የአማራ ሕዝብ ትግል፤ ብዙ እርምጃዎች ወደፊት!!

ከሙሉቀን ተስፋው

የአማራ ሕዝብ አኩሪ ታሪክ ጽፏል፡፡ የአማራ ወጣቶች የአያቶቻቸውን አርበኝነት አስመስክረዋል፡፡ ወሮበላው የወያኔ ቡድንና ተላላኪዎቹ እነደመቀ መኮንን፣ ይህ ሁሉ ሕዝብ በየአካባቢው ገንፍሎ ወጥቶ የጠየቀውን ጥያቄ፣ ከእነሱ የበለጠ ጸረ ሰላምና ጸረ ልማት ያለ ይመስል፣ “ስለሁኔታው ግልጽ የሆነ ግንዘቤ ሳይጨብጡ፣ በጸረ ሰላምና ጸረ ልማት ኃይሎች ተወናብደው በርካታ ወጣቶች ወደአመጽ ተማግደዋል” ሲሉ አድምጠናል፡፡ ወሮበላው ቡድንና ምንደኞች በጸረ ሰላምና ጸረ ልማት ኃይሎች ተወናብደው የሚሏቸው፣ በአማራነታቸው ምክንያት እየደረሰባቸው ያለውን የማያቋርጥ በደል ጠንቅቀው ተገንዝበው፣ ከወልቃይትን አማሮች ጎን መቆም አለብን፤ የወንድሞቻችን ሞት ሞታችን፣ ጥቃታቸው ጥቃታችን ነው” ያሉትንና ለዚህ ጥያቄያቸው ያለፍርሃት ከነብሰገዳዩ የወያኔ ሠራዊት ጋር የተጋፈጡትን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአማራ ልጆች ነው፡፡ ለፍርፋሪ ሲሉ ከወሮበላው የወያኔ ቡድን ጋር አብረው እወነቱን እያወቁ የተወናበዱትና ጭንቅላታቸውን የሸጡት እነማን እንደሆኑ ካወቅን ቆይተናል፡፡

