የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ በቅርቡ አዲስ አበባ ከተማን በተመለከተ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ በህዝብ ላይ እንዳይጫን ተከታታይ ስራ እንደሚሰራ አስታወቀ

(በሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)

የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ ዛሬ ሀምሌ 02 ቀን 2009 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን በተለይም አገዛዙ በቅርቡ ባዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ሸንጎው ያለውን አቋም ግልፅ ማድረጉን ተከትሎ ጉዳዩ መነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ እንደተጠበቀ ሁኖ ህወሃት/ኢህአዴግ አሁን ባለበት ተክለ ቁመና በስልጣን ላይ የመቆየት እድሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ በመምጣቱ በህዝብ ላይ ጥርጣሬንና አለመተማመንን ለመፍጠር ሲል አዋጁን ለማፅደቅ እንደሚፈልግ ስለሚታመን ይህንን ለሀገር ህልውና አደጋ የሆነ አዋጅ ከመፅደቁ በፊት መላው የለውጥ ፈላጊ ኃይሎች በተለይም የገፈቱ ቀማሽ የሆነው የአዲስ አበባ ህዝብ የዜግነት መብቱን በመጠቀም ይህ አዋጅ እንዳይጫንበት በተደራጀ መልኩ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላችንን መወጣት ይገባናል በማለት ሸንጎው አቋሙን ገልጧል፡፡

በተጨማሪም የስርዓቱ መዳከም በሙስና ላይ የቆመውን የተንዛዛ ቢሮክራሲ እና የስርዓቱ ጠባቂ የሆነውን የደህንነት ሃይል ወጪ ለመሸፈን የሚያስፈልገው ገንዘብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ስለሚሄድ ወጭውን ለመሸፈን መሬት መሸጥ የግድ ስለሚሆንበት ይህንን አዋጅ ሊያፀድቀው እንደሚችል ይታመናል፡፡

ስለሆነም ይህንን አዋጅ መቃዎም የስርዓቱን እድሜ ማሳጠር መሆኑን ተገንዝቦ ሁሉም የለውጥ ሃይል ተከታታይ ትግል ማድረግ እንዳለበት በማሳሰብ የዕለቱን ውይይት አጠናቋል፡፡

posted by tigi flate

Advertisements

አገራዊ ንቅናቄው የአገራችንን የፖለቲካ ችግር የሚመጥን መፍትሄ ለመፈለግ ጠቃሚ ነው – ፕ/ብርሃኑ ነጋ።የኢትዮጵያ ጉዳይ ከልብ ያሳስበኛል – አቶ ሌንጮ ለታ

