የወያኔ ቡድን መሪዎ

ች ለስልጣናቸው ናቸው ብለው የሚጠረጥሯቸውን በሙሉ መግደል ማሰርና ማግለል የዘወትር ተግባራቸው ሲሆን በራሳቸው የጦር ኃይል ውስጥም ጦሩን ያሳምጻሉ ተብለው የጠረጠሩትን ሁሉ ከስብሰባና ከግምገማ አዳራሽ እየወሰዱ መዳረሻቸውን እየጠፉ መሆኑን ከወያኔ መከላከያ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመለከታል። በዚህ መሠረት በወያኔ ሰሜን ዕዝ ውስጥ የከፍተኛ መኮንኖች ግምገማ ላይ ያነሱት ሃሳብ አመጽ ቀስቃሽ ነው፤ አፍራሽ ነው ብሄራቸው ተጠርጣሪ ነው በሚል ሶስት ሌ/ሎኔል ሁለት የ3ሻለቃ ማዕረግ ያላቸው መኮንኖች በወያኔ ወታደራዊ ደህንነት ተይዘው ከተወሰዱ በኋላ መድረሻቿው መጥፋቱ ታውቋል። ይህ በሰሜን ዕዝ የተፈጸመው ሁኔታ መረጃዎችና ወታደራዊ አዛዦችችን የበለጠ ስጋት ላይ ጥላችቸው። ተይዘው መዳረሻችው የጠፋ መኮንኖች ማንነትና ብሔራቸው ለጊዜው ያልታወቀ ሲሆን በርካታ የጦር አባላት ግን ሁኔታውን በቅርብ አየተከታተሉት መሆኑ ተገልጿል።

የወያኔው ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ኃይለለማሪያም ደሳለኝ ለወያኔው ፓርላማ ባደረገው ንግግር የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞና ቁጣ ከመልካም አስተዳደር የመጣ ችግር ነው በማለት በማለት ጥፋቱን አምኖ በእንቅስቃሴው የተገደሉትን ወገኖች ይቅርታን ይጠይቅ እንጅ ተቃውሞው ጸረ ሰላም ኃይሎች ያዘጋጁት ነው በማለት የተናገረ ከመሆኑም በላይ ለሞቱ ወገኖች ካሳ ለመክፈል እንዲሁም ገዳዮችን ፍርድ ቤት ለማቅረብ መዘጋጀቱን የሚገልጽ ቃል አለመተንፈሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው የፓርላማ ንግግር ከተራ ፕሮፓጋንዳ ያለፉ አልሆነም ተብሏል። ተቃውሞ አሰምታችኋል፤ ቁጭታችሁን አደባባይ ገልጻችኋል ተብለው በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች በእስር እየማቀቁማና እየተሰቃዩ ስለ እነርሱ አንዳች ነገር ሳይተነፍስ የመልካም አስተዳደር ጉድለትና ስራ አጥነት የፈጠረው ተቃውሞ ነው ማለት ብቻ ምንም ማለት እንድልሆነ የፖለቲካ ታዛቢዎች ይናገራሉ። ወያኔ የችግሩ እናት መሆኑን ካመነ ችግሩን ተከትሎ ለመጡት ችግሮች ሙሉ ኃላፊነት መወሰድና ማስታካከል ይገባዋል በማለት አስተያየታቸውን አክለው ይገልጻሉ።

· የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያዋን ሙስሊሞች ላይ ያወጀውን ጦርነት በመቃወም በኢትዮጵያ ላይ ያለውን ጭቆዎና እንዲያበቃ የድምጻችን ይሰማ በማለት በመረጡት ጊዜና ቦታ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ የቆዩት የሙስሊሙ ህብረተሰብ አርብ መጋቢት 2 ቀን 2008 ዓም በአዲስ አበባ በቢር ኑር መስጊድ ታላቅ ተቃውሞ ማድረጋቸው ታውቋል። የወያኔ ፖሊሶችንና የደህንነት ኃይሎችን በማዘናጋት የተደረገው ተቃውሞ የወያኔ ፖሊሶችን ያስደነገጠ እንድነበር ታውቋል። በዕለቱ ሕዝበ ሙስሊሙ ከያዛቸው መፈክሮች ውስጥ የተቀበረች ፍትህ ቀባሪዋን ትቀብራለች የታሰሩት ይፈቱ ብሔራዊ ጭቆና ያብቃ መብታችን ይከበራል የሚል ይገኙበታል። ሕዝበ ሙስሊሙ የተቃውሞ ድምጹን በስለማዊ መንገድ እንዳያሰማ የወያኔ ደህንነትና የፖሊስ ኃይሎች አባላት ጥበቃ ያድርጉ እንደነረ ታውቋል። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከሳምንታታት በፊት በታላቁ አንዋር መስጊድ ባለፈው ሳምንት በቢኒ መስጊድ ሰላማዊ የሆነ ተቃዋሞ ማድረጋቸው ይታወሳል። \