የአማራ ሕዝብ ትግል ብዙ እርምጃዎች ወደፊት ተራምዷል፡፡ ከሁሉ አስቀድሞ ከወሮበላው የወያኔ ቡድን የበለጠ ጠላት እንደሌለን ግልጽ የሆነ ግንዛቤ ጨብጠናል፡፡ ከተወሰኑ ምንደኛ የብአዴን ከፍተኛ አመራር አባላት ውጪ ያለው የድርጅቱ አመራርም ይሁን አባል፣ የሕዝቡን ጥያቄ አንግቦ ባይታገልም፣ በሕዝቡ መሠረታዊ ጥያቄ ላይ እንደሚያምን፣ ይልቁንም ዕድሉን ካገኘና ከተደገፈ ከሕዝቡ ጎን ሊቆም የሚችል ኃይል እንደሆነም ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጂ ደግሞ እንደነ በረከት ስምኦን፣ ካሳ ተክለብርሃን፣ ታደሰ ካሳና ደመቀ መኮንን ያሉ ምንደኞችና የወሮበላው ቡድን ጉዳይ አስፈጻሚዎች እስካልተነቀሉ ድረስ ይህ ኃይል ለጊዜውም ቢሆን በከፍተኛ መሸማቀቅ ላይ እንደሚኖርም ግልጽ ነው፡፡
የምን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ነው?
በወሮበላው የወያኔ ቡድን ፍጹም የበላይነት የሚዘወረው የፌደራል መንግሥትና፣ እንደነ ካሳ ተክለብርሃን ባሉ የወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚዎችና ምንደኞች የሚሽከረከረው የአማራ ክልላዊ መንግሥት፣ ባለፈው እሑድ ሐምሌ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ጎንደር ውስጥ የተደረገውን ታሪካዊ ሰላማዊ ሠልፍ እና በሰልፉ የተደመጡትን የሕዝብ ጥያቄዎች አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት፣ “በጎንደር የተካሔደው ሠልፍ ካነሳቸው በርካታ ጥያቄዎች መካከል የተወሰኑት ተገቢና ከመልካም አስተዳደር ጋር የተገናኙ እንደሆኑና በአጭርና በረዥም ጊዜ ምላሽ የሚሰጥባቸው ጉዳዮች ናቸው” ማለታቸውን ሰምተናል፡፡ ሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. በደብረ ታቦርና በበርካታ የአማራ ክልል የወረዳ ከተሞች የተካሔዱትን በሺሕዎች የሚቆጠሩ አማሮች የተሳተፉባቸው ሰልፎች፣ እንዲሁም በማግስቱ ነሐሴ 1 ቀን በባሕር ዳር የተደረገው ግዙፍ ሰልፍ ተከትሎም በአገዛዙ በኩል የተሰጡት አስተያየቶች እንደተለመደው መሠረተ ቢስና በክህደት የተሞሉ ናቸው፡፡
እስኪ የመልካም አስተዳደር ችግር ስለሚባለው ተረት ተረት ጥቂት ነጥቦችን እናንሳ፡፡
ወሮበላው የወያኔ ቡድንና ተላላኪዎቹ በወልቃይት አማሮች የማንነት ጥያቄ ላይ ይህንን የመሰለ ምላሽ ሊሰጡ እንደሚችሉ በደንብ ስለሚታወቅ ነው የኮሚቴ አባላቱ ደግመው ደጋግመው “ጥያቄያችን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሳይሆን ብዙዎች የሞቱለትና እኛም መስዋዕት ልንከፍልለት የተዘጋጀነው ወሳኝ የማንነት ጥያቄ ነው” በማለት አበክረው ሲያስገነዝቡ የቆዩት፡፡ ወያኔ ጉዳዩን ከተራ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ወይም የበታችን ካድሬዎችና የወረዳና የዞን አመራሮች በሚፈጥሩት ድክመት ከተከሰተ የመልካም አስተዳደር ችግር ጋር ሊያይዘው እንደሚርመጠመጠው ሳይሆን፣ መሠረታዊ የማንነት አጀንዳ መሆኑን ሕዝባችን በሚገባ ይገነዘባል፡፡ አዎ የወልቃይት አማራ ሕዝብ በሁሉም የአገራችን አካባቢዎች እንደሚታየው የከፋ የመልካም አስተዳደር ችግር አለበት፡፡ ሆኖም የሕዝባችን መሠረታዊ ጥያቄ በወሮበላው የወያኔ ቡድንና በተላላኪዎቹ አማካይነት በግፍ ወደትግራይ ክልል እንዲካተት ተደርጎ ከ25 ዓመታት በላይ በከፍተኛ ጭቆና ሲማቅቅ የኖረው የወልቃይት አማራ ሕዝብ ማንነትን የማስከበር ጥያቄ መሆኑ በጣም ግልጽ ነው፡፡ ይህን ሊቀበሉት አይፈልጉም እንጂ ጠላቶቻችንም በሚገባ ይገነዘቡታል፡፡
የወልቃይት አማሮች ጥያቄ የ40 ሚሊዮን አማራ ጥያቄ እንጂ ወሮበላው የወያኔ ቡድንና ምንደኞች እንደሚሉት የጥቂት አመራሮች ጥያቄ አይደለም፡፡ ወያኔዎችና ጀሌዎቻቸው ይንፈራገጣሉ እንጂ ዛሬ ሁሉም አማራ የወልቃይት አማሮች ጥያቄ ምን እንደሆነ በሚገባ ተገንዝቦ ከወንድሞቹና እህቶቹ ጋር የተሰለፈበት ጊዜ በመሆኑ፣ ወገኖቻችን የሞቱለትና የግፈኛው ቡድን የቶርቼር ሰለባ የሆኑለት ጥያቄ መመለሱ አይቀረም፡፡ በዚህ ላይ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለንም፡፡
ላለፉት 25 ዓመታት ትግሉ ሲደረግ የቆየው አገራችን ከላይ እስከታች ተቆጣጥረው ከሚመዘብሯትና የዘመኑ ሰዎች ከሆኑት ወያኔዎች ጋር በመሆኑ፣ ብዙ የወልቃይት አማሮች እየታገሉ ውድ መስዋዕትነት ሲከፍሉ ቢቆዩም ደፍሮ ከጎናቸው የቆመ ብዙ ሰው አልነበረም፡፡ አሁን ያ የብቸኝነትና የተናጠል ትግል አልፏል፡፡ በዚህ ምክንያት ወሮበላው ቡድን የፈለገውን ያህል እርምጃ ቢወስድ፣ የፈለገውን ያህል አማሮችን ቢያስርና ቢገድል ትግሉ ይበልጥ እየጎመራ ይሔዳል እንጂ ጨርሶ ወደኋላ አይመለስም፡፡
ወሮበላው የወያኔ ቡድን ቅልብ የትግራይ ነብሰ ገዳዮችን አሰማርቶ የአማራ ልጆችን ቢገድል፣ ቢያቆስልና በገፍ እያሰረ ቶርቼር ቢፈጽምም፣ ከዚህ በኋላ ትግሉ ወደፊት እንጅ ጨርሶ ወደኋላ አይመለስም፡፡ አማሮች በአማራነታቸው ሲደራጁና ለአማራነት ሲታገሉ የሚያሸንፋቸው አይኖርም፡፡
ከዚህ በኋላ ሕዝባችን በአንድ በኩል ለም መሬቱን እየተነጠቀ፣ በሌላ በኩል ያለማቋረጥ ከየአካባቢው እየተፈናቀለ በመሠረተው አገር ባይተዋር ሆኖ የሚኖርበት ዘመን አብቅቷል፡፡ ወዳጃችን ማን እንደሆነ፣ ጠላቶቻችንና የጠላቶቻችን አሳዳሪዎች እነማን እንደሆኑ፣ በውድ ወንድሞቻችን ደም የተገበየ ተመክሮ ይዘናል፡፡ አሁን ወንድሞቻችን መስዋዕት የሆኑለትንና ብዙዎች የቶርቼር ሰለባ የሆኑበትን ዓላማ ለማሳካት ሌት ተቀን መሥራት ይጠበቅብናል፡፡ የሚጠበቅብን ተግባር ደግሞ በጣም ዘርፈ ብዙ ነው፡

posted by tigi flate

 

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s