የኢትዮጵያ ወደብ አልባነት እያሰከተለ ያለው ጉዳትና ቀጣዩ አቅጣጫ

ከጊዜው ደረሰ ( gezew.derese@bell.net  

ጠቅላይ ሚኒስቴር መለሰ ዜናዊ በሀገራችን ህልውና ላይ ከፈጸሙት ስህተቶች ሁሉ ትልቁ የሀገራችንን ታሪካዊም ይሁን ህጋዊ መብት ወደጎን በመተው በግል ውሳኔያቸው ኤርትራን በተመለከተ በአቶ ኢሳያስ የሚመራው ቡድን የጠየቃቸውን ሁሉ ያለአንዳች ማመናታት መስጠታቸው ነበር። በአወሮፓውያን አቆጣጠር 1994 የፈጸሙትን ስህተት ደግሞ በ1998 ማረም የሚያሰችላቸው ሁኔታ ቢፈጠርም ይህንን እድል ሳይጠቀሙበት  ሆን ብለው ማለፋቸው ብቻ ሳይሆን እንዲያውም እድሉን እንጠቀምበት ያሉትን ሁሉ በተለያየ የሀሰት ክስ በመክሰስ ፣ ማሰራቸው፣ ከስራ ማባረራቸው፣ ማሰቃየታቸው ወዘተ በታላቅ ምሬትና ሀዘን የሚታወስ በሀገራችንም ታሪካ እንደ ትልቅ ጠባሳ የሚቆጠር የታሪክ አሻራ ነው። ይህ መሰረታዊ ስህተት በሀገራችን ላይ እያደረሰ የሚገኘው አደጋ እስከዛሬም በብዙ መልኩ ለእድገታችንም ሆነ ለመሰረታዊ ህልውናችን አደጋ ሆኖ ይገኛል። በዚህ ጽሁፍ ይህ ስህተት ባሁኑ ስአት ከሚታየው ርሀብና በህዝባችን ላይ ከደረሰው አደጋ እንዲሁም ከመሰረታዊ የልማት ጉዞ አኳያ ያስከተለውን ተጽእኖ በመጠኑ አሳያለሁ።ይህንንም በማድረግ ከእርስ በእርስ ፍራቻ ተላቀን ፣ ካፈርኩ አይመልሰኝ የሚል ስሜትን አስወግደን እያነዳንዳችን የፖለቲካ ልዩ ጠቀሜታ ሳይሆን ሀገርንና ህዝብን ለመታደግ ምን መደረግ እንዳለበት ለመነጋገር ተጨማሪ መንደርደሪያ ይሆናል ብየ አስባለሁ።

የጉዳቱ ስፋት ከኢኮኖሚና እድገት አኳያ ሲታይ

ኢትዮጵያ ከምተገኝበት እጅግ ወደ ሓላ የቀረ ሁኔታ ለመላቀቅ እጅግ ብዙ ገንዘብ ያሰፈልጋታል። ይህን ለማድረግ ደግሞ ወይ ገቢዋን እጅግ ማሳደግ ይኖርባታል ወይም ደግሞ ወጪዋን መቀነስ ይሆርባታት። ከገቢ ወጭ የሚተርፍ ገንዘብ ነው አንድን ሀገር ሀብት እንድታከማች ወይም አዳዲስ የልማት ስራወችን ለመሰራት አቅም እንዲኖራት ወይም ለክፉ ጊዜ የሚሆን መጠባበቂያ እንዲኖራት የሚያደርገው፡፡

በሀገራችን አሁን እየተካሄደ ነው እየተባለ የሚነገረን የልማት ስራ ባብዛኛው የሚካሄደው ወይ በእርዳታ ወይም በብድር በሚገኝ ገንዘብ ነው ። ይህ  የራሱ ችግር አለው። ብድር ጊዜውን ጠብቆ ከነወለዱ መከፈል ይኖርበታል።ይህ ሲሆን ደግሞ ያለ የሌለን ሀብት አሟጦ ለአበዳሪው ነው የሚያስረክበው። ባብዛኛው የሶስተኛው አለም ሀገሮች፣ የተበደሩት ገንዘብና ወለዱ ለመክፈል ከሚችሉት አቅም በላይ እየሆነ ከማይወጡበት ማጥ ውስጥ እንደሚወድቁ የሚታወቅ ነው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም የዚሁ ሁኔታ ሰለባ ነበረች፡፡ ኢትዮጵያ የብድሯ መጠን ለመክፈል ከምትችለው በላይ እንደሆነ ታውቆ ከአመታት በፊት የብድር ምህረት (ብድር ስረዛ) ተደርጎላት ነበር። አሁን ደግሞ  ኢትዮጵያ የምትበደረው ገንዘብ ከአመት አመት በፈጣን ሁኔታ እያደገ ነው፡ በዚህ ከቀጠለም ለመጭው ትውልድ የምታስተላልፈው እዳ እንጂ ሀብትን አይሆንም።

