ዶ/ር መረራ ጉዲና በቀረበባቸው ክስ ላይ ያቀረቡት መቃወሚያ ብይን አልተሰራም

(ግንቦት 25/2009) ዶ/ር መረራ ጉዲና ግንቦት 25/2009 ተቀጥረው የነበረው ባቀረቡት የክስ መቃወሚያ ላይ ብይን ለመስጠት ነበር። መዝገቡን የሚመለከቱት የከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ችሎት ዳኞች የቀረበውን የክስ መቃወሚያ እና የአቃቤ ህግ አስተያየት በመመርመር ላይ እያሉ፤ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዢን (ኢሳት) እና በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦኤምኤን) ላይ የቀረበው ክስ (2ኛው ክስ) አቀራረብ ላይ ችግር በመመልከታቸው ብይኑን ለመስራት እንዳልቻሉ ተናግረዋል። አቃቤ ህግ ባቀረበው 2ኛ ክስ ላይ የወንጀለኛ ህግ አንቀፅ 34(1)ን ማካተቱን የገለፁት ዳኞች፤ አንቀፅ 34(1)ን ለመጥቀስ ክሱ የሚቀርብባቸው ድርጅቶች በመንግስት እውቅና ያገኙ [ህጋዊ ሰውነት ያላቸው] መሆን እንደሚኖርባቸው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዢን (ኢሳት) እና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦኤምኤን) የት ሃገር እንደሚገኙ፣ ህጋዊ እውቅና ያላቸው ስለመሆኑ እና ባጠቃላይ በአሁኑ ሰአት ያሉበት ሁኔታ በክሱ ላይ ባልተገለፀበት ሁኔታ የወንጀለኛ ህግ አንቀፅ 34(1) መጠቀሱ አግባብ እንዳልሆነ ተናግረዋል—ዳኞች። ስለሆነም በወንጀለኛ ስነስረአት ህጉ አንቀፅ 118 እና 119 መሰረት 2ኛውን ክስ አቃቤ ህግ አስተካክሎ እንዲያቀርብ ትእዛዝ ሰጥተዋል። 2ኛው ክስ ተስተካክሎ ከቀረበ በኋላ ዶ/ር መረራ ጉዲና በክሱ ላይ ባቀረቡት መቃወሚያ ላይ ብይኑ እንደሚሰጥ ዳኞች ተናግረዋል።

የዶ/ር መረራ ጠበቃ የሆኑት አቶ ወንድሙ ኢብሳ ከዚህ በፊት በክስ መቃወሚያቸው ላይ ያልተካተተ ነጥብ እንዳላቸው ለችሎት የገለፁ ሲሆን በፅሁፍ ለማስገባት ጠይቀዋል። ዳኞችም አቶ ወንድሙ ከዚህ በፊትም የክስ መቃወሚያ ለ2ኛ ጊዜ እያስተካከሉ ማስገባታቸውን ጠቅሰው ወደፊት መቃወሚያ በሚያስገቡበት ወቅት ሃሳባቸውን በአንድ አጠቃለው በአንድ ጊዜ ማስገባት እንደሚኖርባቸው ገልፀውላቸው የጨመሩትን መቃወሚያ ተቀብለዋቸዋል። አቃቤ ህግ በቀጣይ ቀጠሮ 2ኛ ክስን እንዲያሻሽል፤ እንዲሁም አዲስ በቀረበው የክስ መቃወሚያ ላይ ያለውን አስተያየት እንዲያቀርብ ታዟል። ቀጣይ ቀጠሮ ለሰኔ 13/2009 ተይዟል።

posted tigi flate

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s