ጉዳያችን ሪፖርታዥ 

ሰኔ 10፣2009 ዓም 
==============
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ቅዳሜ ሰኔ 10፣2009 ዓም በኦስሎ፣ኖርዌይ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ጉባኤ ሁለት ከፍተኛ ኃላፊዎችን ጋብዞ ጉባኤ አካሂዶ ነበር።ይሄው በኦስሎ የቀይ መስቀል ዋና መስርያ ቤት አዳራሽ የተካሄደው ጉባኤ ላይ ከ200 ሰው በላይ የታደመበት ነበር።በጉባኤው ላይ የተጋበዙት የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ ነበሩ።
የዝግጅቱን መክፈቻ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሰብሳቢ አቶ ይበልጣል ጋሹ በንግግር ከተከፈተ በኃላ  የመጀመርያ ተናጋሪ የነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ ነበሩ።
አቶ ሌንጮ “ተቀምጨ እንዳልናገር አጭር ነኝ” በሚል ቀልድ አዘል ንግግር ተሰብሳቢውን ፈገግ ካስደረጉ በኃላ የመተባበር አስፈላጊነት ላይ አፅኖት ሰጥተው ተናግረዋል።በመቀጠልም ” በ1966 ዓም ንጉሱ ከስልጣን ሲወርዱ እርሳቸው ይወረዱ እንጂ መጪው ጊዜ የተሻለ እንደሆነ በጣም ተስፋ አድርገን ነበር። ካሉ በኃላ ሆኖም ግን ደርግ መጣ ብለዋል።
አቶ ሌንጮ አያይዘውም ደርግ ሲመጣ ከደርግ የባሰ ሊመጣ አይችልም ብለን ስናስብ የባሰ መጣ።ሆኖም ግን ማሰብ የሚገባን ደርግ ሲገድል በቀጥታ `የፍየል ወጠጤ` እያለ ነበር።ስለሆነም የገደለውን ቁጥር መገመት ይቻላል።የአሁኖቹ ግን በስውር ነው።በስውር ያሰሩት፣የገደሉት እና የሰወሩት ሕዝብ ቁጥር አሁን መናገር አንችልም። ምክንያቱም ሁሉን በድብቅ ነው የሚያደርጉት” ካሉ በኃላ ስለመጭዋ ኢትዮጵያ ማሰብ እንደሚገባ እና እርሳችውንም የሚያሳስባቸው ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል።ለዚህም የሱማሌ፣ደቡብ ሱዳን ጉዳይ እያነሱ በሰፊው ለማብራራት ሞክረዋል። አቶ ሌንጮ ኢትዮጵያ እስካሁን እንደ ሀገር እንድትቆይ ካደረጋት ጉዳይ ውስጥ ቀዳሚው ያሉት የህዝቡ ጨዋነት መሆኑን ሲናገሩ እንዲህ አሉ – “ኢትዮጵያን እስካሁን ጠብቆ ያኖራት የህዝቧ ጨዋነት እንጂ የመሪዎቿ ብቃት አይደልም” ነበር ያሉት።በመቀጠልም አቶ ሌንጮ አሁን ያለው መንግስትም ሆነ ተቃዋሚዎች እንዲሁም ሕዝቡም ትኩረት የማይሰጠው ጉዳይ የህዝብ ቁጥር መጨመር እና እርሱን ተያይዞ የሚመጣው የአካባቢ ብክለት፣ የማህበራዊ ኑሮ መዳከም እና የህዝብ ኑሮ ማሽቆልቆል ዋነኞቹ ችግሮች ውስጥ እንደሚካተት አብራርተዋል።
ከጉባኤው ተሳታፊዎች በከፊል 
በመቀጠል ንግግር ያደርጉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ነበሩ።ፕሮፌሰሩ ንግግራቸውን የጀመሩት ሶስት ነገሮችን በቅድምያ ካላወቅን ነገን ለማወቅ ያስቸግረናል በሚል መነሻ ነጥቦች ነበር። እነርሱም : –
1/ አሁን የገጠመን ባላንጣ (የወያኔ ስርዓት) ብሔራዊ ጥቅም የሚባል ነገር የማያውቅ፣ ስርዓቱ ስልጣኑን የማያስጠብቅበት ሁኔታ ከተፈጠረ ሁሉ ነገር እንዲወድም የሚሰራ ስርዓት መሆኑን፣
2/ የሀገራችን ፖለቲካ  በብዙ ምክንያቶች ውስብስብ ችግሮች ውስጥ ያለ መሆኑ እና
3/ የህዝባችን የሞራል ደረጃ እየወረደ መምጣቱ የሚሉት መሆናቸውን አብራርተዋል።
ከላይ ለተጠቀሱት ችግሮች የአገር አድን ንቅናቄው መፍትሄ መሆኑን ለማመላከት ንቅናቄው እንዴት ችግሮች ይፈታሉ ብሎ እንደሚሰራ አብራርተዋል።
ለመሆኑ የአገር አድን ንቅናቄው ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮች የሚሰጣቸው ስልታዊ ምንድን ናቸው? በሚል በጥያቄ ንግግራቸውን የቀጠሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ንቅናቄው በሚከተሉት ስልታዊ መንገድ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ችግር የመፍታት አቅም እንዳለው አብራርተዋል።
1/ በሚደረጉ የንቅናቄው ውይይቶች መጥራት የሚጎዳላቸው የሃጋራችን የፖለቲካ ችግሮች እንዲጠሩ በማድረግ፣
2/ በውይይቱ ሂደት መስማማት።በሂደቱ ላይ ከተስማማን በውጤቱ ላይ መስማማት መጨረሻ የሚመጣ ጉዳይ ነው። አሁን የውይይቱ ሂደት ዲሞክራሲያዊ መሆኑ ላይ መስማማት እና ውጤቱን ደግሞ ሕዝብ እንዲወስን መተው ነው።
በዲሞክራሲ ሂደት ላይ ከተስማማን በሌሎች ጉዳዮች ላይ ልዩነት አይኖርም ማለት አይደለም።ለምሳሌ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ እና በሌሎች በርካታ ጉዳዮች ላይ የግድ ላንስማማ እንችላለን። ሆኖም  ግን የቀሪ ልዩነታችን መፍቻ ዲሞክራሲያዊ አፈታትን ስለመረጥን ብዥታ አይኖርም  ማለት ነው።
ለጨረታ የቀረበው እና ከበርገን ከተማ የመጡ የጉባኤ ታዳሚዎች በ13 ሺህ የኖርዌይ ክሮነር የወሰዱት ስዕል 
ከእዚህ በተጨማሪ የጋራ ንቅናቄው ምን እያደረገ ነው? ለሚሉ ጥያቄዎች  ፕሮፌሰር ብርሃኑ ሲያስረዱ አገራዊ ንቅናቄው –
ሀ) ዋና ጉዳዮች ላይ ማትኮር መቻሉ ፣
ለ) ሌሎች ድርጅቶችን እያሰባሰበ ወደ አንድ ነጥብ ማምጣት ላይ እየሰራ መሆኑ፣
ሐ) ድርጅቶችን ማቀፉ የትግሉን መልክአ ምድራዊ ሽፋን ማስፋቱ እና አገራዊ ቅርፅ መያዙ፣ የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከላይ የተጠቀሱትን ሶስት የንቅናቄው ተግባራት በምሳሌ ካስረዱ በኃላ የወያኔን ውድቀት ለማፋጠን የሚያስፈልጉ ሶስት አበይት ጉዳዮችን ጠቅሰዋል። እነርሱም –
1ኛ) የጠራ መንገድ በትግሉ ሂደት መያዝ፣
2ኛ) መሬት የያዘ ትግል ማካሄድ እና
3ኛ) ወያኔ ያዳከመብንን ሞራላዊ ልዕልና መልሰን መገንባት እና ማምጣት የሚሉ ናቸው።
ከላይ የተጠቀሱት ሶስት አበይት ጉዳዮች ውስጥ የሞራል ልዕልናችንን መልሰን መገንባት የእረጅም ጊዜ ስራችን መሆን ያለበት ሲሆን ቀሪዎቹ ሁለቱ ግን በፍጥነት የሚሰሩ እና አሁን እያከናወናቸው ያሉ ስራዎች መሆናቸውን አውስተዋል።
በእዚሁ ጉባኤ ላይ ከነበሩት የፕሮፌሰር ብርሃኑ እና አቶ ሌንጮ ንግግሮች በተጨማሪ የጥያቄ እና መልስ መርሃ ግብር ነበር።በጥያቄ ከተነሱት ውስጥ አሁን ያለነው ወጣቶች በወያኔ ዘመን ያደግን ስለሆነ ስለ ጎጥ እየሰማን ስላደግን ኢትዮጵያዊ ስሜታችን ሳይጎዳ ለመጠበቅ ምን ማድረግ ´አለብን? የሚል የነበረ ሲሆን አቶ ሌንጮ ሲመልሱ –
“በኢትዮጵያ ታሪክ ማንም ንጉስ ከእዚህ ብሔር የመጣሁ ነኝ ብሎ አያውቅም።በኢትዮጵያም  ጨቋኝ  የሚባል ብሔር የለም።የጨቆነ ከአንድ ብሔር የወጣ ቡድን ቢሆን ይህ ቡድን ብሄሩን ይወክላል ማለት አለመሆኑ ሊሰመርበት ይገባል።” ብለዋል።በመጨረሻም አቶ ሌንጮ ” እኔ ኦሮሞም ኢትዮጵያዊም መሆን እፈልጋለሁ።” ብለዋል። በማስከተልም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ኢትዮጵያዊነት ከኢትዮጵያዊው ወጣት ትውልድ ውስጥ ወጥቷል የሚል ፈፅሞ ግምት እንደሌላቸው እና ለእዚህም በርካታ  ማስረጃዎች መኖራቸውን አብነት እየጠቀሱ አስረድተዋል።
በመጨረሻም በዋናነት የፕሮፌሰር ብርሃኑን እና አቶ ሌንጮ ለታን ንግግር፣ከህዝብ የተነሱ ጥያቄዎች መመለስ፣የገቢ ማሰባሰቢያ ጨረታ የተካሄደበት ጉባኤ ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ እንግዶችን በክብር በመሸኘት ተፈፅሟል።ባጠቃላይ በእዚህ ጉባኤ ላይ የታየው ከፍተኛ ዲስፕሊን፣የሰዓት አጠቃቀም እና የመድረክ መስተንግዶ ሁሉ የተዋጣለት እና ደረጃውን የጠበቀ መሆን የጉባኤውን ተሳታፊዎችንም ሆነ እንግዶችን ያስደሰተ ተግባር ሆኖ አምሽቷል።

ጉዳያችን GUDAYACHN

posted tigi flate

አዲስ ነገር የለም ትግራይ የጉግማንጉጎች ምድር ከሆነ ሰነበተ – መስቀሉ አየለ

 

