በአፋር ክልል ባለስልጣኖች የሚደረገው የድርድር ሽፍጥ

ከአካዳር ኢብራሂም ( አኩ አፋር)

የአፋር ክልል ከተመሰርተበት ግዜ ጀምሮ ክልሉ በብዙ መንገድ መንግስትን የሚቃወሙ ተጣቂዎች ጠፍተውበት አያውቁም።
ወያኔ የአፋር ክልል የሚል ስያሜ ከላይ ሰጠው እንጂ በትክክል ወደ አፋር ሄዶ በአይኑ አይቶ ለመሰከረ ሁኔታው በግልጽ መረዳት ይቻላል።
ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ሁሉም በወያኔ የበላይነት ወይም የበላይ አዛዥነት የተያዙ መሆኑን ልብ ይለዋል።
በነገራችን ላይ የዚህ ጹሁፍ አላማ በአፋር ህዝብ ላይ የሚደርሰው ሁለገብ በደል ለመዘርዘር አይደለም።

ይልቁንስ የዚህ ጽሁፍ አላማ የአፋር ክልል ባለሲልጣናት በድርድር ስም የሚያደርጉትን ንግድ ላሳያችሁ በዬ ነው።

ያነሳሳኝም ሰሞኑን የአፋር ህዝብ ፓርቲ ከነ 400 ታጣቂዎች ወደ ሀገር ቤት በሰላም ገባ በማለት የተወራው ወሬ በማስመልከት ይሆናል።
ልብ በሉ ዜና አንባቢው ከ 400 ታጣቂዎች በላይ ያለው የአፋር ህዝብ ፓርቲ የተባለውና በኤረትራ መሽገው የትጥቅ ትግል ሲያካሄድ የነበረው ቡድን በሰላም ወደ ሀገር ተመለሰ።
እንዲህ ስል ነበረ እንግዲህ የዘገበው፣ አንድ መታወቅ ያለበት ነገር ወያኔ ላለፉት 25 አመታት በአፋር በኩል በድርድር ስም የራሱን ኪስ በራሱ የሚሰርቅበት ሁኔታ የተለመደ ሆነዋል።

ህወሀት ስልጣንን የያዘው በህዝብ ይሁንታ ሳይሆን በጠብ መንጃ ሰለሆነ በሀገር ውስጥ ከሚጮሁ ሚልዮኖች ይልቅ ወደ ጫካ የሚገቡ መቶዎች ያስፈሩታል።
እናም ሰርዓቱን በመቃወም ወደ ጫካ ከሚገቡት ማነኛዉም ድርጅቶች ወይም ግለ- ሰቦች ጋር ለመደራደር መክፈል ያለበትን ሁሉ ይከፍላል።
ይህን የተረዱት ወያኔ በአፋር ህዝብ ላይ በግዴታ የሾማቸው ካድረዎች በድርድር ስም መነገድ ከጀመሩ ቆይተዋል።
ግን በዚህ ንግድ ውስጥ የአፋር ባለስልጣናት ብቻ ሳይሆኑ ከፌደራልም አንዳንድ የደህንነት ሰዎች እንዳሉበትየ አደባባይ ምስጥር ነው።
በ1994 ዓ.ም ኡጉጉሞ ወይም አርዱፍ የተባለውን ድርጅት ለሁለት ከፍለው ሲያስገቡ በጣም ብዙ ከአርዱፍ ጋር ያልነበሩ ግን የክልሉ ክፍተኛ ባለስልጣናት የቅርብ ቤተሰብ የሆኑ ሰዎች ከጫካ እንደገቡ በማስመሰል ከድርድሩ በሚገኘው ገንዘብና ስልጣን ላይ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሲያደርጉ በተቀራኒው ደግሞ ትክክለኛው የአርዱፍ አባሎች የነብሩትን አንዳንዶቹን በወቅቱ ተመጣጣኝ የስልጣን ቦታ ተሰጥቷቸው የነበረ ቢሆንም ቀስ በቀስ ከስልጣናቸው እያነሱዋቸው የድርጅቱ ዋና መሪ የነበረው አቶ ማሃሞዳ ጋዓስን ጭምሮ ዛሬ ስልጣን ላይ ያለ የአርዱፍ አባል የለም ማለት ይቻላል።
በነገራችን ላይ በወቅቱ የአርዱፍ አባሎች ናቸው ተብሎ የተመዘገቡትን ተራ አባሎች ለያንዳንድ ሰው 5000 የኢትዮ ብር ብቻ ነበረ የሚሰጠው።
አሁን ግን ዕድገት ነው መሰለኝ መሬት ነው የሚሰጠው፣ ያውም በማህበር በማደራጀት ብሆንም ቅሉ ማህበሮቹ በማን ይመራሉ ብላችሁ እንዳትጠይቁኝ! ያው የተለመደ ነዋ።

