ጎሰኝነት የአንድነትና የሀገር ጠንቅ ነው

ከፍያለው አባተ (ዶ/ር) ከውጭም ከውስጥም በአማራው ሕዝብ ላይ ያተኮረ የጥቃት ዘመቻ ለረዥም ጊዜ ሲካሄድ መቆየቱና በደሉ አሁንም (የመንግሥትን ሥልጣን በበላይነት በሚመራው በወያኔ አቀነባባሪነት) ይበልጥ ተጠናክሮ በመቀጠሉ አንዳንድ የአማራ ልሂቃንን “እኛም እንደሌሎች የአማራ ጎሳ ፓርቲ አቋቁመን አማራውን ከጥቃት እንከላከላለን” እንዲሉ ገፋፍቷቸዋል። “እሾህን በሾህ” እንደሚባለው፤ ጎሰኝነት የተጠናወተው ወያኔ የሚፈጽምብንን በደል በአማራ ጎሰኝነት እንመክተዋለን እንደማለት ነው። ይህ አመለካከት ግን (እንደኔ አስተሳሰብ) ውስብስብ ለሆነው የሀገራችንና የአማራ ችግር መፍትሔ አይሆንም፤ አይሠራም። የአማራ ፓርቲ የማቋቋሙን ሀሳብ በመቃወም በቅርብ ጊዜ አንዲት አጭር ጽሑፍ (በኢትዮሚዲያ ድህረ- ገጽ በኩል) አስተላልፌ ነበር። የአማራ ፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም ሽር-ጉድ በሚባልበት ባሁኑ ጊዜ ተቃውሞ ማሰማት እንደማይጥም ይሰማኛል። “እንዳልይዘው ፈጀኝ፤እንዳልተወው ልጄ ሆነብኝ” አለች ይባላል የእሳት እናት። ዝም አይባል ነገር የወገንና የሀገር ጉዳይ ነውና (ይመለከተኛል)፤ በፓርቲው ምሥረታ (ሌላው ቢቀር በቲፎዞነት እንኳን) ተባባሪ አይኮን ነገር (በኔ ግምት) መስመር/ፈር የለቀቀ፤ አቅጣጫውን የሳተ አካሄድ ነው። ስለዚህ ባይጥምም የአማራን ፓርቲ ምሥረታ በሚመለከት ይህችን የመጨረሻ ሀሳቤን ላንባቢዎች ለማካፈል ወሰንኩ። በሀገር ግምባታ ታሪካችን ውስጥ ቀንደኛ ተሳታፊ የሆነውንና በሀገሩ (በኢትዮጵያ) ሲመካ የኖረውን የአማራ ሕዝብ በጠባብ የጎሳ ከረጢት ውስጥ መክተት፤ ሲገነባው የኖረውን የሀገር አንድነት በማላላቱና በመበተኑ ተግባር እንዲሳተፍ ማድረግ ነው። ገምብቶ ማፍረስ። የሀገር አንድነትን መጠናከርና መላላት (ከጠናም መፈራረስ) በሚመለከት የፖለቲካ ጅኦግራፊ ምሁራን ሁለት ኃይሎች መኖራቸውን ይናገራሉ። እነዚህ ኃይሎች የስበትና (centripetal forces) የግፊት ኃይሎች (centrifugal forces) ናቸው። የስበት ኃይሎች የተባሉት የአንድን ሀገር ሕዝብ አንድነት የሚያጠናክሩ ልዩ ልዩ ኃይሎች ናቸው። የግፊት ኃይሎች የተባሉት ደግሞ ለአንድ ሀገር ሕዝብ መበታተንና ለሀገር መፍረስ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ናቸው። የስበት ኃይሎች ከግፊት ኃይሎች የበለጠ ብርቱ ከሆኑ የሀገርና የሕዝብ አንድነት እየጠነከረ ይሄዳል። የግፊት ኃይሎች ከስበት ኃይሎች ይልቅ የሚጠነክሩ ከሆኑ ግን የሀገርና የሕዝብ አንድነት እየላላ ይሄድና ሀገር እስከመፍረስ ሕዝብም እስከመበተን ሊደርስ ይችላል ይላሉ። እነዚህ የፖለቲካ ጅኦግራፊ ምሁራን ከዚህ የሚከተሉትን አራት ዋና ዋና የስበት ኃይሎች (centripetal forces) ይሰጡናል፡ 1. የሀገር ፍቅር (nationalism) 2. አጣማሪ/አዋሀጅ ድርጅቶች (unifying institutions): ለምሳሌ፤ ትምህርት ቤቶች፤ የጦር ሠራዊት፤ ከመንግሥት ጋር የተቆራኘ ቤተክርስቲያን (state church)፤ ወ.ዘ.ተ. 3. ቀልጣፋ ድርጅቶችና የመንግሥት አስተዳደር (effective organization

posted by tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s