የሀገራችንን ያለ የሌለ ሀብት  በከፍተኛ ደረጃ በማራቆት ላይ የሚገኘው አንዱ ወደውጭ  ለሚላከውና ወደሀገር ለሚገባው ሸቀጥና ምርት የምትከፍለው የወደብ ኪራይና ቀረጥ ወጭ ነው። ይህ ወጭ ከአመት አመት እየጨመረና ከአቅም በላይ እየሆነ በመሄድ ላይ ነው።

ይሀ ሁሉ እዳ  የመጣብን ደግሞ ባለሁለት ወደብ የነበረችው ሀገራችን ወደብ አልባ በመሆኗ ነው። በዚህ አንጻር ለኢሳያስ ( ሸአብያ) አገዛዝ አሳልፎ የተሰጠው የኢትዮጵያ ታሪካዊና ህጋዊ ግዛት በመሰረታዊ እድገታችንና አቅም ግንባታ ላይ እያደረገ ያለውን ቀጥተኛ ተጽእኖ በመጠኑም ቢሆን መመልከት ይጠቅማል።

ሸአብያ ኤርትራን ተረክቦ አስመራ ላይ መንግስት ከመሰረተ ወዲህ ኢትዮጵያ በአሰብም ሆነ በምጽዋ ወደቦች በኩል ለምታስገባውም ሆነ ወደውጭ ለምትልከው ምርት (እቃ) ለአቶ ኢሳያስ መንግስት ቀረጥ እና፣ የወደብ ኪራይ ስትከፍል ቆይታለች፡፤ በአውሮፓ አቆጣጠር ከ 1998 ጦርነት ወዲህ ደግሞ የአሰብንም ሆነ የምጽዋን ወደብ መጠቀም አቁማ የወጭና የገቢ ንግዷን በጂቡቲ በኩል ካደረገች በሓላ ለጅቡቲ የምትከፍለው ገንዘብ እጅግ ብዙ ሆኗል፡፡ ይህ ወጪ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው።

በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ የገቢና ወጪ ንግድ ዘጠና ከመቶ (90%) ያክሉ የሚካሄደው በጂቡቲ በኩል ፡ ነው። የኢትዮጵያ የፋይናነስና የኢኮኖሚ እድገት ሚኒስቴር የነበሩት አቶ አህመድ ሸዳ በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ2012 ላይ እንደተናገሩት “ ኢትዮጵያ ለባህር ወደብ ክፍያ በየእለቱ ሁለት ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ትከፍላለች”፡፡ ይህም ማለት የሀገሪቱን የውጭ ንግድ 16% ያክሉን ለጅቡቲ የወደብ ኪራይ ታሰረክባለች  ማለት ነው። http://addisstandard.com…

የአለም ባንክ የ2013 ሪፖርተ እንደሚያሳየው የራሳቸው ወደብ የሌላቸው ሀገሮች አንድ ኮንቴነር አቃን ወደውጭ ለመላክ የሚያወጡት ውጪ ባውሮፓውያን አቆጣጠር በ2006 አሜሪካን ዶላር 2220 ነበር። ይህ ዋጋ በ2013 አመተ ምህረት ወደ 3000 ያሜሪካን ዶላር ከፍ ብሏል። ባንጻሩ የራሳቸው ወደብ ያላቸው ሀገሮች ለተመሳሳይ ኮንቴይነር ወጫቸው በግማሽ (50%) ዝቅ ይላል። http://addisstandard.com/ethiopia-spending-two-million-usd-per-day-for-transit-costs/

