የኢትዮጵያና ኤርትራ መንግስታት የሚያመሳስላቸው የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ይዞታ

ኤርትራዊው ጋዜጠኛ ስዩም ጸሃየ በአፍሪካ ለረጂም ጊዜ ከታሰሩ ጋዜጠኞች አንዱ ነው /ፎቶ - ዋን ዴይ ስዩም(onedayseyoum.com)ዌብሳይት/

የዓለም የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ቀን በዛሬውለት ሲከበር፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ ምንም እንኳን የጋዜጠኞች ይዞታቸው ቢለያይም “አፋኝ” መንግስታት መሆናቸው ነው የተስተጋባው። የአለም የመገናኛ ብሀን ነጻነት ቀን ከመከበሩ አስቀድሞ የጋዜጠኞች ይዞታና የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ሁኔታ የሚያሳስባቸው የመብት ተሟጋች ድርጅቶች የተለያዩ ዘገባዎችን አውጥተዋል።

ኤርትራዊው ጋዜጠኛ ስዩም ጸሃየ በአፍሪካ ለረጂም ጊዜ ከታሰሩ ጋዜጠኞች አንዱ ነው። 14 ዓመትና 226 ቀናትና 15 ሰዓታት በላይእስካሁን ቤተሰብ ሳይጠይቀው በእስር ላይ ቆይቷል።

በህይወት መኖሩን የሚያውቅ ማንም ሰው የለም። በድረገጽ የእህቱ ልጅ የ19 ዓመቷ ቨኔሳ በርኸ የኤርትራን ቴሌቭዥን ከመሰረቱት አንዱ እንደሆነ የምትናገረው አጎቷ ስዩም ጸሃየን ስቃይና ሰቆቃ በማስታወስ፤ እሱና ሌሎች ኤርትራዊ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ በመጠየቅ ላይትገኛለች።

“የሰጡን ማብራሪያ የለም፣ ፍርድ ቤት አልሄደ፣ ከቤቱ ሲወስዱት እንኳ ለምን እንደሚታሰር አልተገለጸለትም። የት እንዳለ አያውቁም፤ በህይወት መኖሩን አያውቁም፤ በተለይ ደግሞ ቅርብ የቤተሰቡ አባላትም ምንም መረጃ የላቸውም። ልጆቹም ባለቤቱም አባታቸው የት እንደሚገኝ አያውቁም። በጣም አሳዛኙ ሁኔታም ይሄ ነው፤ አሰቃቂ ሁኔታ ነው።” ብላለች።
ኤርትራዊው ጋዜጠኛ ስዩም ጸሃየ በአፍሪካ ለረጂም ጊዜ ከታሰሩ ጋዜጠኞች አንዱ ነው /ፎቶ - ዋን ዴይ ስዩም(onedayseyoum.com)ዌብሳይት/

ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከምርጫ 97 ጀምሮ ለዓመታት ሲታሰርና ሲፈታ፤ መልሶ ሲታሰርቆይቷል። በአሁኑወቅት በፍርድ ቤት ጥፋተኛ በተባለበት የሽብር ወንጀልየተፈረደበትን የ18 ዓመታት እስራት 4ኛ አመት ይዟል።

እስክንድር ነጋ

እነዚሁ ሁለት ጋዜጠኞች በሀገራቸውም ሆነ በዓለም ዙሪያ ብቸኞች አይደሉም። በዓለም ዙሪያ ከሰባት ሰዎች መካከል ስድስቱ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ባልተጠበቀባቸውና የጋዜጠኞች ደህንነት ዋስትና በሌለባቸው ሀገሮች ይኖራሉ። በዓለም ዙሪያ ላለፉት 12 ዓመታት የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ያለማቋረጥ ማሽቆልቆሉን ባለፈው ሳምንት በዋሽንተን ዲሲ በፍሪደም ሀውስ ይፍ የሆነ ጥናት ጠቁሟል።
.voanews.
poseted by tigi flate
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s