረገው። አንደኛው ወታደር ያያዘውን ወረቀት ሰጠው በስጋት ተቀብሎ ተመለከተው “ሀገር የመክዳት ወንጀል የፈፀመ” ይላል ። ወታደሩ በመሳሪያው ጫፎ ወደ ቆመው ፓትሮል መኪና እንዲሄድ መልክት አሳየው ልጆቹን በሩ ላይ ጥሎ ወደ መኪናው ገባ ። መኪናው ሞተሩን አስጩሆ ሲሄድ ጎልቶ የሚሰማው የሞተሩ ድምፅ ሳይሆን የልጆቹ የለቅሶ ድምፅ ነው።

ይህ ክስተት የተፈፀመው ከ 5 ወራት በፊት በጎንደር ከተማ ነበር።

ሐሙስ ከሰዓት

በአካባቢው ሰው የተወደደ ጉልማሳ ነው። የራሱን ሚኒባስ መኪና ነው የሚያሽከረክረው።የተጣላን አስታራቄ ለተቸገረ ቀድሞ ደራሽ ። በሱ ሚኒባስ የተሳፈሩ እናቶችና አባቶች አቅመ ደካሞች አይከፍሉም ማለት የቻላል። ሀሙስ ከሰአት ገቢያተኞችን ጭኖ እንደወትሮው እየሳቀና እየተጫወተ ሲሄድ የትራፊክ ፖሊስ እንዲቆም ምልከት አሳየው። መኪናው ዳራ እያሲያዞ እያቆመ በውስጥ መስታወት ትርፍ ሰው አለመጫኑን ከረጋገጠ በኃላ ከነፍገግታው ከመኪናው ወረዳ። በአካባቢው ቁጥቋጦ ውስጥ ተሸሽገው የነበሩት ወታደሮች ጠመንጃቸውን እንደ ወደሩ ከበቡት። ግራ ተጋባ ሽፎቶቸ ናቸው እንዳይል ትራፊክ ፖሊሱን ለ3 አመታታት ያህል ያቀዋል። አንደኛው ወታደር የያዘውን ወረቀት ሰጠው ተቀብሎ ተመለከተው “ሀገር የመክዳት ወንጀል የፈፀመ” ይላል። እጁን እረጋ ብሎ ሰጣቸው። ከፊት አስቀድመውት ሲሄዱ ሚኒባስ ውስጥ ያሉት ተሳፋሪዎች የሚደረገውን ነገር በቁጣ እየተመለከቱ ነበር።
ይህ ድርጊት የተፈፀመው ከአንቦ ወደቶኪ በሚወስደው መንግድ ላይ ከ 2 ወራት በፊት ነው።

ለማሳያ ያህል ከላይ ስለገለፅኳቸው ሰዎች ጉዳይ መንግስት ሲናገር “አሰልጥኜ፣ ቃል ኪዳን አስገብቼ መሳሪያ ያስታጠኳቸው ወታደሮች ነበሩ ሆኖም ለሀገር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰው መሳሪያቸውን ጥለው ማንነታቸውን ለውጠው ግዲታቸውን ሳይፈፅሙ የከዱ ወታደሮች ናቸው” ይላል። የከዱ የተባሉት ወታደሮች ደግሞ ይህን ያላሉ “ለሀገራችን የደምም የአጥንትም መሳዋትነት ከፍለናል፣ የበረሃው ሀሩር ሳይበግራን የወይን አደጋው በርድ ሳያሸንፈን በዱር በግድሉ በየ ግንባሩ ተፋልመናል። ሆኖም በሚገባን ጊዜ ማረግ ልናገኝ ይቀርና ባለ ማአረግ ይጎትተናል፣ የውል አበላችንም ሆነ ደሞዛችን በወራት ነው ይምናገኘው፣ የሠላም ማስከበር ስራ ለመስራት ወደ ሌሎች ሀገራት ለመሄድ በሁሉም መስፈርት ብቁ ብንሆንም ከመሀላችን ተመርጠው ነው ሌሎች የሚሄዱት በዚህ ላይ የሀገር ወታደር እንደሆንን እንዲሰማን አያደርጉንም። ታዲያ ማነው የተከዳው?” ይላሉ።

የሆነው ሆኖ መንግስት ከ2005ዓ.ም ጀምሮ የ1990 ዓ.ም ዘማቾችን፣ የ1994ዓ.ም ዘማችን እና ከዛ በኃላ ውትድርናን ተቀላቅለው ከድተውኛል የሚላቸውን እያፈሰ በፌደራሉ የሸዋ ሮቢት እስርቤት ማጉር ከጀመራ ሦስት አመት ሆኖታል።
ይበልጥም ህዝባዊ እንቢተኝነት በኦሮሚያና በጎንደር መታየት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አሰሳውና አፈሳው ተጠናክሮል።

እንዚህ መንግስት ከድቷናል የሚሉ ወገኖች መሳሪያ መተኮሱንና ማስተኮስ የሚችሉ፣ ጥቃትን እንዴት ይፈፀማል ጥቃትንስ እንዴት መመከት ይቻላል የሚሉትን ነገሮች ጠንቅቀው የሚያውቁ በዚህ ላይ ከመሀበረሰቡ ጋር ተግባብተው የሚኖሩ መሆናቸው በአሁን ሰዐት የመንግስት ትልቁ እራስ ምታት እንዲሆኑ አስችሎቸዋል። ለዚህ ነው መንግስት አይኑንም እጁንም እነሱ ላይ ያደረገው። በብዛት በመሀበረሰቡ ውስጥ የሚገኙት ተክደናል የሚሉት ወገኖች ህዝባዊ እንቢተኝነትን ከተቀላቀሉ ምን ይከሰት ይሆን?
(በሸዋ ሮቢት የፌደራሉ እስር ቤት ከሚገኙ ተማኝ እስረኞች ከሚባሉት ጋር የተደረገ ወግ)

posted by tigi flate

 

 

 

 

 

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s