ይህን ሁኔታ ከሀገራችን እውነታ ጋር ስናዛምደው እጅግ የሚዘገንን ሁኔታን እናያለን፡፡ራሱ መንግስት ያመነው ለጅቡቲ የሚከፈለው በቀን 2 ሚሊዮን ዶላር የወደብ ወጪ የራሳችን ወደብ ቢኖረን ወጭው በ50% ይቀንስ ነበር ብለን ብናስብ እንኳ የራሳችን ወገን የሆነውን የአፋር ህዝብ መኖሪያ የሆነውን የአሰብን ወደብ መጠቀም ባለመቻላችን የምንከፍለው እዳ በቀን በቀን 1 (አንድ) ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማለትም ባሁኑ ምንዛሬ ስሌት (በ21 የ ኢትዮጵያ ብር ምንዛሬ በቀን 21 ሚሊየን ብር )  በአመት ደግሞ 365 ሚሊዮን ዶላር ማለትም 7፣ ቢሊዮን፣ 665፣ ሽህ የኢትዮጵያ ብር  ያክል ኢትዮጵያ ታጣለች ማለት ነው ። ይህ በዝቅተኛ ስሌት  ሲታሰብ ነው።

በዚህ ስሌት ላለፉት 15 አመታት ብቻ የደረሰውን አላስፈላጊ ወጭ ለማስላት (የባከነ ገንዘባችን) የዶላሩ ምንዛሬ በየጊዜው ስለሚለዋወጥወ በማከላዊ ደረጃ ምንዛሬው  1 ዶላር በ 17 የኢትዮጵያ ብር ነበር ብለን ብንወስድ በ15 አመት ውስጥ ያጣነው 15 X 365  = 5,475,000. (አምሰት  ቢሊየን አራት  መቶ ስባ አምሰት  ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር)  በማከላዊ ምንዛሬ ባንድ ዶላር 17 የኢትዮጵያ ብር ሂሳብ ሲመነዘርም 93፣ ቢሊየን 075 ሽህ (ዘጠና ሶስት ቢሊየን ሰባ አምስት ሚሊየን)  የኢትዮጵያ ብር ያክል ነው።<

የገንዘቡን መጠን በማየት ብቻ ሰርአቱ የወሰደው አርቆ አሳቢነት የጎደለው እርምጃ ምን ያህል ኪሳራ በሀገራችን ላይ እንዳደረሰ መረዳት የሚቻል ቢሆንም በዚህ ገንዘብ በሀገራችን ውስጥ ምን ማድረግ ይችላል (ይችል ነበር) የሚለውን መመልከት ደግሞ የሁኔታውን ተጽእኖ ይበልጥ ለመረዳት እንድንችል ይረዳናል።

የኢትዮጵያ ህዝብ እየከፈለ የሚገኘው ቀጣይ ዋጋ

በአለፉት 15 አመታት የተከሰተውን ድርቅ ሙሉ በሙሉ ያለምንም የውጭ እርዳታ መቋቋምና አንድም ህጻን በረሀብ እንዳይሞት ማድረግ ይቻል ነበር።

ሀገራችን ባለፉት 15 አመታት ውስጥ ተከታታይ ድርቅና ረሀብን አሳልፋለች። በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ሁሉ ችግሩን ለመወጣት የሚሰፈልገው ገንዘብ የሚመጣው በማያቋርጥ ልመና ባብዛኛው ከባእዳን በተለይም ከምእራቡ መንግስታት ነው።

ብዙወች የዝናብ እጥረትና ድርቅ የተፈጥሮ ውጤት  ስለሆኑ ከቁጥጥር ውጭ ናቸው ማንም ሊወቀስበት አይገባም ይላሉ፡ ይህ ትክክል አይደለም፣ ድርቅ ተፈጥሮአዊ ነው ብንል እንኳ፣ ይህ አይነቱ የተፈጥሮ መለዋወጥ የሚያስከትለውን አደጋ ለመቋቋም ሀገሪቱ ለምን በቂ መጠባበቂያ አላከማቸችም ወደሚለው ጥያቄ ይወሰደናል። የተለያየ መረጃ በግልጽ እንደሚያሳየው፣ ሀገራችን ወድብ አልባ እንድትሆን በመደረጉ የተነሳ  የምንከፍልውን ወጭ ማስወገድ ብንችል በየጊዜው የተከሰተውን ረሀብ ያላንዳች የውጭ እርዳታ ለመቋቋም የሚያሰችል ሀብት ማከማቸት ትችላለች ። ይህን በመረጃ ለመመልከት ያክል በምእራባውያን አቆጣጠር በ2008 የተከሰተው 10 ሚሊየን ወገኖቻችንን ያጠቃውን ድርቅ ለመቋቋም ሀገራችን ያሰፈልጋታል ተብሎ የነበረው US$460 ዶላ ነበር http://www.wfp.org/…