ከሶስት አመት በፊት በመዋዕለ ህማማት ወደ መቀሌ የተጓዘ አንድ በቅርብ የማውቀው ሰው በድፍን መቀሌ የጾም ምግብ የሚባል ነገር አጥቶ ምን ያህል እንደተቸገረ ገልጾልኝ ነበር።አጠር ባለ አማርኛ ሃጢያት ቤተመንግስቱን ባነጸባት የዘመናችን ሰዶምና ገሞራ ላስቬጋስ እያለሁ ያን ያህል በጾም ምግብ ማጣት አልተፈተንኩም። ቢያንስ ለቬጋን የሚባል የቅንጡዎች የአመጋገብ ዘይቤ አላቸውና በዛ በኩል እሸጎጥ ነበር ብሎኛል። ከሁሉ የገረመው የጾም ምግብ ማጣቱ አይደለም። ሰዎቹ በምሳ ሰዓት ከመሃል አገር እየተጫነ የሚመጣ ሰንጋ በሬ ቁርጥ ለመብላት በየሆቴል ቤቱ ተክተልትለው የሚያሳዩት መንሰፍሰፍ ግብር ሊበሉ በነጋሪት አዋጅ የተጠሩ እንጅ በገንዘባቸው ገዝተው የሚጠቀሙ አይመስሉም ነበር፤ እንደታዛቢው አገላለጥ።Image result for mekelle city photo
ሌላው አስገራሚ ነገር መቀሌ ውስጥ ያሉ ቤተክርስቲያኖች እንደ አውሮፓ ቤተመደሶች መጋዘንና ሲኒማ ቤት ለመሆን የቀራቸው የሃያና ቢበዛ ሰላሳ አመት ጉዳይ እንደሆነ ገብቶኝ እርሜን አውጥቸ ነው የመጣሁት ብሏል።ምክንያቱም እዚያ በቆየባቸው ሳምንታት ማታ ማታ ለመሳለም ጎራ ባለባቸ ቤተክርስቲያናት ሁሉ አውደምህረቶቹ በሰው ድርቅ ተመተው እንዳያቸውና የቀሩትም ተሳላሚዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ እድሜያቸው በአመዛኙ ከስልሳ በላይ የሆኑት አረጋውያን እንደሆኑ፤ እነሱ ደግሞ ከጥቂት አስርተ አመታት ቦሃላ ሲያልቁ ወይንም አልጋ መያዝ ሲጀምሩ አጸዶቹ ዳዋ እንደሚበቅልባቸው ለማወቅ ነቢዩ ኤርሚያንስ መሆን አይጠቅም ማለቱ ነው።
ትግሬዎች ዛሬ እግዚአብሔርም ሆነ የሞራል ህግ አያስፈልጋቸውም። የነሱ የቃልኪዳን ዶሴ የደደቢቱ ማኔፈስቶ ነው። እንደፈለጉ እንዲዘርፉም እንዲገድሉም ከንብረት ባሻገር በነፍስና በስጋ ላይ ያልተገደበ ስልጣን የሰጣቸው ህወሃት መሆኑ ብቻ አደለም፤ አንድ ሰው ማንነቱን የምታውቀው በተጣላኸው ግዜ ነው እንዲሉ ለአምላኩ ያለውን ትህትና እና የአምልኮ ደረጃም የሚታወቀው እንዲሁ በችጋር ወቅት ሳይሆን በጥጋቡ ወራት ነው። ይኽ ሩብ ምእተ አመት ደግሞ ያሳየው ነገር ቢኖር ግን እኒህ መናፍሰት ነገሮች የወንጌልን የሞራል ህግ ቀርቶ በጣም ቀላል የሚባል ሰብአዊነትን ለመሸከም የማይቻላቸው የነተቡ መጽጉዎች መሆናቸውን ነው።የስርዓቱ ዘዋሪዎች እኮ እንደ ቁቤ ትውልድ በሽተኞች ሃይማኖቱን “ሃላፊነቱ የተወሰነ የነፍጠኛው የግል ኩባንያ” አድርገው እንደፈረጁት በየቤተ ሃይማኖቱ የሚሰሩትን ግፍ አጥርቶ መመልከት ነው:: ዛሬ በትግራይ ምድር ሃይማኖት ተረት ነው የምንለውም ለዚሁ ነው።የዘንዶውም እራስ ቢንሆ ባንድ ወቅት “እኔ የማምነው በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ነው” ብሎ ቃለ መጠይቅ መስጠቱን እናስታውሳለን። በርግጥም ሉሲፈራውያን (ምዕራባወያን) ሃያ አምስት አመት ሙሉ ክንዳቸውን የገተሩላቸው ዝም ብለው አይደለም። መድሃኒዓለም እንደተናገረ ሰይጣን ሰይጣንን አያወጣውም፤ አይኑን ገልጦ ላየ አፈሩን ፍም እሳት ያደረገላቸው መሳጢ ተኩላው አባ ጳውሎስ ቢሆኑ ከስብሃት ነጋና ከሳሞራ የማያንሱ ጉግማንጉግ እንደነበሩ ኑሯቸውም ብቻ ሳይሆን አሟሟታቸውም ያሳየው ነገር ነበር።
ዛሬም ቢሆን ደግሞ መቀሌ ያለ የአባይ ወልዱ ዘለፈቶ ቀርቶ አዲስ አበባ መንበረ ጵጵስናው ላይ የወጡት ፓትሪያሪክ በእግዚአብሔር ለማመናቸው ማረጋገጫ የለኝም። ቢያንስ ያለትውፊቱና ያለቀኖናው እስኪፈሰክ አላስችላቸው ብሎ በአብይ ጾሙ ወቅት ሱብኤውን አቃለው ከበሮ መትተው የተሾሙ ቀን በቅቶኛል። ዛሬ አንድ አይጠ መጎጥ አዲግራት ውስጥ ሂጃብ እንጅ ነጠላ መልበስ አይቻልም ብሎ ጅሃድ ሲያውጅ እንዲሁ ከባዶ ተነስቶ አይደለም። እድሜ ቢሰጣቸው ደግሞ ከሰማይ በታች የማይሞክሩት ክፋትና ግፍ እንደማይኖር እርግጠኛ ነኝ። ነገ ጀንበር ስትወጣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቋንቋ ጥናት ኢንስቲትዩት የነዚህ ጉዶች ሴራ ብቻ የያዘ እራሱን የቻለ “ሴራ-ፒዲያ ዘብሄረ ትግራይ ” አዘጋጅቶ ለዓለም እንደሚያበረክት ተስፋ ማድረግ ሞኝነት አይደለም።ቦ ግዜ ለኩሉ ነውና።

