በዜጎች ላይ የሚፈጸመው ሕገወጥ ደባ – ዜጎች በፈረቃና በጨለማ እየኖሩ ኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤት አገር መሸጥ ያሳፍራል።

በዜጎች ላይ የሚፈጸመው ሕገወጥ ደባ – ዜጎች በፈረቃና በጨለማ እየኖሩ ኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤት አገር መሸጥ ያሳፍራል።

Image may contain: text

Minilik Salsawi – mereja.com የወያኔው ኣገዛዝ ለጎረቤት ኬንያ በስድስት ወር ውስጥ የሸጠው ኤሌክትሪክ ኃይል ሰላሳ ኣምስት ሚሊዮን ብር ሲያተርፍ በሃገር ቤት መብራት ተቋርጦባቸው ስራ ካልሰሩ ፋብሪካዎች ለሃገሪቱ ያስገባሉ ከተባለው ውስጥ ስድሳ ሚሊዮን ብር ኪሳራ ደርሳል። ሃገሪቱን በኪሳራ ውስጥ እየዘፈቀ ሕዝብን ለድህነትና ለጨለማ የዳረገው ኣገዛዝ በታንዛኒያ አሩሻ ከተማ ሲካሄድ ከቆየው የምሥራቅ አፍሪካ ኃይል ትስስር ጉባዔ ጎን ለጎን የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ስምምነት መፈረሙ ታውቋል።ታንዛኒያ ከሱዳን፣ ከኬንያ፣ ከጂቡቲና ከሶማሌላንድ ቀጥሎ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመግዛት የተፈራረመች አምስተኛ አገር ሆናለች፡፡አምስት ሀገራት በብርሃን ደምቀው በኢትዮጵያ ውስጥ ዜጎች በጭለማ ይዳክራሉ።

ይህ ዜጎችን እያሰቃየ ኢንቨስተሮችን እያከሰረ ያለው በዝባዥ አገዛዝ በቀጣይነትም ለሳኡድ ኣረቢያ ለቡሩንዲ፣ ለሩዋንዳና ለየመን የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙም ተሰምቷል። በዜጎች ላይ ምን ያህል ደባ እየተፈጸመ እንደሚገኝ በግልጽ እያየን ነው። በመላው ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የሃይል እጥረት እየተከሰተ መብራት በፈረቃ እየተዳረሰ ለጎረቤት ሃገር መሸጥ ለሕዝብ ደንታቢስ የሆነ አገዛዝ መኖሩን በቂ ምስክር ነው። ኢትዮጵያ ከውኃ ብቻ አርባ አምስት ሺሕ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እያላት ዜጎች ላይ ግን በጭለማ እንዲኖሩ ግፍ እየተፈጸመ ይገኛል።

ይህ በወያኔ ኣገዛዝ የሚፈጸም ተደጋጋሚ እብደት ዜጎች የሚፈልጉትን የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሳያሟላ ለጎረበት ኣገር መሸጥ ለሕዝብ ያለውን ንቀት ያሳያል። እንዲሁም እንደፈለገ ወደ ሃገራቱ ምድር እየገባ የሚያፍናቸውን ለኣገዛዙ ተቃዋሚ የሆኑ ዜጎችን የበለጠ ለማፈን ይረዳው ዘንድ የሃገራቱን ኣገዛዝ ለማለሳለስ ይጠቀምበታል። ይህ ኣገዛዝ ለዜጎቹ ደንታ ቢስ መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን ከስልጣን እስካልተወገደ ድረስ በፍጹም ለውጥ እንደማያመጣ ከበፊቱ የተረጋገጠ ነው።

በሃገር ቤት የሚገኙ ፋብሪካዎች በሃይል እጥረት ኪሳራ ላይ ሲወድቁ ሰራተኞቻቸውን ሲቀንሱ ሕዝብ ለድህነት ሲዳረግ የወያኔ ባለስልጣናት የኤሌክትሪክ ሃይል ኀጠው የሚያገኙትን ዶላር ወደየ ግል ኣካውንታቸው ያዘዋውራሉ።የኣፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እና የኣስር ሺዎች ዲፕሎማቶች ከተማ የሆነችው አዲስ ኣበባ በጨለማ ማስዋጥ ኣገዛዙ የሚሰራው ሕገወጥ ተግባር ሽፋን መስጫ ነው። ተማሪዎች ከትምህርት ጥራት በደል በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ሃይል እጥረት በፈጠረው ጨለማ ውስጥ ማጥናት ኣሊያም መማር ስለማይችሉ በቂ እውቀት ማካበት እየከበደ መጥቷል። እናቶች በሃይል ማጣት እንዲሁም በማገዶ እጥረት ያቦኩትን ሊጥ ተበላሽቶ እስከመድፋት ሲደርሱ የመንግስት ስራ በደል የባንክ ሲስተምን አበላሽቶ በኪሳራ የምትኖረዋን ኣገር ለኪሳራ ዳርጓል።ይህ ተደጋጋሚው እብደት ፦ ዜጎች በጨለማ እየኖሩ ኤሌክትሪክ ለጎረቤት ኣገር መሸጥ ያሳፍራል። በዜጎች ላይ የሚፈጸመው ሕገወጥ ደባ ነው። የወያኔ ኣገዛዝ እስካልተወገደ ድረስ ዜጎች ሰላም እና እድገት ኣይኖራቸውም።

posted tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s