ይህ ገንዘብ ባንድ አመት ከሶስት ወር ውስጥ ለጅቡቲ ለወደብ የምንከፍለው ገንዘብ ነው።

አሁን በ 2015 /2016 ከአልኒኖ (El Niño) ጋር በተዛመደ የተከሰተው ድርቅ እስከ 15 ሚሊዮን የሚጠጉ ወገኖቻችንን በረሀብ እየገረፈ ይገኛል። ይህን አደጋ ለመቋቋም በሚቀጥሉት ስድስት ወራት  $285 ሚሊየን ዶላር  (£173m) ያሰፈልጋል ሲል የተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም ገልጧል http://news.bbc.co.uk/2/hi/africa/8319741.stm ። ምናልባትም በአመት ውስጥ ከላይ የተገለጸው ገንዘብ ሁለት እጥፍ ያስፈልጋል ብለን ብንገምት ባጠቃላይ እስከ 855 ሚሊየን ያሜሪካ ዶላር ያሰፈልጋል ማለት ነው።

ዲሰምበር 9፣ 2015 ታትሞ ለንባብ የበቃው ሪፖርተር ጋዜጣ ሀገሪቱን ባለስልጣናት ጠቅሶ አሁን የሚታየው ድርቅ እያስከተለ ያለውን ጉዳት ለመቋቋም 1.4 ቢሊየን ዶላር እንደሚያሰፈልግ ዘግቧል። http://vps17307.inmotionhosting.com…

ኢትዮጵያ በያመቱ 365 ሚሊዮን ዶላድ ያላግባብ ለጅቡቲ ለወደብ ክፍያ እንደምታወጣ ስናስብ ይህን ታይቶ የማይታወቅ እየተባለ የሚነገረውን ድርቅ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ያለምንም የውጭ እርዳታ የአራት አመት የወደብ ወጫችን ብቻ ሊሽፍንልን እንደሚችል ማሰብ ተገቢ ነው።

ይህ ባለመሆኑ ብዙ ሽህ ኢትዮጰያዊ ህጻናት ፣ አዛውንቶችና ሌሎችም ወገኖቻችን ምግብ አጥተው ህይወታቸው እየተቀጠፈ እንደሆነ ስንመለከት  ከፍተኛ ብስጭትና፣መጠን የሌለው ቁጣ ቢሰማን ያለምክንያት አይደለም።

ለያንዳንዱ የሀገሪቱ ክልል 10 ቢሊየን 350 ሚሊየን (አስር ቢሊዮን 350 ሚሊየን) የኢትዮጵያ ብር ተጨማሪ በጀት መመደብ ይቻል ነበር።

ኢትዮጵያ ባሁኑ ሰአት በ9 ያስተዳደር ክልሎች  የተዋቀረች ነች ፡ ይህ የባከነ ገንዘብ ለአያንዳንዱ ክልል እኩል ቢከፋፈል ኖሮ አሁን ባላቸው አመታዊ በጅት ላይ በአመት በአመት ለያንዳንዱ ክልል ቢያንስ 690 ሽህ  ( ስድስት መቶ ዘጠና ሽህ ብር  ) በ15 አመት ውስጥ ደግሞ ለያንዳንዱ ክልል 10 ቢሊየን 350 ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር ተጨማሪ በጀት መመደብ ይቻል ነበር።ይህ ሲሆን ደግሞ በተጨማሪው ገንዘብ ምን ያክል መምህራንን፣ የጤና ባለሙያወችን ፣ የልማት ሰራተኞችን የእርሻ ባለሙያወችን መቅጠር እንደሚቻል ምን ያክል የልማት ሰራ መስራት እንደሚችል፣ ምን ያክል በየጎዳናው የሚንከራተቱ ህጻናትን፣ እናቶችና አዛውንቶችን  ለመታደግ እንደሚያስችል ምን ያክል የድንገተኛ አደጋ መቋቋሚያ ፕሮጋራም ማዘጋጀት እንደሚቻል ወዘተ ማገናዘብ አስቸጋሪ አይደለም።

