መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ (በኤፍሬም ማዴቦ)

” “ ቦርዱ ደግሞ አስለቃሽ ጪስ ተብለዉ ቢጠሩ ለአገርም ለወገንም የሚጠቅሙ ይመስለለኛል። አስለቃሽ” “ ” ጪስ ያስለቅሳል ዕምባ ባንክ ዕምባ ያጠራቅማል። አትልፋ! የስም መቀያየር ዋጋ የለዉም እንዳትሉኝ! “ ” “ ” እኔ ከ ዕምባ ጠባቂ ሺ ግዜ ዕምባ ባንክ ይሻለኛል፤ ሌላ ቢቀር ዘመድ ሲሞትበት ዕምባ ጠብ ለማይለዉ ለእንደኔ አይነቱ ሰዉ ዕምባ ያበድራል። አምላኬን የምወድ ክርስቲያን ነኝ። አዎ የአባቴን ገዳይም ቢሆን ይቅር ማለት የሚችል ልብ ያለኝ ክርስቲያን ነኝ። ይቅር ካልተባባልን የወደፊቷን ኢትዮጵያ ማየት እንደማንችልም በሚገባ የምረዳ ሰዉ ነኝ። ግን “ በይቅርታ ስም አገርና ህዝብ ሲበደል ማየትም መስማትም አልፈልግም። በደላችንን ይቅር በለን እኛም ” የበደሉንን ይቅር እንደምንል መለኮታዊ ትዕዛዝ ናት። እቺን መለኮታዊ ትዕዛዝ ነብሰ ገዳዮች የራሳቸዉ መጠቀሚያ ሲያደርጉ አንገቴን ደፍቼ አልመለከትም። የአገር ሽማግሌዎች፤ ቄሶችና ፓስተሮች በይቅርታ ስም የነብሰገዳዮች ተላላኪ ሲሆኑ ማቅለሽለሽ ብቻ ሳይሆን ዉስጥ አጥንቴ ድረስ እየገባ ያመኛል።

 

 

 

በኔ “ ” እምነት ይቅርታ የሚጀምረዉ ከራስ ነዉና የህወሓት መሪዎች ስለ ይቅርታ ቦርድ ከማዉራታቸዉ በፊት እያንዳንዳቸዉ ቢያንስ መንፈቅ ሱባኤ ገብተዉ በየወንዙ፤ በየተራራዉና በየአደባባዩ ገድለዉ ለቀበሯቸዉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ፈጣሪያቸዉንና የሟች ቤተሰቦችን ይቅርታ መጠየቅ አለባቸዉ። “ ” ይህንን ካደረጉ ብቻ ነዉ ይቅርታ ቦርድ የሚባለዉ እነሱ የፈጠሩት ተቋም ተቀባይነት የሚኖረዉ። ዛሬ “ ” ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ይቅርታ ቦርድ የሚባለዉ ተቋምና ተቋሙ ዉስጥ ያሉት ፍጹም የወያኔ አሻንጉሊት የሆኑ ተላላኪ ግለሰቦች ግን ከይቅርታ ጋር የሚያገናኛቸዉ ምንም ነገር የለም። በተለይ ፓስተር ዳንኤል ገ/ ስላሴን የመሳሰሉ ትዕዛዝ የምቀበለዉ ከፈጠሪዬ ብቻ ነዉ የሚሉ ነገር ግን የነብሰ ገዳዮችን ትዕዛዝ እየተቀበሉ ያለ ምንም ጥፋት የታሰሩ ሰላማዊ ዜጎችን አሳሪዎቻችሁን ይቅርታ ካልጠየቃችሁ እያሉ ሲጨቀጭቋቸዉ ስመለከት ኢትዮጵያ እዉነትም የነአቡነ ጴጥሮስና የነቄስ ጉዲና ቶምሳ አገር ናት እንዴ እያልኩ እራሴን እንድጠራጠር ያደርገኛል። ፓስተር ዳኔልን የመሳሰሉ እንኳን ለፈጠሪ ለገዛ ሂሊናቸዉም “የማይገዙና ወያኔ ሂዱ ሲላቸዉ ወዴት ብለዉ የማይጠይቁ ሆዳም ግለሰቦች የቤተ ክርስቲያን Pastor” “ተብለዉ ከሚጠሩ የህወሓት Patter” ተብለዉ ቢጠሩ የሚያምርባቸዉ ይመስለኛል። ፓስተር እስኪ ያስቡበት . . . ፈጣሪም የሚወደዉኮ ሰዉ እራሱን ሲመስልና እራሱን ሲሆን ነዉ! አሜን ነዉ ፓስተር? . . . አሜን! ሌላዉ ህወሓት ያንን አስቀያሚ ፊቱን በዲሞክራሲ ለመሸፈን ሲል ብቻ የፈጠረዉ ተቋም ፓርላማዉ ነዉ። በአለም ዉስጥ የማያስብ፤ የማይወያይ፤ ህግ የማያወጣና ምንም አይነት ዉሳኔ የማይወስን ግዑዝ ፓርላማ ቢኖር አዲስ አበባ ዉስጥ ያለዉ የወያኔ ፓርላማ ብቻ ነዉ። ስለ ወያኔ ፓርላማማ ባላወራ ደስ ይለኛል. . . . . ደግሞስ ይህ ሲሰበሰብም ሳይሰበሰብም የሚተኛ እንቅልፋም ፓርላማ ምን የሚወራ ነገር አለዉ? እኔማ ፓርላማዉን ባሰብኩ ቁጥር ትዝ የሚለኝ አባዱላ ገመዳ ብቻ ነዉ። መቼም አባዱላ ሲወለድ ስም ” ” “ ” “ ” ያወጣሁለት እኔ ብሆን ኖሮ ከ አባ ዱላ ዱላዉ ስለሚሻለኝ አባ ን አስቀራት ነበር። የወያኔ ፓርላማ ተረት የሚተረትበት ቤት ነዉ ሲባል በተደጋጋሚ እሰማለሁ። በፍጹም የማልስማማበት አባባል ነዉ። ተረት የሚተርተዉኮ የሚያስብ ሰዉ ነዉ፤ የሚተረተዉም ለሚሰማ ሰዉ ነዉ። የወያኔ ፓርላማ የሚያስብም የሚሰማም ሰዉ የለበትም- ይልቅ ለእናንተ መስማት ለምትችሉት ወገኖቼ ተረት ብጤ ልንገራችሁ – ተረት አበዛሁባችሁ አይደል? አይዟችሁ! እኔ ሰለማስብ እናንተም ስለምትሰሙ ነዉ። አንዴ ኢትዮጵያ ዉስጥ ማየትና መስማት የተሳናቸዉ ሰዎች ጉዳያችን በፓርላማ ካልታየልን አሉና ጉዳያቸዉን ይዘዉ ፓርላማ ሄዱ። አራት ኪሎ ደርሰዉ መንገድ ሲያቋርጡ ያየ አንድ ባለታክሲ አንዱን ማየት የተሳነዉ አቤቱታ አቅራቢ ዬት ነዉ የምትሄዱት ብሎ ጠየቀዉ። ፓርላማ ብሎ መለለት። ለምን አለዉ? ጉዳያችንን ለፓርላማ ልናሰማ . . . እነማናችሁ እናንተ? እኛ ማየትና መስማት የተሳነን ኢትዮጵያዊያን ነን። እንዴ! የኢትዮጵያ ፓርላማ ከመቼ ጀምሮ ነዉ ማየትና መስማት የተሳናቸዉን ሰዎች ጉዳይ ማየት የጀመረዉ . . . . ፓርላማዉ እራሱ እኮ“ ” ማየትና መስማት የተሳነዉ ፓርላማ ነዉ ብሎ ባለ አቤቱታዉን አሳቀዉ።
ወያኔ ደርግን አሸንፎ አዲስ አበባ ሲገባ የረባ ቅያሪ ልብስ ያልነበራቸዉ እነ ስብሐት ነጋ፤ አባይ ጸሀዬ፤ “ ” “ ” መስፍን ስዩም፤ አባይ ወልዱና ጓደኞቻቸዉ ዛሬ የሚነዱት መኪና ቤንትሊ እና ሮይስሮልስ ነዉ። የሚኖሩባቸዉ የተንጣለሉ ቪላዎች ዉበትማ እንኳን በየቀኑ እላዩ ላይ ቤቱ የሚፈርስበት ደሃዉ ኢትዮጵያዊ እነሱንም ይገርማቸዋል። እነዚህ ሰዎች በገቢያቸዉ ልክ ቢኖሩ ኖሮ የሚኖሩባቸዉን ቪላዎች እንኳን ሊኖሩባቸዉ በአይናቸዉም ማየት የማይችሉ ሰዎች ናቸዉ። እነዚህ የለየላቸዉ ዘራፊዎች ከስራ መልስ . . . ስራ እንኳን የላቸዉም . . . ከወሬ መልስ ለሁለተኛ ዙር ወሬ ሲሰበሰቡ የሚጠጡትን መጠጥ ስም እንኳን እኔ እነሱም አያዉቁም። የህወሓት ስራ አመራር ኮሚቴ አባል ሆኖ አዉሮፓና አሜሪካ ቪላና የባህር ማዶ ባንክ ሂሳብ የሌለዉ ሰዉ የለም። አዲስ አበባ ዉስጥ ትላልቆቹ ህንጻዎች የሚጠሩት በወያኔ ጄኔራሎች ስም ነዉ። መሬት የሚሰጠዉ ለእነሱ ብቻ፤ አለችሎታቸዉ ብድር የሚያገኙት እነሱ ብቻ፤ ህንጻ መስራት የሚችሉትም እነሱ ብቻ ናቸዋ። እነዚህ በጣት የሚቆጠሩ የህወሐት ባለስልጣኖች ከኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ባለፉት ሀያ አምስት አመታት የዘረፉት ገንዘብ 100 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ስራ ሳይሰራ እየተኛ ቢዉል ሰላሳ አመት ይኖርበታል። እንግዲህ ይታያችሁ እነዚህ ወስላቶች አገራችንን እንደዚህ ሙልጭ አድርገዉ “ ” ከዘረፏት በኋላ ነዉ ትናንሹን ሌባ ለመቅጣት ሙስና ኮሚሺን የሚባል ከሌባ ሌባ እየመረጠ የሚቀጣ ” ” ድርጅት የፈጠሩት። አቶ ሃይልዬን በስኳር መላስ አልጠረጥራቸዉም ነበር፤ ግን ከ አህያ ጋር ዉለዉ እቺን “ ” ስኳር መላስ ተማሩ መሰለኝ እየመረጡ የሚያስሩት ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል አይነቱን ትናንሹን ሌባ ነዉ። “ ” እዉነቱን ለመናገር ኢትዮጵያ ዉስጥ ሙስና ኮሚሺን መቋቋም አልነበረበትም – ከተቋቋመም ስሙ“ ” “ ሙስና ከማና ነዉ መሆን የነበረበት፤ አማርኛ ለማይገባቸዉ ለነፕሮፌሰር ሳሞራ ደግሞ ስርቂ ” እንተኮይኑ ከማና መባል ነዉ ያለበት . . . . ኡወ ፕሮፌሰሬ ስርቂ ከማሁም! ኢትዮጵያ ፍትህን ሳያዛባ ህዝብን በእኩልነት ያሰተዳደረ መንግስት ኖሯት አያዉቅም። ሁሉም መንግስታት ዜጎችን አላግባብ አስረዋል፤ ገርፈዋል፤ ገድለዋል። የኃይለ ስላሴ ስርዐት የኢትዮጵያን ገበሬ እንደ ዕቃ የባላባቶች ንብረት ያደረገ ፊዉዳል መንግስት ነበር። ደርግም . . . እንደ ስሙ ደብድብ፤ ርገጥ ግደል ስርዐት ነበር። ሆኖም ቅድመ ህወሓት የነበሩት መንግስታት ሌላ ቢቀር በኢትዮጵያ አንድነትና ዳር ድንበር ከባዕዳን “ ” “ ጋር አይዋዋሉም። ቅድመ ህወሓት መሪዎቻችን ኢትዮጵያን አገሬ ኢትዮጵያ ወይም አገራችን” “ ” “ ኢትዮጵያ እያሉ ነበር የሚጠሯት እንጂ እቺ አገር እያሉ አይጸየፏትም። ዛሬ ኢትዮጵያን እናት አገሬ” ኢትዮጵያ እያለ በአለም ዙሪያ ለኢትዮጵያና ለህዝቦቿ ጠበቃ የቆመዉ ዕድሜዉ አርባና ከአርባ በላይ የሆነዉ ኢትዮጵያዊ የአገር ፍቅርን እንደ ምግብ እየበላ ያደገዉ በቀሀስና በደርግ ዘመነ መንግስት ነዉ። በእነዚህ ሁለት ስርዐቶች ወቅት