 

posted tigi flate

“የሰኔ አንድ ሰማዕታት አደራ በትግላችን እውን ይሆናል!!!” – ከአርበኞች ግንቦት 7 የተሰጠ መግለጫ

ሰኔ አንድ በኢትዮጵያ የሰማዕታት ታሪክ ልዩ ስፍራ የሚሰጠው ነው።

ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓም እንደ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም ሁሉ መብታቸውን የጠየቁ፣ በባርነት፣ በጭቆና እና በዘር መድሎ አንኖርም ያሉ ኢትዮጵያውያን በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ ደማቸው እንደ ጎርፍ እንዲፈስ የተደረገበት ዕለት ነው። በየካቲት 12 እና በሰኔ 1 መካከል ልዩነት ቢኖር፣ የገዳዮች ማንነት ነው። የካቲት 12 ቀን 2009 ዓም የአገራቸውን በጣሊያን መወረር የተቃወሙ የቁርጥ ቀን ልጆች በፈጸሙት ታሪካዊ የአልገዛም ባይነት ተጋድሎ ፣በአረመኔው ግራዚያኒ ትእዛዝ ተጨፍጭፈዋል። ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓም ደግሞ የጭቆናን ቀንበር ሰብረው ለመውጣት ትግል ያደረጉ፣ በአገራቸው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ተገንብቶ ማየት የሚሹ፣ በግንቦት 7 1997 ዓም ምርጫ ወላጆቻቸው የሰጡት ድምጽ እንዲከበርላቸው የጠየቁ እንቦቀቅላዎች፣ አገር በቀል በሆነው የግራዚያኒ የመንፈስ ልጅ መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ፣ ከ40 በላይ ወጣቶች በአደባባይ የተጨፈጨፉበት፣ ብዙዎች ለአካል ጉዳትና ለእስር የተዳረጉበት ነው

 

እነዚህ ሰማዕታት የህይወትና የአካል መስዋትነት ሲከፍሉ በህይወት ላለነው ታላቅ አደራ አስቀምጠውልን ማለፋቸውን ምንጊዜውም ልብ ልንል ይገባል። ሰማዕታቱ “ኢትዮጵያችን ዘረኝነትን፣ ጭቆናንና አፈናን አሸንፋ፣ በዲሞክራሲ፣ በፍትህና በነጻነት የምትመራ አገር እስከምትሆን ድረስ ትግላችሁን ቀጥሎ፣ ያን ጊዜ የእኛ ደም ከንቱ ሆኖ አየቀርም” የሚል አደራ አስቀምጠውልን አልፈዋል። ይህ ታሪካዊ አደራ ዛሬ ዛሬ እየተደረገ ላለው የሞት ሸረት ትግል የማንቂያ ደወል ሆኖ እያገለገለ ነው። ዛሬ በመላ አገራችን እየተቀጣጠለ የመጣው የነጻነት ትግል ለእነዚህ ሰማዕታት ትልቅ ርካታን የሚሰጥ ነው። በእያንዳንዱ ቀን በምናደረገው ትግል ውስጥ ሰማዕታቱ አብረው ይዘከራሉ።

የሰኔ 1 ሰማዕታትን አደራ ጠብቀው የተጓዙ በርካታ ወጣቶች የህይወት መስዋትነት ከፍለዋል፣ እየከፈሉም ይገኛሉ። ከሰኔ 1 ቀን 1997 ዓም ወዲህ በመላ አገሪቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ለነጻነታቸው የህይወት መስዋትነት ከፍለዋል። በአወዳይ፣ አምቦ፣ ሃሮማያ፣ አርሲ፣ ጎንደር፣ በጎጃም ባህርዳር እና በሌሎች በርካታ የአገሪቱ ክፍሎች በተካሄዱ የነጻነት ትግሎች በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ2 ሺ ያላነሱ ሰዎች በአረመኔው አገዛዝ በግፍ ተገድለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በየእስር ቤቱ እየማቀቁ የሚገኙትንማ ቤት ይቁጠረው። የሰኔ ሰማዕታት የለኮሱት ትግል ፣ አደራቸውን በተቀበሉ ወጣቶች እየጎመራ ሲሄድ ስንመለከት ፣ የሰማዕታቱ ደም ከንቱ አለመሆኑን ብቻ ሳይሆን፣ አደራውን በተቀበሉ ወጣቶችም እንድንኮራ አድርጎናል።

ትግል እንደ ዱላ ቅብብሎሽ አንዱ ለሌላው እያስረከበው የሚሄድ ነገር ነው። አንድን ትግል አንድ ግለሰብ ወይም የአንድ ትውልድ አባላት ብቻ ከዳር ያደርሱታል ብሎ ማመን ስህተት ነው። የሰኔ ሰማዓታቱ የትግሉ ሻማ ለዚህ ትውልድ አስረክበዋል፣ ይህ ትውልድ ደግሞ ሻማው እንዳይጠፋ ብቻ ሳይሆን ይበልጥ እንዲቀጣጠል አድርጎ ለሚመጣው ትውልድ ያስረክባል፣ የሚመጣው ትውልድም ለቀጣዩ ትውልድ እያስረከበ ይሄዳል። የህወሃትን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ማስወገድ ከትግሉ ግቦች ውስጥ አንዱ ቢሆንም፣ በዚህ አገዛዝ ቦታ ላይ የሚተካውን ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መፍጠር ፣ የተፈጠረው ስርዓት በጠንካራ አለት ላይ እንዲቀመጥና ቁመናውንና ጥንካሬውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንዲሄድ ማድረግ የትውልዶች ስራ ነው። የዚህ ትውልድ የቤት ስራ የህወሃትን አገዛዝ አስወግዶ በምትኩ የዲሞክራሲያዊ ስርዓትን መሰረት መጣል ነው ብሎ ድርጅታችን አርበኞች ግንቦት7 በጽኑ ያምናል። ለዚህ ስርዓት መመስረትም አስፈላጊውን መስዋትነት እየከፈለ ይገኛል፤ ይህ ስርዓት እውን እስኪሆንም መከፈል ያለበትን መስዋትነት ሁሉ ይከፍላል። አርበኞች ግንቦት7 የሰኔ ሰማዕታት ያስረከቡትን አደራ ምንጊዜም ጠብቆ አደራቸውን ዳር ለማድረስ የሚተጋ ድርጅት ነው። ሰኔ 1 በአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮች ዘንድ ልዩ ስፍራ የሚይዝ ቀን እንደመሆኑ፣ በዚህ ቀን ሁሉም ታጋይ የትግሉን ቃል ኪዳን ያድሳል። ሰማዕታቱንም ይዘክራል።

የሰኔ ሰማዕታት አደራውን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ያስረከቡት በመሆኑ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዚህ አደራ ዙሪያ ታቅፎ ትግሉን ማካሄድ አለበት። የህወሃትን ዘረኛና ጨፍጫፊ አገዛዝ ለማስወገድ ብቻ ሳይሆን፣ በተነቀለው ጉቶ ላይ የዲሞክራሲያንና የነጻነትን ችግኝ ለመትከልና ለማሳደግ የመላው ኢትዮጵያዊን ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ሁላችንም የሰኔ ሰማዕታትን አደራ እያስታወስን እጅ ለእጅ ተያይዘን ትግላችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ዛሬም አገራዊ ጥሪ እናቀርባለን።

