ወያኔ ሊታደስም ሊታከምም የሚችል ኃይል አይደለም ! መወገድ ያለበት እንጂ !

ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር) ጥቅምት 17 ፣ 2016„

በገሀነም ውስጥ እጅግ የሚያቃጥለው ቦታ የተያዘላቸው የሞራል ቀውስ በሚታይበት ወቅት ለህዝብ ወገናዊነትን ለማያሳዩ ሰዎች ነው።“ Danteመግቢያ ሰሞኑን ወያኔ የሚያወናብደው ራሱን ለማደስ እንደተዘጋጀና ጊዜም እንደሚያስፈልገው ነው። በአገዛዙ ውስጥ የአስተደዳደር ብልሹነት አለ፣ የኪራይ ሰብሳቢነት ባህል ተስፋፍቷል፣ ሙስና ለቢሮክራሲው ማነቆ በመሆን ስራ አላሰራም በማለት የአገርን ዕድገት እየጎተተ እንደሆነ እየመላለሰ ይነግረናል። እነዚህንና „ “ ሌሎች የአስተዳደር ብልሹዎችን በየስብሰባውና በቴሌቪዢን የውይይት መድረከ ላይ የሚያወሩልን የአገዛዙ የመሪ ቁንጮዎች በሽታዎቹ ከሰማይ እንደወረዱ እንጂ እነሱ ለአጋዛዛቸው እንዲያመቻቸው ሆን ብለው የፈጠሩትና ከተበላሸ ኢ- ሳይንሳዊና አገር አፍራሽ የአሰራር ዘዴ ጋር እንደተያያዘ አድርገው አይደለም የሚያቀርቡት። በሌላ አነጋገር፣ ለከፋፍለህ ግዛ እንዲያመች በፌዴራሊዝም መልክ ተዋቀረ „ “ የሚባለውና የብሄረሰቦችን መብት የሚያስከብረው ፣ በመሰረቱ ግለሰብአዊ ነፃነትን በማፈን በክልል መልክ በተዋቀረው ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን አቀጭጮ የሚያስቀረው አስተዳደር ለሙስናና ለአስተስዳደር ብልሹ፣ እንዲያም ሲል ለአጠቃላይ ዕድገት ከፍተኛ እንቅፋት እንደሆነ ወያኔ በፍጹም ሊያምን አይፈልግም። ከዚህም ባሻገር፣ ይህ ዐይነቱ የግለሰብ ነፃነትን አፋኝና ፈጠራ እንዳይኖር ያደረገው ስርዓት በየክልሉ ራሳቸውን ያደለቡ ዋር- ሎርዶችን እንደፈጠረና ለሁለ- ገብ ዕድገት እንቅፋት እንደሆነ ወያኔ በፍጹም የተገነዘበ አይደለም። በሁለተኛ ደረጃ በዓለም አቀፍ ኮሙኒቲው ግፊት ወያኔ በ 1993 ዓ.ም ተግባራዊ ያደረገው የተቅዋም መስተካከል ዕቅድ (Structural Adjustment Program)የሚባለው፣ አብዛኛውን ህዝብ በማደኽየት ጥቂቶችን የሚያደልበው የኒዎ- ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ በአገሪቱ ውስጥ የተዛባ ዕድገት ማምጣቱ ብቻ ሳይሆን፣ አገሪቱን የቆሻሻ መጣያ በማድረግ እንደ አንድ ህብረ- ብሄርና እንደ ህብረተሰብ እንዳትገነባ የሚያደርገው ፖሊሲ ዛሬ በአገራችን ምድር ውስጥ ለሚታየው አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማህበራዊ ቀውስ ተጠያቂ እንደሆነ ወያኔ በፍጹም ሊረዳ አይችልም።

 

 