· ከሁለት መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ሲገደሉ በሺህ የሚቆጠሩ ሲታስሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲደበደቡ ድምጻቸውን ያላሰሙ የሃይማኖት እንዲሁም ገዳዮችን አሳሪዎችንንና ደብዳበዎችን ሳያወግዙ የቆዩ የሃይማኖት አባት ተብዮዎች በሻሽመኔ ከተማ ባካሄዱት ስብሰባ በሕዝብ ተቃውሞና ቁጣ ለጠፋው ንብረትና ለተቃጠለው ሀብት በእጅጉ አዝነናል ማለታቸው ትዝብት ላይ የጣላቸው ሲሆን የዘረኛውና የአምባገነኑ አገዛዙ ሌላ መሳሪያ መሆናቸውን በግልጽ ለሕህዝብ አስይተል። በስብሰባው ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶድክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት ሃይማኖት መሪዎች የተገኙ ሲሆን በወያኔ አገዛዝ የሚጨቆነው ሕዝብ ከተቃውሞና ከቁጣ ተቆጥቦ በልማት ስራ ላይ እንዲትተጋ ትምህርት ለምስጠት ቃል ገብቷል። የሃይማኖት መሪዎቹ ሕዝብን በግብረ ገብነት አንጸው ፈሪሃ እግዚእብሔር እንዲኖረው እንዲሁም ለመክራውና ለስቃዩም ድምጽ በመሆን ለተገፋትና ለተጨቆኑ አቤት ባይ መሆን ሲገባቸው ከገዳይና ከአሳሪ ጎን መቆማቸው የወያኔ ጉዳይ ፈጻሚ ካድሬ እንጅ የህዝብ እረኛና ጠባቂ አለመሆናቸውን በግልጽ አሳይተዋል ተብሏል።

· ከሁለት ዓመት በፊት ከኩዋላ ላምፑር ወደ ፔኪንግ ሲጓዝ በረራ ላይ እያለ መዳረሻው ጠፍቶ የቀረውና በበረራው ቁጥር MH370 እየተባለ የሚጠራው የማሊዢያ አውሮፕላን ስብርባሪ አካል ነው ተብሎ የሚጠረጠር የብረት ቁራጭ በሞዛምቢክ ወደብ የተገኘ መሆኑ ሲገለጽ በቅርቡ ለምርመራ ወደ አውስትራሊያ ይላካል ተብሏል። ይህንን አንድ ሜትር ርዝማኔ ያለውን የብረት ቁራጭ ያገኘው ባለፈው ታኅሳሥ ወር የእረፍት ጊዜውን በሞዛምቢክ የወደብ መናፈሻ ሲዝናና የነበረው የደቡብ አፍሪካ ወጣት ሲሆን ብረቱን ወደ ቤቱ ይዞ ከመጣ በኋላ ለባለስልጣኖች ያስረከበ መሆኑን ገልጿል። የደቡብ አፍሪካ የትራንስፖርት ጉዳይ ባለስልጣኖችም ዕቃውን መረከባቸውን ገልጸው እቃው ሰለጠፋው አውሮፕላን ጉዳይ ኃላፊነት ወደተሰጠው አገር ወደ አውስትራሊያ የሚላክ መሆኑን ገልጸዋል። በካምቤራ የሚገኘው የአውስትራሊያ የትራንስፖርት ሚኒስትርም ሁኔታውን አረጋግጦ ከማሌዢያና ከደቡብ አፍሪካ ባለስልጣኖች ጋር እየመከረ መሆኑን አሳውቋል። በበረራው ቁጥር MH370 የሚታወቀው የማሊዢያ አውሮፕላን 239 መንገደኞችን አሳፍሮ ከኩውላ ላምፑር ወደ ፔኪንግ ሲጓዝ በበረራ ላይ እንዳለ ተሰውሮ መጥፋቱ ይታወሳል። ከአየር ላይ ወርዶ ባህር ውስጥ ሰጥሟል የሚል ግምት ቢሰጥም እስካሁን ድረስ የወደቀበት ቦታም ሆነ የአውሮፕላኑ አብዛኛው ክፍል ያልተገኘ መሆኑ ተነግሯል። ባለፈው ሐምሌ ሪዩኒየን በምትባልና በህንድ ውቅያኖስ ላይ በምትገኝ ደሴት አንድ ለመዝናናት የመጣ የፈረንሳይ ዜጋ የአውሮፕላኑ ክንፍ አካል የሆነ ስብርባሪ ክፍያ ማግኘቱና በምርመራም የአውሮፕላኑ አካል ሆኖ መረጋገጡ አይዘነጋም።