ክብር ለሰኔ አንድ ሰማዕታት! ድል ለኢትዮጵያ ነጻነት ወዳዶች ሁሉ!

posted tigi flate

አለም የሚመራው በለየላቸው ማጅራት መቾች ነው | መስቀሉ አየለ

ጆርጅ ቡሽና ቶኒ ብሌየር ኢራቅ ውስጥ አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሰው ገድለዋል።አካለ ጎደሎ ሆኖ የቀረውና የተፈናቀለውን ሰው ሲጨመርበት ደግሞ ስሌቱን ሆድ አይችለውም። ይኽ አሃዝ የጸጥታው ምክር ቤት እራሱ በሾማቸው አጣሪ ኮሚሽን የተረጋገጠ ቢሆንም በመጨረሻ ሰአት የምርመራው ውጤት ግን ለሚቀጥሉት ስልሳ አመታት ለህዝብ እንዳይገለጥ ወስነው በደንበኛ የብረት ካዝና ቆለፉበት። ያን ግዜ ተጠያቂዎቹ በህይወት ስለማይኖሩ እንዲሁ ወሬ ዘርተው ጋዜጣ ይሰሩበታል ነው ማለት ነው።

ሳውዲ አረቢያ የሚባለው አገር የአንድ ሰው ንብረት ነው። አገሩም የተጠራው የዛሬ መቶ አመት ገደማ በነበረው የዘላኖቹ አለቃ ስም ነው፤ አልሳውድ ይባል ነበር፤ የንጉሳዊ ቤተሰብ እየተባለ ዛሬ ድረስ የዘር ግንድ የሚመዘዘው ከዚህ ሰው ነው። የርሱ የልጅ ልጆች ደግሞ አይሲስ የሚባል አደገኛ ቫይረስ ፈጥረው ይኸው አለሙን መከራ ያበሉታል።ነገሩ እንዲህ ነው። በዚሁ በሳውዲ አረቢያ ውስጥ በአስገድዶ መድፈር፣ በድራግ ሽያጭ፣ በግድያ፣ በኦርጋን ትራፊኪንግና በሌሎች ከባባድ ወንጀሎች ተከሰው የሞት ፍርዳቸውን ይጠብቁ የተነበሩትን ወንጀለኞች በሚስጥር ከእስር ቤት አውጥተው አይሲስን ሲፈጥሩ እና መካከለኛውን ምስራቅ በእሳት ሲያነዱት የምዕራባውያን ቡራኬ ስላለበት ነው።

ዛሬ ሳውዲ አረቢያ የሚባል የፍየል ጠባቆዎች ስብስብ የመንን ከደቡብ አሜአሪካና ከምስራቅ አውሮፓ የጦር አውሮፕላን የሚያበሩ መርሰነሪ ገዝቶ ያስደበድባል፤ዛሬ የመን የሰው ደም ለጠማው የዘመኑ ኢሊምናቴና መሶናይት የተሰጠች የመስዋእት ጠቦት ሆና እለት እለት እንደመና የእሳት ድኝ ከሰማይ ይወርድላታል። በውስጥ በተደረገ ስምምነት ማንኛውም አይነት የምእራቡ የዜና ትቋም ስለየመን አዳርና ውሎ ትንፍሽ እንዳይል ተደርጎዋል።
የጸጥታው ምክር ቤትም ሆነ የተባበሩት መንግስታትም ቢሆኑ ስለጉዳዩ አጀንዳ ይዘው ለመወያየት እንኩዋን ፈቃደኛ አይደሉም።

ዩክሬንን ጨምሮ የምስራቅ አውሮፓ አገሮች ሁሉ ከአሜሪካኖቹ በላይ አሜሪካዊ መሆን በሚፈልጉ ባንዳ መሪዎች እንዲሞሉ ተደርጎዋል።አንደበተ ቁጥቧን ፕሬዝደንት ዲልማ ሮውሴፍን ያህል ቅን መሪ አንስተው ነፍሱን ለአሜሪካ የሸጠውን ማይክል ተመርን ያነገሱት ብራዚላውያን ዛሬ አይናቸው ሲገለጥ ውረድ ማለት ጀምረዋል።እርሱ ስልጣን ላይ በወጣ ማግስት ድፍን ብራዝሊን ለአሜሪካ በቆዳ ምላሽ መቸብቸብ ሲጀምር ብራዚላውያን ግን ዘግይተውም ቢሆን አይናቸውን በመግለጣቸው አገሪቱ ሌላ ዙር ትርምስ ውስጥ መገባቷ ነው መዘዙ።

እንዲህ ካናቱ የገማ አለማቀፍ ተቋም እረጋ ብለው ሲያዩት ነገሩ ሁሉ ይበልጥ ውስጡን ለቄስ ነው። በነፍስ የሚስያቡ ሰዎች ገብተው የሚወጡበት አይደለም።ዛሬ እነ ቢልጌት ደግሞ የአለምን የህዝብ ቁጥር ለመቀነስ ብዙ ገንዘብ የፈሰሰበት ትላልቅ ፕሮጀክት ይዘው በር ላይ እየጠበቁ ነው። ለዚህ ፖሊሲ ተፈጻሚነት ደግሞ ቴድሮስ አድሃኖም የመሳሰሉ የፍናፍንት ስነልቦና ያለው ደርቲ ሰው ያስፈልጋል። ሁለት አመት ሙሉ አሰልጣኝ ቀጥረው ሲያዘጋጁት መክረማቸው ለዚሁ ነበር።

ነጮችን የቢግባንግ ባሌቤት ያደረጋቸው የለም፤ ይኽች ምድር የሁሉም ናት ባለቤት የላትም። ሰው ሆነን የተፈጠርን እኛ ይሕችን ፕላኔት ከሁሉም ተጋርተን ለመኖር የማንም በጎ ፈቃድ አያስፈልገንም። ቆዳውን ቀይሮና ስሙን አሳምሮ ነገር ግን የሂትለሩን የዘር ፍጅት ሚንስቴር ጆሴፍ ጊዮብልስን ተክቶ የመጣው ቢል ጌትና ኩባንያው በዛሬው እለት ሁለት እግሩን በአለማቀፉ የጤና ድርጅት ላይ ተክሏል። ከዚህ ሴራ ጀርባ ያለውን እውነት ደግሞ ያየነው እኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ በመሆናችን ብቻችንን ጮኸናል። በተጻራሪው ፤ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱን የመረጠው አለም ግን ከጩኸታችን ጀርባ ያነበረውን ቁጭት አንድ ቀን በዓይኑ ያየዋል።
ባለፈው ሰሞን የራሽያው ፕሬዝዳንት ፑቲን በአደባባይ ወጥቶ እንዳጋለጠው በኮንጎ ውስጥ ተበትኖ ድፍን ምእራብ አፍሪካ ከአንድ አመት ለበለጠ ግዜ ሲበላው ከከረመው የኢቮላ ሰደድ እሳት ጀርባ እጁ ያለበት ዋነኛው ሰው ቢልጌት መሆኑን እንዲሁም የአለም የጤና ድርጅት አፋጣኝ እርምጃ እንዳይወሰድና የሰዎችን ህይወት መታደግ እንዳይቻል ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ለበርካታ ወራት ድምጹን ያጠፋው በዚህ በጡት አባቶቹ በነቢልጌት ተጽእኖ እንደ ነበረ እንቅጩን አውጥቶ ለአለም ህዝብ አሳይቷል።