በሶስተኛ ደረጃ፣ የኢኮኖሚውን ቁልፍ ቁልፍ መስኮችን ለመቆጣጠርና ሀብት ለመዝረፍ እንዲያመች በአዲስ መልክ የተዋቀረው የመንግስት የመጨቆኛ መኪናና፣ በየጊዜው ፋሺሽታዊ መልክ እንዲይዝ እየተጠናከረ የሄደው የአገዛዝ መሳሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተዘረጋው የሚሊታሪ-ኢንደስትሪያልውስብስብና(Complex) የፊናንስ ካፒታል ጋር በመቆላለፍ በአገራችን ምድር ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ነፃነትን ማፈኑና፣ ለዕውነተኛ ዕድገትና ህብረተሰብአዊ ውህደትና ጥንካሬ ከፍተኛ እንቅፋት እንደሆነ አገዛዙና ካድሬዎቹ በፍጹም የተገነዘቡት አይመስልም። ከዚህ ስንነሳ የብልሹ አስተዳደርና ሙስና ከላይ የተጠቀሱት፣ የክልል አስተዳደር፣ የኢኮኖሚው ፖሊሲና የመንግስቱ መኪና አወቃቀርዕይንታዎች(Manisfestations) ወይም ውጤቶች እንጂ በራሳቸው እንደ ዋና ምክንያት ሊታዩ የሚችሉ አይደሉም። ስለሆነም በአገራችን ምድር አማራ በመባል በሚታወቀውና በኦሮምያ ክልል የሚካሄዱትና በየቦታው እየተስፋፉ የመጡት ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች በመሰረቱ የነፃነት ጥያቄዎች ሲሆኑ፣ ወደ ውስጥ ገባ ብለን ስንመለከት ደግሞ ላይ በተዘረዘሩት መልክ በተዋቀረው ዘራፊና(Predatory State) ፋሺሽታዊ አገዛዝ ስር አንገዛም፣ ይህ ዐይነቱ አወቃቀር የአንድነታችን፣ የኢኮኖሚ፣ የባህልና የማህበረሰብ ዕድገታችን፣ የህልውናችን፣ የብሄራዊ ነፃነታችን ፀር በመሆን ታሪክ እንዳንሰራ የሚያግዱን ናቸው በማለት የተነሱ ህዝባዊ አመጾች ናቸው። ስለሆነም ይላል ጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ወያኔና ካድሬዎች የውጭ ኃይሎች ተጠሪዎች በመሆን የውክልና ጦርነት በማካሄድ እንደ ማህበረሰብና እንደ አገር እንዳንኖር እያደረጉን ነው፤ የውጭ ኃይሎች ገብተው እንዲፈተፍቱ መንገዱን በማዘጋጀት ርስ በርሳችን እንድንጨራረስ ሊያደርጉን ነው በማለት ነው በአገዛዙ ላይ በአንድነት ከዳር እስከዳር የተነሱበት። ይህንን አገር አፍራሽ ሂደቱን ግን ወደ ተራ የአስተዳደር ብሉሽነት በመቀየርና ለማስተካከል ይችል በማስመሰል ህዝቡን በማወናበድ ላይ ይገኛል። ከዚህ ስንነሳ ተሃድሶ የሚለውን ሳይንሳዊና ፍልስፍናዊ አባባል ጠጋ ብለን እንመልከት። በእርግጥ ወያኔ እንደሚለው ራሱን ማደስ ይችላል ወይ? ፅንሰ- ሃሳቡ በየጊዜው እየተደጋገመ በመሰማቱ አብዛኛው ህዝብ ተሃድሶ ማለት ምን ማለት እንደሆን እንዲረዳው ትንሽ ማተቱ የሚከፋ አይመስለኝም። ተሃድሶ ማለት ምን ማለት ነው ? በመሰረቱ ተሃድሶ ማለት ቀድመው የነበሩ ነገሮችን በአዲስ መልክ ከአንድ ሁኔታ ጋር በማቀናጀት ለአንድ ህብረተሰብ ልዩ ዕምርታን መስጠት ማለት ነው። ተሃድሶ የሚባለው ፅንሰ- ሃሳብ ቃል በቃል ሲተረጎም ሬናሳንስ ሲሆን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በጣሊያን ምድር በ 15 ኛው ክፍለ- ዘመን ተግባራዊ የሆነና፣ የግሪክን ፍልስፍና፣ የማቲማቲክስን፣ የሳይንስን፣ የአርክቴክቸርና ሌሎችንም ግኝቶች ወይም ፈጠራዎች መሰረት ያደረገ ሁለ- ገብ የሆነ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ነው። ጸንሳሺዎቹም በ 14 ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ ላይ ኮንስታንቲኖፕል የሚባለውና ዛሬ ኢስታንቡል በመባል የሚታወቀው ከተማና ዛሬ ቱርክ የሚባለው ግዛት ሲወረር ሽሽተው ወደ ጣሊያን የሄዱ ቄሶችና ፈላስፋዎች፣ ወይም ደግሞ ኒዎ-ፕላቶናውያን(Neo-Platonic) በመባል የሚታወቁ ምሁሮች የአዳበሩትና የአስፋፉት ሰፋ ያለ የጭንቅላት እንቅስቃሴና ተግባራዊም የሆነ ነው። ይህ አዲሱ መንፈስን በማደስ የተጀመረው ምሁራዊ እንቅስቃሴ እነ ዳንቴ ካዳበሩት እንደ የአምላኮች ኮሜዲ ከመሳሰሉት ሌትሬቸሮች ጋር በመዋሃድ ልዩ ዕምርታን በማግኘት በዚያን ጊዜ በጣሊያን ምድር የተዘረጋውን አስከፊ ስርዓትና ብልሹ የሆነ የህዝብ የአኗኗርን ስልት በመቀየር የህዝቡን ጭንቅላት በማደስ ኋላ- ቀር ከሆነው አስተሳሰቡ በመላቀቅና ራሱን በራሱ በማግኘት ዕውነተኛ ነፃነትን እንዲጎናጸፍ በማድረግ ሁለንታዊ ዕድገት እንዲመጣ በር የከፈተ ሰፋ ያለ ህብረተሰብአዊ እንቅስቃሴ ነው። የዚህ ውጤት እነ ጋሊሊ፣ እነ ዳቪንቺና ሚካኤል አንጀሎና፣ እንዲሁም በሺህ የሚቆጠሩ ሳይንቲስቶችና የኦፔራ ሰዎችና ሰአሊዎች ብቅ እንዲሉ ያደረገ ነው። በሌላ አነጋገር፣ ሬናሳንስ ወይም ተሃድሶ የሚባለው መንፈስን ከዕውነተኛ ዕውቀት ጋር በማገናኘትና በማደስ የሰው ልጅ ዕውነተኛ ነፃነቱን በመጎናጸፍ ራሱን በልዩ ልዩ መልክ እንዲገልጽና፣ አንድ ማህበረሰብ እንዲመሰርትና በሰላምና በስምምነት እንዲኖር ያደረገና የሚያደርግ ሳይንሳዊና ፍልስፋናዊ ሂደት ነው። የሬናስን አፍላቂዎችና በመቀጠልም ያዳበሩትና ልዩ ዕምርታን የሰጡት ምሁሮች በመሰረቱ ምንም ወንጀል ያልሰሩና፣ መንፈሳቸውን ከእግዚአብሄር ጋር በማቀራረብ በኮስሞስ በማስመሰል በምድር ላይ ዕውነተኛ ገነትን ሊመሰርቱ የቻሉና፣ ማቴሪያላዊ ዓለምን ከመንፈሳዊ ጋር በማዋሃድ የሰው ልጅ በአርቆ አሳቢነት እየተመራ ሚዛናዊና ጥበባዊ ኑሮን እንዲኖር ሁሉን ነገር ያዘጋጁና ተግባራዊ ያደረጉ ታላቅ ምሁራን ናቸው። በሌላ አነጋገር፣ እንደ ወያኔ ከፋፋይ፣ ጨፍጫፊ፣ ህዝብን ከህዝብ ጋር በማጣላት አንድ ህዝብ በዘለዓለማዊ ትርምስ ውስጥ እንዲኖር ያደረጉ አይደሉም። በዘራፊነትና ባልተስተካከለ ዕድገትም የሚታሙ ሳይሆን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ዕውነተኛና ሃርሞኒየስ የሆነ የአርክቴክቸር ስራን ተግባራዊ እንዲሆን ያደረጉና፣ ለጠቅላላው የምዕራብ አውሮፓ ስልጣኔ መሰረት የጣሉ ናቸው። ከዚህም በመነሳት ነው በኋላ ካፒታሊዝምና የኢንዱስትሪ አብዮት ተግባራዊ መሆን የቻሉትና፣ በምዕራብ አውሮፓ ምድር ውስጥህብረ- ብሄሮች እንዲመሰረቱና እንዲጠናከሩ የተደረገው። ይሁንና ግን የሬናሳንስ መልዕክት ካፒታሊዝምን ማስፋፋት ሳይሆን፣ የየግለሰቦችን ዕውነተኛ ነፃነት በማወጅ በልዩ ፈጠራ ዘዴ ሚዛናዊ ዕድገትን ማምጣት
