ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን አስሬአለሁ የሚል ወህኒ ቤት ጠፋ – ታሪኩ ደሳለኝ

መንግስት ስለ ተመስገን ሁኔታ ዝምታን ከመረጠ ዛሬ ታህሳስ 4/2009ዓ.ም 5 ቀን ሆነው፡፡
ይህን 5 ቀን እኛም በመላው ሀገሪቱ ተመስገን የገኛባቸዋል ባልናቸው እስር ቤቶች ሁሉ እደጅ ብንጠናም አንደም እስር ቤት ተመስገንን አይቻለሁ የሚል አልተገኝም፡፡ ተመስገን በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ከስረኞች ሁሉ በተለየ በከፍተኛ እንግልትና በጫና ውስጥ እንደሚገኝ ደጋግምን መግለፃችን ይታወቃል፡፡ ይባሱንም በእስር ቤቱ የታመመውን ህመሙን አንዳይታከም ተከልክሎ ክህመም ጋር አንዴ ጭለማ ቤት አንዴ ቅጣት ቤት እየመላለሱት የመንግስት የእስር ጊዜውን እያሳለፈ እንደሆነ ይታወቅ ነበር… አሁን ያለውን ነገር ስለማናውቅ ነው፡፡

ከአንድ ወር ከአስራ አምት ቀን በፊት የዝዋይ እስር ቤት አስተዳዳሪዎች “አመክሮ ተገምገም” ሲሉት ተመስገን “በዚህ መንግስት አመክሮ አልገመገም” ማለቱ የእሰር ቤቱን አስተዳዳሪዎች አንደበሳጫቸው አውቀናል፡፡ ከዛ በኋላ ተመስገንን የምንጠይቀበትን ሰዓት ወደ 8 ደቂቃ ቀንሰውታል፡፡ እኛንም ስንገባና ስንወጣ አላስፈላጊ አንግልት እያደረሱብን ችላን ቆይተናል፡፡ የእስር ቤቱ አስተዳደር የተመስገንን አመክሩ ሲከለክል ከጠቀሳቸው ምክኒያቶች አንዱ አሁን ሀገሪቱ ላለችበት ሁኔታ የተመስገን ፁሁፍ ዋነኛውን ድርሻ ይይዛል ማለቱ እስረኞችን በተመለከተ የፍርድ ቤት ስራንም ጨምሬ እሰራለሁ እየለን እንደሆነ ይቆጠራል (ፍርድ ቤቶች ነፃ እንደልሆኑ ቢታወቅም)፡፡ ተመስገን በተመለከተ ፍርድ ቤት እንሄድ ወይስ ዝዋይ እሰር ቤት እያለን የምናሰበው ያንዱን ስራ አንዱ እየሰራው አንደሆነ ስልምንረዳ ነው፡፡

የዝዋይ እሰር ቤት ሹማምንቶች ሆኑ ሌሎች አለቆቻቸው ተመስገን በተመለከተ እውነታውን አንዲያሰውቁን ደግምን እንጠይቃልን፡፡ ተመስገንን በተመለከተ ለተፈጠረው ነገሮች ሁሉ የመጀመሪያ ሀላፊነት የሚወስዱት ተመስገን በጃቸው ላይ የነበረው የዝዋይ እስር ቤት አለቆችን ነው እነሱም..
1. ኮሌኔር አሰፍ ኪዳኔ የዝዋይ እስር ቤት አዛዥ
2. ኮሌኔር ደሳለኝ የእስርኞች አስተዳዳሪ
3. ኮሌኔር ገብረዋድ የእስረኞች የጥበቃ መሬና አስተባባሪ

psted by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s