በዚሁ አጋጣሚ ግን ግልጽ መሆን ያለበት አንዱ ቁልፍ ጉዳይ በግዜው ድፍን አለም የበረራ መስመሩን በሙሉ ፤ የንግድ እንዲሁም የቱሪዝም አገልግሎትን አቋርጦ፣በሩን በምዕራብ አፍሪካ ላይ ሲዘጋ፤እነ ሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫን እስከ መሰሰረዝ ሲደርሱ የወያኔው ሚንስቴር ግን ቁጭ ብሎ ሲያሰላ የነበረው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚገኘውን ትርፍ ሲሆን ይባስ ብሎ በመቶ የሚቆጠሩ ፤ዕእርዳታ ሰጭ ታስክ ፎርስዕ ወደ ላይቤሪያ ካዘመተበት ባዶ እብሪት ጀርባ ያለውን እውነት መጎርጎሩ አይከፋም።

posted tigi flate

አርበኞች ግንቦት 7 ቴድሮስ አድሃኖምን የሚያጋልጥ መረጃ ለቀቀ

የዓለም ጤና ጥበቃ ዳይሬክተርነት በህዝባችን ላይ የተፈጸመውን ወንጀል መሸፈኛ ሊሆን አይችልም!

አርበኞች ግንቦት 7

ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ድርጅትና እንደ መንግሥት በአገራችን ውስጥ እንዲተገበሩ በወጡ አፋኝ ፖሊሲዎችና በህዝባችን ላይ በተወሰዱ ፋሽስታዊ እርምጃዎች ሁሉ ወሳኝ ሚና ከነበራቸው ጥቂት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ቴዎድሮስ አድሃኖም አንዱ ነው።

ይህ ወንጀለኛ ግለሰብ የአምባገነኖች ስብስብ በሆነው የአፍሪካ ህብረት ሙሉ ድጋፍ አግኝቶ ለአለም ጤና ጥበቃ ዳይሬክተርነት እጩ ሆኖ ሲወጣ እንደ ትልቅ ገድል የተቆጠረለት የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ሆኖ ባገለገለባቸው አመታት አስመዝግቧል የተባለው የጤና መሻሻልና በውጪ ጉዳይ ሚንስትርነት አበርክቷል የተባሉት አስተዋጾዎች ናቸው።
ምዕራባዊያን ለጋሾች ለታዳጊ አገራት የጤና አገልግሎት በየአመቱ የሚሰጡትን ገንዘብ የሚመድበውና የመደበውን ገንዘብ ሥራ ላይ መዋሉን የመከታተል ሃላፊነት የተጣለበት ግሎባል ፈንድ የተባለው አለም አቀፍ ተቋም ቴዎድሮስ አድሃኖም የአገራችንን ጤና ጥበቃ ሚንስትር መሥሪያ ቤት በመራበት ወቅት ለነፍስ አድን ዕርዳታ ከሰጠው አንድ ቢሊዮን ሶስት መቶ ስድስ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ውስጥ ከፍተኛውን ገንዘብ እንዴት አድርጎ እንዳባከነና ለፖለቲካ ፍጆታ እንደዋለ በኦዲተሮቹ አስመርምሮ ይፋ አድርጓል።

ሜይ 14 ቀን 2012 ዓም ይፋ የሆነው ይህ የምርመራ ሪፖርት እንደሚያትተው በፈረንጆች አቆጣጠር 2009 እና 2010 ለአገራችን የተሰጠው የነፍስ አድን እርዳታ ገንዘብ ዋና አላማው በደማቸው ውስጥ የኤች አይቪ ቫይረስ የተገኘ ፤ በሳምባ ህመምና በወባ የተጠቁ ሰዎችን ህይወት ከሞት ለማትረፍ የታሰበና የገንዘብ ድልድሉም የሚከተለውን የሚመስል ነበር።

• ለሳምባና ወባ ህክምና 404 ሚሊዮን ዶላር
• ለኤች አይቪ 879 ሚሊዮን ዶላር
• የኤች አይቪ ተሸካሚዎች ኔት ዎርክ 9 ሚሊዮን ዶላር
• በኤች አይቪ በሽታ ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት መርጃ 14 ሚሊዮን ዶላር በድምሩ አንድ ነጥብ ሶስት መቶ ስድስት ሚሊዮን ዶላር

ከዜጎች ህይወትና ደህንነት በላይ የፖለቲካ ሥልጣን ዕድሜው እጅግ የሚያሳስበው የህወሃቱ ቴዎድሮስ አድሃኖም ግን ለነፍሰ አድን ከተሰጠው ከዚህ መጠነ ሰፊ ገንዘብ ውስጥ 165,393,027 /አንድ መቶ ስልሳ አምስት ሚሊዮን ሶስተ መቶ ዘጠና ሶስት ሺ ሃያ ሰባት/ የአሜሪካን ዶላር የለተቋሙ እውቅናና ፈቃድ 1309 ጣቢያዎችን አስገንብቻለሁ በማለት ገንዘቡን እንዳባከነ የግሎባል ፈንድ ኦዲተሮች ባደረጉት ምርመራ ደርሰውበታል። ከዚህም በተጨማሪ 57, 851, 941 ዶላር የት እንደገባ ማረጋገጫ አልተገኘለትም ።

የት እንደገባ ማረጋገጫ አልተገኘለትም የተባለውን ሃምሳ ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሃምሳ አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ አርባ አንድ ዶላር ጉዳይ የሚያውቀው ቴዎድሮስ አድሃኖም ብቻ ሊሆን እንደሚችል ገምተን ወደ ጎን እንተወውና በእርዳታ ገንዘቡ ተገንብተዋል ስለተባሉት ጤና ጣቢያዎች ሪፖርቱ የሚያወራውን እንመልከት ። በግሎባል ፈንድ የኦዲት ሪፖርት መሠረት ቴዎድሮስ አድሃኖም 1309 ጤና ጣቢያዎችን በተቋሙ ገንዘብ ገንብተናል ብሏል።
ከነዚህ 1309 ጤና ጣቢያዎች ውስጥ የግሎባል ፈንድ ኦዲተሮች 77ቱን እንዲጎበኝ ተደርጎ፤

