ለኦርቶዶክስ ኤግዚብሽን ማዕከል ይከላከላል ለሌላው ፓርላማም ይፈቀዳል | ቃልኪዳን ኃይሉ

 

የተከበሩ አቶ አባዱላ ገመዳን ሳይ አንድ ተረት ትዝ አለኝ፡፡ “የሰፌዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ” የሚለው፡፡ ማለቴ እኔ በዚህ የጸሎት ስነ ስርአትና አምልኮ ጠብቄው የነበረው ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንጂ አፈጉባኤውን ስላልነበረ ነው፡፡

ይሁን ግን ቢሆንም ይህ ፓርላማ እኮ የሙስሊም፣ የኦርቶዶክስ፣ የካቶሊክም የሌላም የሌላም የሌላም አማኞች ተወካይ መቀመጫ ነው፡፡ ታዲያ በምን ስሌት ነው አባዱላ እንደገዛ ግቢያቸው እንዲህ አምልኮ የሚያካሂዱበት፡፡

ከምንም በላይ ጠሎት አድራጊዎቹ አውሮፓውያን መሆናቸውን ሳይ የሆነ ነገር መኖሩ የገባኝ፡፡ በመጀመሪያ ለሁሉም ቢሆን ኢትዮጵያውያን የሀይማኖቱ አባቶቹ እያሉ ስለምን ፈረንጆች ሆኑ? ይህ ነገር አንድ ብቻ ሳይሆን ብዙ ፍንጭ ይሰጠናል፡፡ ትልቅ የእምነት አቧራ ኢትዮጵያ ላይ ሊነሳ መሆኑ መጠቁም ነው፡፡

እንዴት ያለ ለሚለው፡፡ እንዲህ ያለ እላለሁ፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተሀድሶ የሚል አቧራ እየነፈሰ ነው፡፡ ተሀድሶ ወሬ ብቻ ሳይሆን በትክክል መዋቅር የተዘረጋለት ከላይ እስከታች ሰንሰለትና እዝ ያለው ከባድና ኃይለኛ ድርጅት ነው፡፡
እንዲህ እንደሚባለው “ጸጋ” ያላቸውን አገልጋዮች ለመምታትና ለመጎንተል የመጣ ቃል አይደለም፡፡ ይህ ማጭበርበሪያ በራሳቸው በተሀድሶዎች የተፈጠረ ቀልድ ነው፡፡ በዚያ ላይ ተሀድሶ ራሱን የቻለ ምንም አይነት አስተምህሮና ዶግማ የሌላው ከሌላ ሃይማኖት የተቀዳ ግልባጭ ነው፡፡

ይህንንም ለማረጋገጥ ተሀድሶዎች የሚያወጡትን መጻሕፍትና መፅሔቶች መመልከት ይቻላል፡፡ ከዚያ ይልቅ ተሀድሶዎች ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ በዚህ ሰአት ለምን እንዲህ የልብ ልብ ተሰማቸው? የሚለውን ጥያቄ ብናነሳ መልካም ነው?

ለተሀድሶዎች አሁን ምን አለ? አሁን ማን አላቸው? ጊዜው ደረሰ ሲሉስ ምን ማለታቸው ነው? ይህንን ሁላችንም በየልባችን እንመልሰውና፡፡ የተከበሩ አባዱላን ፎቶ ስናየው አንዳች ነገር ይነግረናል፡፡

ይህም ይህን ፎቶ ማን አነሳው? ለምንስ ለሕዝብ ተለቀቀ? ከፎቶው ጋርስ ኢትዮጵያ ውስጥ ሀምሳ ሺህ ቸርች ለመገንባት የታቀደው እቅድ ለምን ይፋ ሆነ?

ይህ ምን ያሳየናል? ምናልባትም ለዘመናት በኢትዮጵያ ላይ የነበረውን የኦርቶዶክስ ተፅዕኖ (Dominance) ለመቀየር የታሰበ አንዳች ኃይልና ሴራ ያለ ይመስላል፡፡ ግን ለምን ኦርቶዶክስ ተፅእኖ በኢትዮጵያ ላይ እንዳይኖር ተፈለገ? ኢትዮጵያዊነትን ስለሚያጎላ ከብሐየር ይልቅ ሕብረ ብሔርን ስለሚያቀነቅን፤ ለአድዋ ጦርነት አሌ የማይባል ድርሻ ስላለው፡፡ በዚህም ነጮች ባጠቃላይ ቅር ስላላቸው ወይስ ለምን?

ሌላ ጥያቄ ኢትዮጵያውያን እውነት የ“ቸርች” እጥረት ነው ያለባቸው ወይስ የእውነተኛ አገልጋይ፤ እውነት ኢትዮጵያ ክርስትናን በመንግስት ደረጃ አንድ ሺህ ስድስት መቶ አመት ያስቆጠረች፤ የክርስቶስን መወለድ ካወቀችና አምላክነቱን ካመነች ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አመት (ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ ልብ ይሏል) የሆናት ሀገር ለምን አሁን ተጨማሪ “ቸርች” አስፈለጋት? ለምን ሀምሳ ሺህ?

አዲስ የሚመጡ አማኞች ይኖሩ ይሆን? ከየትኛው እምነት? የተሀድሶዎች ሚናስ እዚህ ላይ ምን ይሆን? ሌሎች ባለስልጣኖች በዚህ ላይ ሌሎች አማኞች የሚያነሱትን ቅሬታ እንዴት ያዩታል? የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስተር የሚለከተሉት እምነትና በማሕበረ ቅዱሳን ላይ እየደረሰ ያለው ጫናና መከራ እንዴት ይታይ ይሆን?

እስኪ እነዚህን ጥያቄዎች እየመለሰን “የሚመጣው ዘመን እንዳይቀድመን እንዘጋጅ” እንዲል ማሕበረ ቅዱሳን፡፡

.zehabesha

posted by tigi flate

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s