ለሁለተኛ ጊዜ የጎንደር ሕዝብ ቤቱን ዘግቶ ተቀመጠ – የወያኔ የኣደባባይ ተቃውሞ ጥሪ ከሽፏል።ጎጃም ፍኖተ ሰላም ታላቅ የተቃውሞ ትእይንት እየተካሄደ ነው::

   Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ       ሁለተኛው ዙር ኣድማ በጎንደር ከተማ ተጀምሯል የሚል መረጃ ከከተማዋ በስፋት ተሰራጭቷል፤ ኣሁን የጎንደር ሕዝብ የሕወሓት ጦር ከተማዋን ለቆ ካልወጣ ምንም ኣይነት ስራ እንደማይሰራ ቤት ውስጥ በመቀመጥ ኣድማ እንደሚያደርግ በተግባር እያሳየ ነው። ===  በምእራብ ጎጃም ዋና ከተማ ፍኖተ ሰላም ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ሲሆን ሕዝቡ የሕወሓትን ስርዓት በመቃውም ላይ ይገኛል።

በትላንትና እለት ሕዝቡ ኣደባባይ ወጥቶ የትግራይ ተወላጆችን እንዲገድል በከተማዋ የወያኔ ደህንነቶች ወረቀት ቢበትኑም በኣፋጣኝ በተወሰደው እርምጃ የወያኔ ሴራ መክሽፉ ታውቋል፤ ትላንትና በተለቀቀ መግለጫ አስቸኳይ መልእክት ለጎንደር ሕዝብ በሚል የወልቃይት ማንነት ኣስተባባሪ ኮሚቴ ባወጣው ማስታወቂያ መሰረ የጎንደርን የሕዝብ እንቅስቃሴ ግብረሃይል ምንም ኣይነት ኣድማ ኣለመጥራቱንና የተጠራው ኣድማ የወያኔ ሴራ ስለሆነ የጎንደር ሕዝብ እንዳይቀበለው ኣሳስቧል። ሕዝብን ለማበጣበጥና ወያኔ የደም ጥማቱን ለማርካት የጠራው ኣመጽ ስለሆነ ማንም በዚህ የኣደባባይ ተቃውሞ ኣድማና ኣመጽ እንዳይሳተፍ ኣሳስበዋል።ወያኔ የጎንደር ሕዝብ በትግራይ ላይ ተነስ ብሎ ወረቀት በትኗል። እየተባለ ነው የማንነት ኣስተባባሪው ኮሚቴም ደግሞ እኛ ኣድማ ኣልጠራንም ማንም ሰው እንዳይወጣ መልእክቱን ኣድርሱልን ብለው ነበር።

Image may contain: outdoor
posted by tigi flate
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s