• 71%ቱ ለጤና ጣቢያ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች ውስጥ አንዱ የሆነውን የውሃ አገልግሎት በጭራሽ እንደሌለው፤
• 32%ቱ ሽንት ቤት የሚባል ነገር እንዳልተሠራለት፤
• 53%ቱ ገና ተሠርተው ከማለቃቸው የህንጻዎች ወለሎች በከፍተኛ ሁኔታ ተሰነጣጥቀው መገኘታቸውን፤
• 19%ቱ ደግሞ ጣራቸው ማፍሰስ መጀመራቸውን አረጋግጦአል።

የወያኔን ባለሥልጣናት የሞራልና የሙስና ዝቅጠት ደረጃ ግምት ውስጥ አስገብተን ይህንን የኦዲት ሪፖርት ማንበብ ከፈለግን እነዚህ ለጉብኝት ክፍት የሆኑት 77 ጣቢያዎች በተሻለ የጥራት ደረጃ ላይ ይገኛሉ ተብለው የተገመቱና በዚህም የተነሳ ቢጎበኙ ለጋሾች ተጨማሪ ዕርዳታ ሊሰጡን ይችላሉ አለያም ደግሞ በተሠራው ሥራ ያወድሱናል በሚል እምነት ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ለጉብኝት ክፍት ያልነበሩት ቀሪዎቹ 1232 ህንጻዎች በምን ሁኔታ ላይ ሊገኙ እንደሚችሉ ከዚህ በመነሳት ማወቅ ይቻላል። ጭራሽ የመሠረት ድንጋይ ሳይጣል ተሠርተዋል ተብለው ሪፖርቱ ውስጥ የተጠቃለሉ ሊኖሩ እንደሚችልም መጠርጠር አይከፋም ። የኛ ነው የሚሉትን የትግራይ ህዝብ ነፍስ ለመታደግ በዚያ በ1977ቱ የድርቅ ወቅት ከአለም ለጋሾች የተላከን የዕርዳታ እህል ሽጠው በምትኩ አሸዋ በጆንያ ሞልተው ሂሳብ ያወራረዱ ሽፍቶች የፈረንጅ እግር በማይደርስባቸው የአገሪቱ ክፍሎች የጤና ጣቢያ ህንጻዎችን አስገንብተናል ብለው ገንዘቡን ቢበሉት ምን ያስገርማል?

የግሎባል ፋንድ ኦዲት ሪፖርት ከላይ በተገለጸው ብቻ አላቆመም ። ድርጅቱ ለነፍስ አድን በሰጠው ገንዘብ ህክምና እርዳታ ይሰጥባቸዋል የተባሉና አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ 46 የህክምና አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ጎብኝተው አብዛኛዎቹ የቧንቧ ውሃ አገልግሎት እንደሌላቸው፤ ለበሽታ ናሙና ምርመራ የሚጠቀሙባቸው ማይክሮስኮፖች የተበላሹና ያረጁ በመሆናቸው በተለይ የወባና የሳምባ በሽታን በትክክል ለመለየት የማያስችሉ መሆናቸውን ፤ በ46ቱም ተቋማት ውስጥ ካሉ ዶክተሮችና ነርሶች ስለወባ በሽታ ማኔጅመንት አንዳቸውም ሥልጠና አግኝተው እንደማያውቁ፤ ለህመምተኞች የሚሰጠው መድሃኒት መበላሸት ወይም አለመበላሸቱ በወቅቱ ቁጥጥር እንደማይደረግበት ወዘተ መታዘባቸውን አጋልጠዋል።

የኢትዮጵያዊያንን ህይወት ለማትረፍ ግሎባል ፈንድ የሰጠው ገንዘብ በዚህ መልኩ መባከኑንና በእርዳታ ስምምነቱ ውስጥ ላልተገለጸ አላማና ተግባር መዋሉን ካረጋገጠ ቦኋላ ተቋሙ እርምጃ ለመውሰድ የጀመረውን እንቅስቃሴ በወቅቱ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር የነበረው ሟቹ መለስ ዜናዊ ጣልቃ ገብቶ እንዳከላከለና ለግሎባል ፈንድ የገንዘብ ዕርዳታ ከሚለግሱ የአለም ዲታዎች አንዳንዶቹ የተለያየ ግፊት ፈጥረው ተድበስብሶ እንዲቀር እንዳደረጉት የሚያጋልጥ መረጃ በእጃችን አለ።

እንግዲህ ቴዎድሮስ አድሃኖም የጤና አገልግሎቶችን አስፋፍቶአል በማለት ለአለም ጤና ጥበቃ ዳይሬክተርነት እያደረገ ባለው ዘመቻ በመናፈስ ላይ ካለው የፈጠራ ህይወት ታሪክ በስተጀርባ ያለው እውነታ ይህ እንደሆነ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እናውቃለን። በዚህ ዘረፋ ምክንያት ህክምና አጥተው ህይወታቸው የተቀጠፈ ዜጎች ቁጥርም ውሎ አድሮ ጊዜ የሚያጋልጠው ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

ከዚህ ወንጀል በተጨማሪ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆኖ ባገለገለባቸው ጊዜያትም፡ ድርጅቱ ህወሃት በህዝባችን ላይ የፈጸማቸውን የጎዳና ላይ ጭፍጨፋዎች ፤ በየእስር ቤቱ በተወረወሩ የፖለቲካ እስረኞች ላይ የደረሰውን ሰቆቃና ግርፋት ፤ እንዲሁም እትብታቸው ከተቀበረበት ቦታ በጉልበት እንዲፈናቀሉ ተደርገው ለጎዳና ተዳዳሪነት የተዳረጉ በሺዎች የሚቆጠር ዜጎች ስቃይና መከራ ተሸፍኖ እንዲቀር የቻለውን ሁሉ አስተዋጾ አድርጎአል። የንቅናቄያችን ዋና ጸሃፊ የሆነውን ጓዳችን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከየመን አየር ማረፊያ አሳፍኖ በመውሰድ ተግባር ውስጥም እጁ እንዳለበት እናውቃለን። የአጋዚ ጦር በቅርቡ በኢሬቻ በአል ላይ፤ በጎንደር፤ በባህርዳር ፤ በጌዶ ወዘተ የፈጸመውን ፋሽስታዊ ጭፍጨፋ ጀማሪ ዲሞክራሲ ስለሆን ህግ አስከባሪዎች በእውቀት ማነስ የፈጸሙት ነው በማለት እያናናቀ በተለያዩ አለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተዘባብቶብናል።

