በአማራ ክልል በርካታ ዞኖች ነዋሪዎች ከምግብ እጥረትና የተነሳ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ለመመገብ መገደዳቸውን ተነገረ

ኢሳት (ሰኔ 16 ፥ 2008)

ድርቅ ጉዳት እያደረሰ ባለባቸው የአማራ ክልል በርካታ ዞኖች ነዋሪዎች ከምግብ እጥረትና አቅርቦት የተነሳ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ለመመገብ መገደዳቸውንና ህጻናት ክፉኛ እየተጎዱ መሆኑ ተገለጠ።

በሰቆጣ ከተማ ነዋሪ የሆኑትና የአራት ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ እህተ አሻግሬ ከምግብ እጥረት የተነሳ የነበራቸው ክብደት ወደ 40 ኪሎግራም መቀነሱንና ልጆቻቸም የከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን ለጀርመን የዜና አገልግሎት አስረድተዋል።

የሚቀርብላቸው የምግብ እርዳታ በበቂ ሁኔታ ባለመኖሩ ምክንያት በአሁኑ ሰዓት የቤተሰብ አባላቱ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ለመመገብ መገደዱን የከተማዋ ነዋሪ ተናግረዋል።

ሳልገዝር አሻግሬ የተባለ የሶስት ወር ህጻን እስከ ስድስት ኪሎግራም ድረስ መመዘን ቢጠበቅበትም በምግብ እጥረት የተነሳ ህጻኑ 2.2 ኪሎግራም ብቻ ክብደት እንዳለው የዜና አውታሩ በአካባቢ እየደረሰ ስላለው የድርቅ አደጋ አስመልክቶ ባቀረበው ሪፖርት አመልክቷል።

በሰቆጣና አካባቢው ተመሳሳይ ችግሮች እየተባባሱ መሆኑን የገለጹት የእርዳታ ተቋማት በኩላቸው በአማራ ክልል ብቻ 2.3 ሚሊዮን ህዝብ ለአስቸኳይ የምግብ እጥረት ተጋልጦ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅት በሰቆጣና አካባቢው በምግብ እጥረት ከፍተኛ ጉዳይ የደረሰባቸው ህጻናት በማገገሚያ ጣቢያ ተገኝተው ልዩ እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑ ታዉቋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ህጻን ወደዚህ ተቋም መወሰድ ባይቻል ኖሮ በህይወት ሊኖር እንደማይችል ወ/ሮ እህተ በአካባቢው ጉብኝንት ላደረገው የጋዜጠኛ ቡድን አስረድተዋል።

ወ/ሮ ፋንታነሽ ጥላሁን የተባሉ የአራት ልጆች እናት በበኩላቸው ልጆቻቸው ከምግብ እጥረቱ የተነሳ ለአካል እና ለጤና ችግር መዳረጋቸውን ከዜና አውታሩ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል።

የተባበሩትን መንግስታት ድርጅት ከምግብ እጥረት ተጋልጠው ከሚገኙት ወደ ስድስት ሚሊዮን ህጻናት መካከል ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑት የከፋ የምግብ እጥረት ጉዳት እያደረሰባቸው መሆኑን ይገልጻሉ።

opsetd by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s