የዘንድሮውን የ2008 (የ2015/2016ቱን) የሀገሪቱን አጠቃላይ በጀት 50% መሽፈን ይቻል ነበር።

ከሀሪቱ አጠቃላይ በጀት አኳያ ሲታይ ደግሞ፤ የኢያትዮጵያ ትልቁ ባጀት እየተባለ የሚጠቀሰው ባውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 የተመደበው 11 ቢሊየን ዶላር ነው www.theeastafrican.co.ke/… ። ይህ ማለት ለ15 አመት በወደብ አልባነታችን የባከነው ገንዘባችን የአገሪቱን ትልቁን በጀት ከ50% በላይ ሊሸፍን በቻለ ነበር ማለት ነው።

የሀገሪቱን ከፍተኛ የካፒታል በጀት ሙሉ በሙሉ መሸፈን ይቻል ነበር

እንደ ሀገሪቱ የዘመኑ ባለስልጣኖች አነጋገር ከሆነ ለ 2015   (ባውሮፓውያን አቆጣጠር  ) ከተመደበው በጀት ውስጥ ለአጠቃላይ ካፒታል ወጭ የተመደበው ገንዘብ ውስጥ 12.1 ቢሊየን ብር ከውጭ በብርድና በእርዳታ የሚገኝ ነው። ለጅቡቲ በ2014 እና በ2015 የተከፈለው የወደብ ክፍያ ብቻ ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር 365፣000x2x21 (አሁን ባለው ምንዛሬ መሰረት ) 15 ቢሊየን 330 ሽህ ብር ነው። ማለትም ያለምንም እዳና የውጭ እርዳታ የሁለቱ አመት በወደብ ክፍያ  የምንፈልገውን የካቲታል ወጭ ሙሉ በሙሉ ሽፍኖ  ከሶስት ቢሊየን ብር በላይ ለሌላ ጉዳይ ሊውል የሚችል ትርፍ ገንዘብ ማሰቀመጥ እንችል ነበር ማለት ነው። http://allafrica.com..

በዚህ ገንዘብም ምን ያክል እወራ ጎዳና፣ ሆስፒታሎች፣ ትምርት ቤቶች ጤና ጣቢያወች፣ የልማትና ምርምር ጣቢያወች፣ ፋብሪካወች ወዘተ መመስረት እንደሚቻል መገናዘብ አይከብድም

በመላው ሀገሪቱ የአእምሮ ጤና አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ ማዳረስ ይቻል ነበር

ይህ በያመቱ በራሳችን ላይ ያመጣነው ኪሳራ በጤናና በትምህርት ያስከተለውን ተጽእኖ ለማመዛዘን ደግሞ በከፊል የሚከተለውን እንመልከት። ሐገራችን በአእምሮ ጤና አገልግሎት በኩል እጅግ  ሐላ ቀር ከሚባሉት የአለም ክፍሎች የምትመደብ ነች። በዚህ ሙያ የሰለጠኑ የአእምሮ ጤንነት የህክምና ሌሎችም ባለሙያወች (ሳይካትሪስቶች) ከመቶ የማይበልጡ ናቸው፤ በመላ ሀገሪቱ ለዚህ አገልግሎት የተከፈቱ ሆስቲታሎች ከአራትና አምስት አይበልጡም። በአጠቃላይ የአምሮ ጤንነት ችግር የሚደርስባቸው ኢትዮጵያውአን ሁሉ እጅግ አሰቃቂ የሆነ ችግር ውስጥ ነው የሚገኙት። በቅርብ የወጣ አንድ ሰፋ ያለ ጥናት እንደሚያሳየው፣ ለዚህ ችግር መሰረታዊ አገልግሎት ለማቅረብ የሚፈለገው በጀት ለአምስት አመት የሚከተለውን ይመስላል፡

posted by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s