ነው። የካፒታሊዝም በአሸናፊነት መውጣትና የሬናሳንስ መሰረተ- ሃሳቦች ቀስ በቀስ መደምሰስ ወይም መቀልበስ ከኃይል አሰላለፍ ለውጥ ጋር የተያዘ ነው ማለት ይቻላል። ወደ ወያኔው ተሃድሶ ስንመጣ ግን በመጀመሪያ ደረጃ በድርጅቱ ውስጥ የተጠቃለሉት ግለሰቦች ከጦር ሜዳ ጀምረው በደም የተጨማለቁና የስው ልጅ ህይወትም ቅንጣት የማይሰጣቸው ሰይጣናዊ ባህርይ የተዋሃዳቸው ናቸው ማለት ይችላል። በዓለም ታሪክ ውስጥ በሰው ልጅና በህብረተሰብ ዕድገት ታሪክ ውስጥ ያልታየን ድርጊት የፈጸሙና ድርጊታቸው በሙሉ ህብረተሰብን ማከረባበትና አገርንም ማወደም ነው። ታሪክን ማፈራረስና፣ አንዱ የህብረተሰብ ክፍል ከሌላው ጋር እንዳይገናኛና እንዳይግባባ ልዩ ልዩ ፊደሎችን በመቅረጽ ቅጥ ያጣ ኑሮ እንዲኖር ባህላዊ ያደረጉና ፀረ- ዕድገትን ያስፋፋ ናቸው። በሌላ ወገን ግን እነ ዳንቴ በአስራአራተኛው ክፍለ- ዘመን ያደረጉት በዚያን ጊዜ የኢጣሊያን ህዝብ በተለያየ ዲያሌክት ይነጋገር ስለነበርና መግባባትም ስላልነበር፣ አንድ ሁሉንም ሊያግባባ የሚችል ሰዋስውና ቋንቋ በመፍጠር ለጣሊያን ዕድገት ዕምርታን የሰጡ ናቸው። ይህም ማለት የወያኔው አካሄድ የዚህ ተቃራኒና የአንድን ህዝብ መተሳሰር በማፍረስ በእንግሊዞች የቋንቋ ምሁራን፣ በመሰረቱ ተንኮለኞች በመታገዝ በአገራችን ምድር ተግባራዊ ያደረገ እጅግ አደገኛ አካሄድ ነው። ውጤቱ እንደምናየው፣ በተበላሸ ሁኔታ ወይም የአኗኗር ስልት፣ በተዝረከረከ የከተማ አወቃቀር፣ በአንድ የኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ ብቻ በመመካት በተለያየ የምርት ውጤት ሊገለጽ የሚችል የስራ- ክፍፍል እንዳይኖር ያደረገና፣ ብቃትነት ያላቸው ኢንስቲቱሽኖች እንዳይመሰረቱ በማድረግ በየአካባቢው የሰውና የተፈጥሮን ሀብት በማንቀሳቀስ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ዕውነተኛ ህዝባዊ ሀብት(National Wealth) እንዳይፈጠር ያደረገ ነው። በዚህም መሰረት በአንድ አካባቢና በአገሪቱ ምድር ውስጥ ስርዓት ባለው መልክ በኢንዱስትሪ ተከላ ላይ የተመሰረተ፣ ከሌሎች መስኮች ጋር የተያያዘ የውስጥ ገበያ(Home Market) እንዳይዳብር ያደረገ ነው። በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ በሌለበት አገርና፣ የውስጥ ገበያም እንዳይዳብር ከውጭ ኃይሎች ጋር በመቆላለፍ ሻጥር በሚሰራበት አገር ውስጥ አንድ ጠንካራ አገር ወይም ህብረ-ብሄር መመስረት በፍጹም አይቻልም። የወያኔም ተልዕኮ ይህ ሲሆን፣ ከበስተጀርባ ሆነው የሚበውዙት፣ የእንግሊዝ፣ የአሜሪካንና የምዕራብ ጀርመን የስለላ ድርጅቶችና፣ በተራድዖ ስም የሚንቀሳቀሱት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ናቸው። ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ በዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ምን ዐይነት ተሃድሶ ማካሄድ ይቻላል ? ጭፈጨፋና ተሃድሶ እዚያው በዚያው ወይስ ማጭበርበር ! እንድምንከታተለው ወያኔ በአንድ በኩል ራሴን ለማደስ ዝግጁ ነኝ፣ በዚህም ላይ ዕቅድ በማውጣት ላይ ነን ይላል። እዚያው በዚያው ደግሞ እጅግ በሚያሰቅቅ ሁኔታ ምስኪኑን ህዝባችንን ይጨፈጭፋል። በየቦታው የአጋዚ ወታደሮችን በመላክ ፋሺሽታዊ ጭፍጨፋውን ተያይዞታል። በዚያው መጠንም ሌሎች እምቢ ያሉትን ሰላማዊ ዜጎችን በማፈናቀልና ሀብታቸውን በመቀማት የቁም ስቅላቸውን