በጌድዮ ዞን ፖሊስ አዛዥ በአጋዚ ተገደለ – የቧንቧ ውሃ ተመርዟል

ሰኞ፣ ሴፕቴምበር 10 – በጌድዮ ዞን የምትገኘው ዲላ ወረዳ ፖሊስ ዋና አዛዥ በአጋዚ ተገደለሲሉ በስልክ ያነጋገርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸውልናል።

ከሶስት ቀናት ቃጠሎ፣ ዘረፋ እና ውድመት በኋላ አጋዚ በትላንትናው እለት ዲላ እንደገባ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። አጋዚ የጦር ቀጠና ምትመስለው ዲላ ከተማ እንደገባ አቶ ከበደ የተባሉትን የዞኑን ፖሊስ አዛዥ በጥይት ደብድቦ ገድሏቸዋል።

ላልውፉት ሶስት ቀናት በዲላ፣ ይርጋጨፌ፣ ወናጎ እና ፍሰሀ-ገነት የተነሳው አመጽ ያነጣጠረው በጉራጌ እና አማሮች ላይ ነበር። የጌዲዮ ተወላጆች ከአካባቢው ካድሬዎች እየታዘዙ አብያተ-ክርስትያናትን እና መስጊዶችን ጨምሮ 60 የሚሆኑ መኖርያ ቤቶችን አቃጥለዋል። ህወሃት ሕዝባዊ አመጹን መቛቛም ስላልቻለ ከ10 አመታት በፊት የነበረውን ቁርሾ በመቀስቀስ የጌዲዮ ተወላጆች በአማራ እና በስልጤ ተወላጆች ላይ ዘመቻ እንዳስነሳ ነው የአካባቢው ሕዝብ የሚናገረው።

በስልክ ያነጋገርናቸው አንዲት የአማራ አዛውንት ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ እንደወደመና የሚያርፉበት መጠለያ እንኳን እንደሌላቸው ተናግረዋል።ልጆቻቸው በሙሉ ጥቃቱን በመሸሽ ወደ ጫካ እንደገቡም ተናግረዋል:: የአካባቢው የስልጤ ተወላጆች ለግዜው በመስጊድ ውስጥ ተጠልለዋል ብለዋል።

posted by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s