በተለይ በሀይለ ስላሴ ዘመን ኢትዮጵያዊ በየሄደበት ይከበር ነበር። በደርግና በኃይለ ስላሴ ዘመን የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የኢትዮጵያና የዜጎቿ ጥቅም ማስጠበቂያ ቦታዎች እንጂ የህወሓት አባላት መሰብሰቢያና የጥላቻ ዘፈን መዝፈኛ መድረኮች አልነበሩም። ኢትዮጵያዊያን በአምስትና ስድስት መቶዎች ሲገደሉና የኢትዮጵያ ህዝብ በቅዱስ ዮሐንስ ጥቁር ለብሶ ሀዘን ሲቀመጥ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ይህንን ሀዘን ይጋራሉ እንጂ ጭራሽ ሞታችንና መከራችን ያስደሰታቸዉ ይመስል የአንድን ዘር የበላይነት እያወጁ ጮቤ አይረግጡም! በዋሺንግተን ዲሲዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዉስጥ“ ” ትግራዋይነት ክቡር መንነት እየተባለ ሲጨፈር ያ በወጣትነቱ አድር ባይ ዛሬም አድር ባይ የሆነዉ ግርማ ብሩ ቁጭ ብሎ ይመለከት ነበር። ይህ ህይወቱን ሙሉ ለሆዱ ብቻ የኖረ አድር ባይ አልገባዉም እንጂ “ ” ኦሮሚያ ዉስጥ ዘጠኝ ወር ሙሉ የሱን ወገኖች የጨፈጨፉት እነዚያ ትግራዋይነት ክቡር መንነት እያሉ ሲጨፍሩ የነበሩትና የትግራይን ህዝብ ከተቀረዉ ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር ለማጋጨት ሆን ብለዉ የተነሱ የህወሓት አባላት ናቸዉ ። ኢትዮጵያ ሁለቱ የአለማችን ትልልቅ ሀይማኖቶች ክርስትናና እስልምና ከሺ አመታት በላይ ጎን ለጎን የኖሩባት አገር ናት። እነዚህ በስነ ምግባር የታነጹ መልካም ዜጎችን የሚያፈልቁ ተቋሞች ዛሬ የህወሓት “ ” ስልጣን ማስጠበቂያ ተቋሞች ሆነዋል። የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች አብዮታዊ ዲሞክራሲ
የማይዋጥላቸዉን ዜጎች ቃሊቲና ቂሊንጦ የሚልኩ የህወሓት ማጥቂያ መሳሪያዎች ናቸዉ። ዩኒቨርሲቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤቶች ገዢዎቹ ያሰቡለትን ብቻ የሚያስብ ደካማ ትወልድ የሚፈጥሩ የፕሮፓጋንዳ ተቋሞች ናቸዉ። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን አዉቀዋለሁ፤ ማወቅ ብቻ ሳይሆን የዚህ ዩኒቭርሲቲ “ ” ኩሩ ተመራቂ ነኝ፤ ይህ ዩኒቨርሲቲ እኔን እኔ ያደረገ ምርጥ የአገራችን ተቋም ነበር፤ እንደዛሬዉ ከጫካ የመጡ ተፈራ ዋልዋና በረከት ስምኦንን የመሳሰሉ በወጉ 12 ኛ ክፍል ያልጨረሱ ደናቁርት እነ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትንና እነ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘዉዴን ቁጭ አድርገዉ ታሪክ ለማስተማር ከመሞከራቸዉ በፊት! “ ዛሬ ኦሮሚያ፤ ጎንደር፤ ጎጃም ፤ ኮንሶ፤ ኦጋዴን፤ ቢኒሻንጉል፤ አፋርና ጋምቤላ ዉስጥ እንዳሰኛችሁ” ” ” ትገድሉናላችሁ እንጂ ካሁን በኋላስ ለ ህወሓት አንገዛም እያሉ ለፍትህና ለእኩልነት ውድ ህይወታቸዉን የሚሰጡት የኢትዮጵያ ወጣቶች ከሰሞኑ በረከት ስሞኦን፤ አባይ ጸሐዬና እነዚያ ሁለት አሻንጉሊቶች“EBC” “ ” ላይ ቀርበዉ የነገሩን አይነት መልካም አስተዳደር ስለጎደላቸዉ ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያ ወጣት የአንድ ዘር የበላይነት እንዲጠፋ ይፈልጋል፤ የኢትዮጵያ ወጣት ነጻነት፤ ፍትህ፤ እኩልነትና ዲሞክራሲ በተረጋገጡበት አገር ዉስጥ መኖር ይፈልጋል፤ የኢትዮጵያ ወጣት ዬትም ቦታ ይወለድ ወይም ከየትኛዉም ዘር ይወለድ የወደፊት ዕድሉ በችሎታዉና በባህሪይዉ እንጂ በዘሩ እንዲመዘን አይፈልግም። ለዚህ ነዉ ይህ ወጣት ዛሬ በአራቱም ማዕዘን ባዶ እጁን እስካፍንጫቸዉ ከታጠቁ የአግዓዚ ነብሰ ገዳዮች ጋር ፊት ለፊት የሚጋፈጠው። የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነትና ለእኩልነት የሚያደርገዉ ትግል ክፉኛ ያስደነገጠዉ ዕብሪተኛዉ ስዩም መስፍን የመንና ሊቢያ ዉስጥ የደረሰዉ ቀዉስ ኢትዮጵያም ዉስጥ መድረሱ አይቀርም ብሎ የአዞ ዕምባ እያነባ የሱንና የጓደኞቹን ምኞት ነግሮናል። ወይ አቶ ስዩም ! . . . ይህ ያነበበዉን እንኳን የማይረዳ ጅላጅል የባድሜ ጉዱን የረሳን መስሎታል። ኢትዮጵያን የመን፥ ሶሪያና ሊቢያ ወደ ተጓዙበት መንገድ የሚወስዳት ስዩም መስፍን የገነባዉን ዘረኛ ስርዐት ዘለአለማዊ ለማድረግ የሚደረገዉ የጅምላ ግድያና ጭፍጨፋ ነዉ እንጂ ይህ ዕብሪተኛ ሊነግረን እንደሞከረዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱና ለነጻነቱ የሚያደረግዉ ትግል አይደለም። የኢትዮጵያ ወጣት በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመረዉ የመብት፥ “የነጻነትና የዲሞክራሲ ትግል እነ መስፍን ስዩም EBC” ላይ ቀርበዉ ስለደነፉ የሚቆም ትግል አይደለም። አባይ ጸሐዬ፤ ስዩም መስፍን፤ ሳሞራ የኑስና አባይ ወልዱ የሚገነፍሉ ድስቶች ናቸዉ . . . . እነዚህ ጡንቻ “ ” እራሶች አልገባቸዉም እንጂ የሚገነፍል ድስት የሚያበላሻዉ እራሱን ነዉ! ቸር ይግጠመን!!! አፍሬም ነኝ ከአርበኞች መንደርebini23@yahoo.com

posted by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s