· የአልጄሪያ የጸጥታ ኃይሎች ሐሙስ ዕለት ጉማር በምትባለው በአልጀርያና በቱኒዚያ ወሰን አቅራቢያ በምትገኘው ከተማ ባካሄዱት አሰሳ ሶስት አሸባሪዎችን ገድለው ሶስት ስቲንገር የተባለ የጸረ አውሮፕላን ሚሳየል መተኮሻ መሳሪያ ያገኙ መሆናቸውን ባለስልጣኖች ገልጸዋል። ከሶስቱ ስቲንገሮች ሌላ 20 የሚሆኑ የካላሽንኮፍ መሳሪያዎች ሌሎች ሶስት የሚሳየል መተኮሻዎችና እንዲሁም ቦምቦችና ጥይቶች ያገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል። አልጀሪያ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ እስላማውያን አክራሪዎችን ስትዋጋ የቆየች ስትሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህም አክራሪ አሸባሪዎች በቱኒዚያ የተለያዩ ጥቃት መፈጸማቸው ይታወቃል።

· በሊቢያ እንዲቋቋም የተፈለገው የህብረት መንግስት እውን እንዳይሆን እንቅፋት በሆኑት የሊቢያ ባለስልጣኖች ላይ ማዕቀብ ለማድረግ የአውሮፓው ህብረት አገሮች እየመከሩ መሆናቸው ተነገረ። የአብዛኛውን የአውሮፓ አገሮች ስምምነት አግኝቷል የሚባላው የማዕቀብ ሀሳብ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በተግባር ይውላል ተብሏል። ማዕቀቡ የሚጣልባቸው ባለስልጣኖች እነማን እንደሆኑ በይፋ ባይነገርም በትሪፖሊ በሚገኘው የመንግስት አካል ውስጥ የፓርላማው መሪ የሆኑት ኑሪ አቡ ሳህማና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በካሊፋ ጉዌል ሊሆኑ እንደሚችሉ አንድ ስማቸውን መግልጽ ያልፈለጉ የአውሮፓው ህብረት ባለስልጣን ጠቁመዋል። ለረዥም ጊዜ የሊቢያ መሪ ሆነው የቆዩት ጋዳፊ የዛሬ አምስት አመት በሕዝብ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከስልጣን ቢወገዱም በባዕድ ጣልቃ ገብነትና አክራሪ ኃይሎች ባደረጉት እንቅስቃሴ ምክንያት በአገሪቱ ሁለት ተጻራሪ የሆኑ ራሳቸውን መንግስት የሚሉ አካሎች መቋቋማቸው ይታወሳል።

· በሲየራ ሊዮን ውስጥ በነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ከፍተኛ ወንጀል በመፈጽሙ የአስራ አምስት አመት እስራት ተፈርዶበት የነበረውና የእስራት ዘመኑን ሳይጨርስ በምህረት ተለቆ የነበረው የሚሊሺያ መሪ እንድገና መታስሩ ተነገረ። ሞይኒና ፎፋና የተባለው በአገሪቱ የርስ በርስ ጦርነት በተካሄደበት ወቅት በርካታ ሰው በመግደሉና ብዙዎቹንም ከእነ ህይወታቸው እንዲቃጠሉ በማድረጉ በልዩ ፍርድ ቤት የአስራ አምስት ዓመት እስራት ተፈርዶበት ታስሮ የቆየ መሆኑ ይታወቃል። ሁለት ሶስተኛውን የእስራት ጊዜ በማገባደዱ በምህረት ተፈትቶ የነበረ ቢሆንም ሲፈታ ቃል የገባውን ግዴታ አላከበረም በሚል ምክንያት ትናንት አርብ መጋቢት 2 ቀን 2008 እንደገና በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል።

በተያያዘ ዜና በሲየራ ሊዮን ጽንስን ለማስወረድ የሚፈቅደው ረቂቅ ህግ የአገሪቱ ምክር ቤት ቢወስንም ፕሬዚዳንቱ ህጉን ፈረመው ለማጽደቅ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህንን እርምጃ የወሰዱት በሃይማኖት አባቶች ግፊት ሲሆን ህጉ ሊጸድቅ የሚችለው ሕዝቡ በውሳኔ ህዝብ ድምጽ ሰጥቶ ከደገፈው ብቻ ነው ብለዋል።

posted by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s