ጎንደር፣ ወሎ: ‹‹የወያኔ ወታደሮች አስከሬን በየቦታው ወዳድቋል›› የጎበዝ አለቆች • በወልዲያ ዩንቨርሲቲ የዐማራን ጥያቄ ያነሱ ተማሪዎች ታስረዋል፤

ከሙሉቀን ተስፋው

በሰሜን ጎንደር በወገራ፣ በአርማጭሆና በወልቃይት አካባቢዎች የዐማራ ተጋድሎ ከፍተኛ ድል አስመዝግበዋል፡፡ ትናንት ኅዳር 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ከሰዐት በኋላ በሁለት ባንዳዎች እየተመራ የመጣው የወያኔ ሠራዊት በገበሬዎች ላይ ድንገተኛ ተኩስ ከፍቶ ነበር፡፡ ቆራጦቹ የዐማራ ገበሬዎች የመጣውን የወያኔ ጦር ፊት ለፊት በመግጠም ሙትና ቁስለኛ ብቻ አድርገው በድል አጠናቀዋል፡፡ ተስፋ የቆረጡት ወታደሮች ጥቂት የገበሬ ቤቶች ማቃጠላቸውም ታውቋል፡፡


ትናንት በጃኖራ በነበረው ውጊያ በርካታ ድሎች ተመዝግበዋል፡፡ ዐሥራ ሁለት ወታደሮችን ይዞ በአንድ በር ሲዋጋ የነበረው የወያኔ ጦር ከጋንታ መሪው ውጭ ያሉት 11ዱም ተገድለው መሪው ቆስሎ በአንዱ የጎበዝ አለቃ እጅ ወደቀ፡፡ በዚህ ጊዜ የጎበዝ አለቃው (ስሙን መጥቀስ አልፈለግንም) ‹‹አንተን መግደል ለእኔ ቀላል ነው፤ ነገር ግን እኛ መገዳደልን አልመረጥንም፤ ብገድልህም ብተውህም ለእኔ ለውጥ የለውም፤ የምትድን ከሆነ ሒድ ታከም›› በማለት አሰናበተው፡፡ የሞቱ ወታደሮችን በተመለከተ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹የወያኔ ወታደሮች አስከሬን በየቦታው ወዳድቋል፤ ከ50 በላይ የሚሆን የጠላት ጦር ዶጋ አመድ ሆኗል›› በማለት መልሰዋል፡፡ 


ዛሬ ኅዳር 25 ቀን ተጨማሪ የወያኔ ጦር በእንቃሽ ቆላማ ነብር ጠማጅ በተባለ አካባቢ ሒዶ ከገበሬዎች ጋር ውጊያ ገጥሟል፡፡ የዐማራ የጎበዝ አለቆችን ከሕጻን እስከ አዛውንት በመቀላቀል ተጋድሎውን እየደገፉ ሲሆን የወያኔ ወታደሮች ዒላማቸውን በግለሰቦች መኖሪያ ቤትና ንብረት ላይ አድርገዋል፡፡ ከቦታው ስለጉዳዩ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የዐማራ ጎበዝ አለቆች በተኩስ ጩኸት ምክንያት መሰማማት አልቻልንም፡፡ ሆኖም ሁሉም ሁሉም ዐማራ በያለበት የተጀመረውን ተጋድሎ እንዲቀላቀል ጥሪ አድርገዋል፡፡ 


በሌላ ዜና ከሰሜን ወሎ ወልዲያ ዩንቨርሲቲ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዩንቨርሲቲው በሚከበርበት ወቅት የወልቃይት ጠገዴን፣ የራያ ኮረም አላማጣና የመተከልን ዐማራነት ጥያቄ ያነሱና የነ ደረጀ ደገፈውን አዲስ ሙዚቃ በመዝፈናቸው ምክንያት አድማ በታኝ ፖሊስ በመግባት 45 የሚሆኑ የዐማራ ተማሪዎችን ማሰሩን ዜና ያመለክታል፡፡ በወልዲያ ዩንቨርሲቲ የሚማሩ የዐማራ ተማሪዎች የተጋድሎውን ጥያቄ ወደፊት በተለያየ ጊዜ ማምጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡ 

posted by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s