የአማራ ሕዝብን ትግል ለማጥላላት ሕወሃት ሩጫ ላይ ነው | የኮሎኔል ደመቀን በፍርድ ቤት ስም ለዘላለም እስረኛ አድርጎ ለማሰቀየት ተወስኗል

ሕዝቡና ዙሪያውን የከበበው መከላከያ ሰራዊት ተፋጠዋል

(ዘ-ሐበሻ) የሕወሃት አገዛዝ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ወደ ጎን በማድረግ ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በወልቃይት ተወላጆች ላይ የፈጸመው ግፍ አልበቃ ብሎ ሐምሌ 4 ሌሊት በሕዝብ ተወካይ ኮሚቴዎቹ ላይ በወሰደው የአፈና እርምጃን በመቃወም እጄን አልሰጥም ያሉት ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ሊገሏቸው ተኩስ የከፈቱባቸውን ከትግራይ የመጡ ልዩ ሀይል አባላት መካከል ሁለት ገድለዋል። ኮሎኔሉን አናስነካም ካለው ሕዝብ የአካባቢው የጸጥታ ሀላፊዎች በሽማግሌ በጎንደር አንገረብ እስር ቤት ለጊዜው እንዲቆዩ ከሕዝብ ጋር የገቡትን ቃል አፍርሰው ሕወሓት የፌዴራል መንግስት በሚል የግድያ ክስ እመሰርታለሁ ሐምሌ 22 ቀን 2008 ፍርድ ቤት ይቀርባሉ መባሉን ሕዝቡ በመቃወም ላይ ነው።

በጎንደር እና አጎራባች ከተሞች በከፍተኛ ደረጃ የታጠቀ ሰራዊት በይፋና በስውር እየተንቀሳቀሰ ሲሆን የሕዝቡን ጥያቄ ይዘው የቀረቡ 22 ሽማግሌዎች ባቀረቡት ጥአቄ ለጊዜው ሰራዊቱ በጎንደር ከተማ የማይታይ ቢሆንም በዙሪያ ሰፍሮ የሕወሃት መሪዎችን ትዕዛዝ እየተጠባበቀ ነው። ጉዳዩ በማንኛውም ጊዜ ወደ ህዝቡ ላይ ለመተኮስና ለበቀል እርምጃ ተዘጋጅተዋል የሚሉ ዘገባዎች ወጥተዋል።
በሕወሓት የበላይነት የሚዘወረው የፌዴራል መንግስት የይስሙላ ስልጣን የሰጣቸው የተለያዩ ክልሎች በጎንደር የተከሰተውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት በማውገዝ ተጠምደዋል።ይህ በሕወሓት ጥሪ የሚደረግ ውግዘት ስርዓቱ በጎንደር የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ጠንካራ መሆን በተለይም ሰላም ባስን ጨምሮ ጥቂት ለአገዛዙ ይሰራሉ በተባሉ የሕወሃት ሰዎች ንብረት ላይ ጥቃት መድረሱ ድንጋጤ ፈጥሮበታል። ሰላም ባስን ጨምሮ የትግራይ ልዩ ሀይል ንብረት የሆኑ ሁለት ተሽከርካሪዎች ጋይተዋል።

በጎንደር ሕዝቡ የታፈኑና ዛሬም የደረሱበት ያልታወቀ አራት የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላትና በአሁኑ ወቅት በጎንደር አንገረብ እስር ቤት የሚገኙት የኮ/ል ደመቀ ጉዳይ በሰላም እንዲፈታ፣ ኮሎኔሉ ራሳቸውን ለመከላከል የወሰዱት እርምጃ እንደ ወንጀል የማይቆጠር ነው የሚል ጥያቄ አቅርቧል።

ከደርግ ጋር በተደረገው ትግል የተሳተፉትና በመከላከያ ሰራዊቱ እስከ ኮሎኔል የደረሱት ኮ/ል ደመቀ እና ሌሎችም የኮሚቴ አባላት የታገልነው በጉልበት ትግሬነት ሊጫንብን አይደለም መብታችን ይከበር ብለው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ቆይተዋል። የፌዴሬሽን ም/ቤት በህወሃት ባለስልጣናት ፍላጎት መሰረት የወልቃይትን ጉዳይ ለማዳፈን በመሞከሩ ሕዝቡ ሕወሃት በሀይል ጥያቄውን ለመጨፍለቅ ለወሰደው የዕብሪት እርምጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ስርኣቱ በሚገባው የጠመንጃ ቋንቋ ሲያነጋግሩት መደንገጥ ጀመረ ሱሉ ብዙዎች ተደምጠዋል።

ጎንደርን-የአማራ ሕዝብ ተቃውሞ ተከትሎ የሕወሓት ደጋፊዎች የዘር ግጭት የሚያስነሳ ቅስቀሳ በማድረግ የተጠመዱ ሲሆን በርካታ ኢትዮጵያውያን ሕወሓት ለኢትዮጵአውያን መካከል የሚነዛው የዘር ፖለቲካ ወደ ጥፋት እንዳያመራ ማሳሰብ ይዘዋል።

.zehabesha

posted by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s