በቦሌ ቡልቡላ ቤታችን አይፈርስም ያሉ ወገኖች የፌደራል ፖሊሶች ጥይት ራት ሆኑ

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 12 በተለምዶው ቦሌ ቡልቡላ በተሰኘው አካባቢ በሕገወጥ መንገድ ተሰርተዋል በሚል የፌደራል ፖሊሶች እና የአካባቢው አፍራሽ ግብረሃይል ዛሬ ጠዋት ቤቶችን ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱ ከአካባቢው ሕዝብ ጋር በተነሳ ግጭት በርካቶች መቁሰላቸውና ህጻናት ሳይቀሩ መሞታቸው

ከስፍራው የሚመጡ መረጃዎች እንደሚያመለከቱት “ከቤታ

ከስፍራው የሚመጡ መረጃዎች እንደሚያመለከቱት “ከቤታችን ወዴት እንሂድ?” ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በፌደራል ፖሊሶች እና በአፍራሽ ግብረሃይሉ ቤታቸው ሊፈርስባቸው ሲዘጋጁ ግጭቱ ጀምሯል:: ከዚያም የፌደራል ፖሊሶች ወደሕዝቡ የተኮሱ ሲሆን እስካሆን በግምት 9 ወይም 10 የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉና ሌሎችም በርካቶች መቁሰላቸው ተሰምቷል:: ቤቶችም መፍረሳቸውን ቀጥለዋል::

ምንጮች እንደሚሉት በኦሮሚያ ሕዝባዊው አመጽ ከተነሳ በኋላ ፌደራል ፖሊሶች ለህዝብ ተቃውሞ ምንም ዓይነት ሰላማዊ ምላሽ መስጠት አቁመዋል:: በቀጥታ ወደ ሕዝብ መተኮስ የጀመሩ ሲሆን ዛሬም ቤታችንን አታፍርስ; እኛን አፈናቅላችሁ መሬቱን አትሽጡ ባሉ ወገኖች ላይ ምላሹ ጥይት መሆኑ ብዙዎችን አሳዝኗል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ሕዝቡ በፌደራል ፖሊሶቹ ላይም ጥቃት ማድረሱን መረጃዎች የሚጠቁሙ ሲሆን ዘ-ሐበሻ ምን ዓይነት ጉዳት በፖሊሶቹና አፍራሽ ግብረሃይሉ ላይ እንደደረሰ ለማጣራት ያደረገችው ጥረት አልተሳካም::

በአካባቢው ያለው ውጥረት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ እንዳየለ ነው:: ጉዳዩን ተከታትለን ለመዘገብ እንሞክራለን:

.zehabesha.

posted tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s