የጋምቤላው ጉዳይ] ለዛሬ ደማችንን እንልሳለን | ከታምራት ነገራ

ከማንኛውም አደጋ ሊጠብቁን ሲገባቸው ከውስጣችን ሆነው የሚያጠቁንን ፤ ለጠላት አልሞ ተኳሽ አስተኳሽ የሆኑብንን ምን እንደምናደርግ ግራ ገባን እንጂ በውጭ ኃሎች መጠቃቱንም፤ የመጣውንም ኃይል መክቶ መመለሱንማ በሚገባ እናውቅበታለን፡፡ የውጭ ሚዲያ “በሊቢያ ኢትዮጵውያን እንደ ዶሮ ታረዱ” ብሎ ሲነግረን የኛው የእራሳችን የተባለው መንግስት ደግሞ “ሟቾቹ ኢትዮጵያውዊ መሆናቸው አልተጣራም” አለን፡፡ የሟቾች ፎቶ ሲመጣ አብረን ብይ ተጫውተን ፤ ጮርናቄ ተቃምተን ፤ቪዲዮ ቤት ተጋፍተን ያየነው አብሮ አደግ ጓደኞቻችን ሆነው አረፍነው፡፡ ዛሬ ደግሞ የሱዳን ሚዲያዎች እራሳቸው “ጋምቤላ ውስጥ የተገደሉት ኢትዮጵውያን ቁጥር ከ 200 በላይ ነው” ብሎ ሲዘግብ የእኛው መንግስት “የሞቱት ቁጥር 140 አልበለጠም” ይለናል፡፡ በእኛ ላይ ለሚደርሰው ጥቃት ትክክለኛ መረጃ እንኳ ለማግኘት መንግስታችንን ማመን አቃተን፡፡ፎቶ ምንጭ: ሐና

 

በባዕድ ከተጠቃነው በእኛው ወገን፤ በእኛው መንግስት የተጠቃነው በዛ፡፡ ጥቃቱም፤ የደረሰብንም ቁስል ፤የቁስሉ ሕመምም እኛው በእኛው ሆኖብን ከባዕድ እጅ ይልቅ አመመን፡፡ በዚህች አላቂ ትንሽ እድሜ ለአንድ ቀን እንኳን አንገታችንን ቀና በሚያስደርግ በምናምነው መንግስት መወከል የመይጨበጥ ሕልም ሆነብን፡፡ በዚህ ሁሉ ውርጅብኝ ውስጥም ሆነን፤ ከእኩለሌሊት በበረታ ጭለማ ውስጥም ታስረን አንድ ተስፋ ይታያል፡፡ ምን ብንቆስል መቆጨት አላቆመንም፡፡ ምን ያህል ደጋግመው ቢያቆስሉን ለአገራችን እህህ እማማ ብሎ ማብሰልሰሉን መታመሙን አልተውንም፡፡ ግድ መስጠት ያቆምን መታመም ያቆምን ቀን ያን ቀን ሞትን፡፡
ደማችንን እየላስንም፤ ቁስላችንን እያስታመምንም ቀን እንጠብቃለን፡፡ ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ሲሰብር አይተናል፡፡ ቀን የወጣለት አንበሳ ደግሞ ምን እነደሚያደርግ እናያለን፡፡ ይህን ቀን እኛ ባናይ እንኳን ቁስላችንን ፤ቁጭታችንን ለልጆቻችንም ቢሆን እናስተላልፋለን፡፡
ለዛሬ እናለቅሳለን፤ ለዛሬ ደማችንን እንልሳለን…
Posted by: tigi flate
zehabesha
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s