ኢህአዴግ ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ የቤተክርስቲያንን አንድነት መጠበቅና ዕርቅ ማውረድ አይቻልም ተባለ

ኢሳት (ሃምሌ 19 ፥ 2008)

ሃገር ቤት ባሉ አባቶችና በውጭ ባሉት አባቶች መካከል ዕርቅን በማውረድ የቤተክርስቲያኒቱን አንድነት መጠበቅ ስልጣን ላይ ያለው መንግስት በቀጠለበት ሁኔታ የማይታሰብ ነው ሲሉ ብፁዕ አቡነ መልከ-ፀዴቅ ገለጹ።

በውጭ ሃገር ባለው የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በኩል ዕርቅ በማውረድ የቤተክርስቲያኒቱ አንድነት ለመጠበቅ ከፍተኛ ጥረት መደረጉን፣ ሆኖም በመንግስት ጣልቃ-ገብነት መክሸፉን ዘርዝረዋል።

በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሃፊ የሆኑት ብፁዕ አቡነ መልከ ፀዲቅ፣ በዋሽንግተን ዲሲ ኢሳት ስቱዲዮ ተገኘተው በሰጡት በዚህ ቃለምልልስ፣ ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስን ከመንበራቸው ከማባረር ጀምሮ የነበረውን ሂደት በዝርዝር በማስታወስ፣ በኢትዮጵያ ለውጥ እስኪፈጠርና አዲስ መንግስት እስኪተካ በሃገር ቤትና በውጭ ያሉ አባቶችን አስማምቶ የቤተክርስቲያኒቱን አንድነት ማምጣት እንደሚያስቸግር አስረድተዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s