ያሳያቸዋል። በሌላ አነጋገር፣ የወያኔ አገዛዘ በየቦታው እየጋለ የመጣውን ህዝባዊ ብሶትና ቆራጥ የተሞላበት ትግል በውጭ የስለላ ድርጅቶች በመታገዝና በመመከር ጭፍጨፋውን በየቦታው እያካሄደ ነው። ይሁንና ቆራጡ የጎንደርም የሆነ የኦሮሞ ወንድማችንና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ዕምቢተኛነታቸውን በማስተጋባት ለአንዴም ለመጨረሻም ጊዜ እየተፋለሙት ይገኛሉ። በአንዳንድ አካባቢዎችም ድልን እየተጎናጸፉ ነው። በዚህ ዐይነት መልክና ቁልፍ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዘርፎች እንድ አንድ ኩባንያ በተደራጀ መልክ ከአንድ ብሄረሰብ በተውጣጡ፣ ሰውነታቸው በደም በታጠበ ግለሰቦች በተያዘበት አገርና፣ በግለሰብ ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሌለበት አገርና፣ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እንዳይቻል አንድ አገዛዝ በውጭ ኃይሎች እየታገዘ መንግስታዊ መኪናዉን ፋሺሽታዊ በሆነ መልክ ባዋቀረበት አገር እንዴት አድርጎ ተሃድሶን ማምጣት ይቻላል? በፍጹም የማይታለምና የማይቻልም ነው። አንድ በኮሜዲ መልክ የቀረበ ጥንቆላ፣ አንዷ ታማ ጠንቋይ ቤት ትሄዳለች። ጠንቋይዋ የመንፈስ በሽታ የተናወጣትን ለማዳን
ያልሞኮረችው ነገር የለም። በመጨረሻ የደረሰችበት ድምዳሜ ከአቅሟ በላይ እንደሆነና መፈወስም እንዳማይቻል ነው። የወያኔም የጭንቅላት በሽታ እንደዚህ ነው። አጥፍቼ ልጥፋ በሚለው እርኩስ አስተሳሰብ የተለከፈ ስለሆነ መፈወሻ የሚገኝለት አይደለም። መፈወሻውም በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ስትራቴጂያዊ ህዝባዊ እንቅስቃሴና በሱ ላይ የተመሰረተ በማያዳግም መልክ የሚያወድመው ርብርቦሽ ነው። በሌላ ወገን የወያኔን ነፍስ ለመዝራት በልደቱ አያልነህ የሚመራው ኢዴአፓና አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ነን ባዮች የማያደርጉት ሽር ጉድ የለም። ልደቱና ሌሎች ግለሰቦችና አንዳንድ ድርጅትን እንወክላለን የሚሉት በአገራችን ምድር ውስጥ እንደዚያ ያለ ጭንቅላትን የሚዘገንንና እንቅልፍ „ “ የሚያሳጣ ድርጊት በህዝባችን ላይ እየተፈጸመ ባለበት ወቅት ወያኔ በጠራው የመወያያ ስብሰባ ላይ መገኘታቸው የቱን ያህል የህዝባችን ሁኔታ እንደማይመለከታቸው ነው የሚያረጋግጠው። እነዚህ„ “ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ኃይሎች እንደዕውነቱ ከሆነ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በአገራችን ምድር ምን እንደተካሄደ የገባቸውና የተገነዘቡም አይመስልም። ለመረዳትም የሚፈልጉ አይደሉም። የዲሞክራሲንና የነፃነትን ጉዳይ ከተራ ምርጫና ፓርላሜንት ውስጥ ተቀምጦ ከመዘባነን ጋር ነው የሚያያዙት። በዚህም መሰረት ማንም ውክልና ሳይሰጣቸው አሜሪካና አውሮፓ እየመጡ የዓለምን ህዝብ (International Community) እንወክላለን