ወደ ዋናው አርዕስት ልመልሳችሁ’…….

የአፋር ህዝብ ፓርቲ ወይም የአፋር ህዝብ ጋዲሌ ( አርበኞች ) የተባለው ድርጅት በአፋር ከተመሰረቱ ድርጅቶች ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ፓርቲው ግልጽ የሆነ ፕሮግራምና የምሁራን አመራር ያለው በመሆኑ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጲያዊ ነጻ እስካልወጣ አፋር ነጻነት ሊያገኝ አይችልም በማለት የሚያምን መሆኑን ነው።
ይህም ደግሞ በፕሮግራም ደረጃ ብቻ ሳይሆን በተግባሪም በአሁኑ ግዜ በኢትዮጲያ የነጻነት ትግል ውስጥ ትልቅ ዕውቅና ካለው አርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር በጥምረት የሚሰራ መሆኑን ለየት ያደርገዋል።

ፓርቲው ከተቻለ ለማጥፋት ካልሆነ ደግሞ ለማዳከም ሲል ወያኔ የህን አሁን የሞከረውን ዕርምጃ መውሰድ ነበረበት።

እናም ወያኔ ከአፋር ህዝብ ፓርቲ ጋር ድሪድር አድረገዋል ማለት ባይቻልም ፓርቲው እንዳስታወቀው በመንግስት ተሌቪዥን የታዩት አቶ አሎ አይዳሂስና ሌላው ጦር መሪ የነበረው ኮሎነል ሙሀመድ አህመድን የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከስልጣን አሰናብቶዋቸው ነበረ ተብሏል።

የመሪዎቹ መባረር ምክንያትም በግል ከመንግስት ጋር በመገናኘታቸው መሆኑን የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መግለጫ በወቅቱ ገልፆ ነበረ።
የሚገርመው እነዚህ ሁለት ግለ ሰቦች ከመንግስት ጋር በይፋ ድርድር በመጀመራቸው ከፓርቲው መግለጫ የወጣባቸው በ17/ 03/ 2015 ነበረ።

እስካሁን ድረስ በቲቪ ሳያሳዩዋቸው የቆዩት ለምን እንደሆነ ባይገባኝም እንደኔ ሳስበው የኦሮሞን ትግል፣ የጎንደር ትግል፣ የኦጋደን፣ ትግል ያስመረረው ወያኔ እስኪ በዚህ ለክፉ ቀን ያስቀመጥኩትን ድራማ እፎይ ልበልበት ብሎ የጋበዝን ኢህአዴጋዊ ሃራካት ድራማ ብየዋለሁ።
በነገራችን ላይ ልብ ብላችሁ ከሆነ በዜናው ከ 400 በላይ አባሎች ያለው የአፋር ህዝብ ፓርቲ በማለት ያሳዩን ስዎች አብዛኛቸው የትም ጫካ ያልነበሩ፣ ቪዲዮው ላይም የተቀረጹት አንዳንዶቹ ሳያውቁ፣ አንዳዶቹ ደግሞ ተክፍሏቸው መሆኑን አረጋግጨለሁ።
በወቅቱ ሁለት ግለሰቦች ስባረሩ ከኤረትራ በኩል 30 የሚሆኑ ተጋዮች ወደ ሀገር የገቡ ሲሆን በክልል መንግስት 120 ታጣቂዎች እጅ እንደሰጡ ተግልጾ ነበረ።
280… ምናምን ሰዎች ደግሞ EBCን በመወከል የድራማው ተዋናዮች ናቸው ማለት ነው።

 

posted by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s