አደር ባዮች የዓላማ ፅናት ስለሌላቸው ፅኑዎችን ይረግማሉ፡፡

: ወያኔ ስልጣኑን ለማስረዘም ከሚጠቀምባቸው ስልቶች አንዱ በጥቅም የታሰሩ ሃሳብ የለሽ የሆኑ አደር ባዮችን መፈልፈል ነው። አድር ባይነት በየዘመን መለወጫው እንደልክፍት ብቅ ይላል፡፡ አብዛኞቹ አድር-ባዮች ሰብዕናን ባወጣው ዋጋ የሚሸጡ ናቸው፡፡ በዚህ ሽቀላና ደጅ-ጥናት ላይ የተሰማሩ ሁሉ፤ አቋም ለበስመ-አብ-ወልዱም ስለሌላቸው፤ አቋም ያለው አይጥማቸውም ወይም ከናካቴው ይጠላሉ፡፡ አደር ባዮች ቀን ለሰጠው መልካም መደላድል ለመሆኑ ዝግጁ ናቸው፡፡ ታዛቢ ዐይን ጠያቂ ታሪክ እንዳለ ይዘነጋሉ፡፡ የዓላማ ፅናት ስለሌላቸው ፅኑዎችን ይረግማሉ፡፡Minilik Salsawi

መቼም በእኛ አገር፤ ዕውነተኛ ያልሆነው ነገር ዕውነተኛ ታሪክ ይበዛል ።ትውልድ ተስፋ እንዳይቆርጥ ተስፋ እናሳየው እንጅ በጥቅም እንዳይማልል ሰፊ ስራዎች መሰራት ያስፈልጋል፡፡ ለምርጫ ዕድል እንዳለው እናስተምረው፡፡ ወላዋይ ትውልድ እንዳንፈጥር እንጠንቀቅ፡፡በአምባገንኖች ስርአት ውስጥ አደርባይነት ማስፋፋት የገዢዎች ዋነኛ ተግባር መሆኑን እና በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሆዳቸውን የሚሞሉ አደርባዮችን ሲሻቸው ልናስተምራቸው ካልጣማቸው ነቅሎ መጣል የትግሉ አንዱ አካል መሆኑን መዘንጋት የለብንም።

ወያኔ የመዋዠቅንና የአድር-ባይነትን ባህል በማስፋፋት ሁነኛ ህብረተሰብ በማክሰም ሆዳም ማህበረሰብ ለመፍጠር በመትጋት ላይ ስለሆነ ቀድመን መንቃት ያስፈልገናል፡፡ በተሳሳተ መንገድ የተሳሳተ አቅጣጫ ይዞ የሚሄድ ማህበረሰብ እንዳንይፈጠር ከልብ እንጣር፡፡ አድር-ባይነትን እና አደርባዮችን እናስወግድ፡፡ በትግሉ ውስጥ ፅናትና ዘላቂነት ከዕቅዳችን ጋር ይተሳሰሩ ዘንድ አለመዋዠቅ ሾውሸዌ አለመሆን ዋና ነገር ነው፡፡ ዕዳው በቀጥታ የራሳችን፤ በተዘዋዋሪ የልጆቻችን መሆኑን አለመዘንጋት ነው!

posted tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s