ለሚሉት የሚያሰሙት እሮሮ በመሰረቱ የህዝባችንን የዕውነተኛ የነፃነት ትግል የሚያጨናግፍ ነው። አካሄዳቸው በአገራችን ምድር ውስጥ ዕውነተኛ ዕድገት እንዳይመጣ የሚያደርግ ነው። እነዚህ ተቃዋሚ ነን ባዮች የዓለም ፖለቲካ አወቃቀርና ብወዛ በፍጹም የገባቸው አይመስልም። ያም ሆነ ይህ፣ ወያኔ ተሃድሶ እያለ የሚያናፍሰው ወሬና የሚያካሄደው የእነወያይ ስብሰባ ማዘናጊያና ራሱን ማጠናከሪያ ዘዴ ነው። አገዛዙ የሚታደስም የሚታከምም አይደለም። ህፃናትን ሳይቀር በስናይፐር የሚገድልና ሴትን ቤንዚን በማርከፍከፍ አሰቃይቶ የሚገድል አገዛዝ በፍጹም ሊታደስ አይችልም። ዕውነተኛ ተሃድሶ ሊመጣ የሚችለው ከዚህ አገዛዝ ባሻገር በሀቀኛ አገር ወዳዶችና በተገለጸላቸው ምሁራን አማካይነት ነው። ይህም ቢሆን ከህዝብ ትግል ጋር መዋሃድና የህዝቡን ኃይልነት የሚያበስር መሆን አለበት። ከዚህም ጋር ተያይዞ የመንግስቱ የመጨቆኛ መሳሪያ እንዳለ በመንኮታኮት ለዕድገት በሚያመች መልክ ከማንኛውም የውጭ የስለላ ድርጅት ነፃ በሆነ መልክ መደራጀት አለበት። ከህዝብ ጋር የሚሄድና የሚዛመድ እንጂ በህዝቡ ላይ ጠበንጃውን የሚቀስር አገዛዝ አይደለም ህዝባችንና አገራችን የሚመኙት። ከዚህም ባሻገር ዕውነተኛ ተሃድሶ በሁለ- ገብ የትምህርት ዘመቻ የሚታገዝ ሲሆን፣ የኢኮኖሚ ፖሊሲዉም በመንግስትና በህዝብ መሀከል በመደጋገፍ ላይ የተመሰረተ ሁለ-ገብ(HolisticEconomic Policy) የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲ ተግባራዊ የሚሆንበት ነው። በሌላ አነጋገር፣ አገዛዙ እስካሁን ድረስ የሚመራበትን የኢኮኖሚ ፖሊሲና የዓለም አቀፍ ኢንስቲቱሽኖችን ምክር በመጣል ርስ በርሱ የተሳሰረ የውስጥ ገበያን ሊያስገነባ የሚያስችል የኢንዱስትሪ ተከላና የቴክኖሎጂ ምጥቀትን የሚያመጣ ፖሊሲ የተሃድሶ መሰረተ- ሃሳብ ናቸው። በመጀመሪያ ግን ይህን አገዛዝ ገርስሶ በመጣል፣ ህዝባችንን ለስራ በማንቀሳቀስ መሰረታዊፍላጎቶቹን(Basic Needs) ሊያሟላ የሚችልበትን ሁኔታ ማደራጀት አለብን። በዚህ መልክ ብቻ ነው ወደ ፊት መግፋትና ቀስ በቀስም ህዝቦቿን ማሰተናገድ የምትችልና የተከበረች ኢትዮጵያን መገንባት የሚቻለው። ይህንን የተቀደሰ ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ በየቦታው በተሰበጣጠረ መልክ የሚካሄደው እንቅስቃሴ በአንድ የአስተሳሰብ ክልል ውስጥ(Unity of Thought) መካተት አለበት። ሁሉም በየፊናው ለስልጣን መታገሉን አቁሞ በአንድ ማዕከላዊ አመራር ስር በመመራት ወደ ድል ለማምራት መዘጋጀት አለበት። እየተሰበጣጠሩ መታገልና፣ የሚሆን የማይሆን ሰበብና ተንኮል እየፈጠሩ ዝናን ለማግኘትና ለመታወቅ መሞከር የህዝባችንን ሰቆቃ ያራዝመዋል። የአገራችንን መበታተን ያፋጥነዋል። ይህ ደግሞ የማንኛችንም ምኞትና ፍላጎት አይደለም። ስለዚህ ከመሰባሰብና ተወያይቶ በአንድ ሃሳብ ዙሪያ ከመታገል በስተቀር ሌላ አማራጭ ሊኖር አይችልም።

posted by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s