እንዲህ አይነት ወንጀለኛን የአፍሪካ አምባገነኖችና አንዳንድ ለሰው ልጆች ሰብዓዊ መብት ደንታ የሌላቸው የአገራቸውን ጥቅም ብቻ ለማስከበር ደፋ ቀና የሚሉ ምዕራባዊያን መንግሥታት አሞጋግሰው ለአለም ጤና ጥበቃ ዳይሬክተርነት ቦታ ቢያነግሱትም ባያነግሱትም ፍትህ እኩልነትና ነጻነት በምድራች ኢትዮጵያ እውን በሚሆንበት ቀን በግልና በቡድን ከፈጸመብን ወንጀል ተጠያቂነት ሊያድኑት እንደማይችሉ ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 ያምናል።
የተባበሩት መንግሥታት አካል የሆነው የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት በእስከዛሬ ታሪኩ በሙያቸውና በሥነምግባራቸው የላቁ ሰዎችን እንጂ እንደ ቴዎድሮስ አድሃኖም ያሉ በሙያቸው የቀጨጩ ፤ ለፖለቲካ ፓርቲያቸው የሥልጣን ዕድሜ መራዘም ሲሉ ንጹሃንን በጠራራ ጸሃይ በማስጨፍጨፍ በሰው ደም የተጨማለቁ ወንጀለኞችን አስተናግዶ አያውቅም። ለንግዳቸው እንጂ ለጥቁር ህዝቦች ህይወት ደንታ የሌላቸው አለም አቀፍ ቱጃሮች እንደ ቴዎድሮስ አድሃኖም አይነት በጥቅም የሚገዛ ታዛዥ ሎሌ በቦታው ለማስቀመጥ እያደረጉ ያሉትን ሩጫ በቅርበት የሚከታተለው አርበኞች ግንቦት 7 የአለም ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የወንጀለኞች መደበቂያ ዋሻ ሊሆን እንደማይችል ይገነዘቡት ዘንድ ያሳስባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

posted tigi flate

የዘር ፍጅት በአማራው ላይ ሲጋለጥ | ወያኔ በፈረንጅ እየታገዙ የሚፈፅሙት ዘር ማምከን ዝርዝር መረጃ እጃችን ገብቷል

በአስቸኳይ ህዝብ ሊያውቀው የሚገባ በጣም አሳዛኝ እና አስደንጋጭ ነገር ነው። አንድ እማኝ በመረጃ አስደግፈው እንዲህ ምስክርነት ይሰጣሉ።
የጓደኞቸ ቤት ልጅ እየተንከባከበች እንድትማር ከማክሰኝት ወረዳ አሯጌ ማርያም የመጣች የ13 ዐመት ትንሽ ልጅ አለች። በቅርቡ ነው ወደ ጎንደር የመጣችው። እጄን አመመኝ ስትላቸው እስኪ እንይልሽ ብለው ሲያዮላት ክንዷ ላይ የተቀበረ ለ 3 አመት የወሊድ መቆጣጠሪያ የሚውል ኖርፕላንት አለ። ደንግጠው ይሄ ምንድነው ወንድ ታውቂያለሽ ወይ ሲሏት ኧረ እኔ ገና ልጅ ነኝ ምንም ወንድ አላውቅም አለቻቸው። ይሄን ማን አደረገልሽ ስትባል።
አሯጌ ማርያም ትምህርት ቤት ሀበሾችም ፈረንጆችም መጥተው ተማሪወች እያረገዙ ስለሆነ በቤተክርስቲያን ተለፎ ከ10 ዐመት በላይ የሆኑ ተማሪወች የወሊድ መቆጣጠሪያውን ኖርፕላንት መጠቀም አለባቸው አሉን። አባቴ አይሆንም እነዚህ ከወንድ ያልደረሱ ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ልጆች ናቸው ቢልም አይ ቤተክርስቲያንም ተነግሯል ይደረግ ተብሎ ተገደደ። ከወላጆቻችን ፈቃድ ውጭ አይናችሁን ጨፍኑ ተብለን አስገቡልን። 5ተኛ ክፍል ጀምሮ ለሁላችንም አስገቡልን አለች።
በጉዳዩ አስተያየት የጠየቅናቸው የጤና ባለሞያ ጉዳዩ እጅግ እንዳስደነገጣቸው በመግለፅ ሲቀጥሉ “እንግዲህ አስቡት ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱትን የዘር ፍሬያቸው ገና ያልፋፋውን ለዘላለሙ እንዳይወልዱ መካን ሊያደርጓቸው ቆርጠው ተነስተዋል” ይላሉ። ለዚህ ደግሞ የአካባቢው የጤና ጣቢያ ሰሪተኞች እና የጤና መምሪያ ሀላፊወች ከቤተክርስቲያን ጋር እየተባበሩ ነው። ይሄ በጣም አስደንጋጭ የሆነ የዘር ማጥፋት ነው። ምንም የማያውቁ ወጣት እህቶቻችን አደጋ ላይ ናቸው።
ይሄን ካላስቆምነው የወያኔ ህልም ይሳካል። በየትኛውም የህክምና ሙያ የ12 እና የ13 ዐመት ህፃን የወሊድ መቆጣጠሪያ አይሰጠውም። ያውም ለኢትዮጵያውያን ይሄ እድሜ በጣም ለጋ እድሜ ነው እንደ ፈረንጆቹ አይደለም። እህቶቻችን ገና 15 ዐመት እንኳን ሳይሞላቸው የዘር ፍሬያቸው ሳይለመልም ሊመክኑ ነው። ለማስረጃ የተላኩት ፎቶወች እጃችን ገብተዋል።
ኢትዮጵያውያን ይህን ፈፃሚወቹን ተከታትለው ማጋለጥ ይጠበቅባቸዋል። ይሄ ነገር ቶሎ መቆም አለበት የአስገቡትንም ቶሎ ማውጣት አለባቸው። ምስክርነት የሰጡት የህክምና ባለሞያ የልጅቷን ሰኞ እናስወጣዋለን ብለዋል። የሚገርመው የህፃናቱ ሳይበቃ ለእናቶችም እናድርግላቹህ ሲሏቸው አይሆንም ቢሉም ጤነኛ እና ቆንጆ ልጅ እንድትወልዱ ሌላም የህክምና አገልግሎት የምታገኙት ይህን ስትቀበሉ ነው ብለው ምንም ያልተማሩትን አታለው አድርገውላቸዋል። ጉዳዩ ያስደነገጣቸው እማኝ እስክንጠፋ አይለቁንም ብለዋል።
በወያኔ የውሸት ፖርላማ ውስጥ የህዝብ ቆጠራ በአማራ ክልል ከ2.5 ሚሊዮን ህዝብ ጎደለ የት እንደጠፋ አላወቅንም ያሉት አንዱ ዘር ማፅጃው የጭካኔ ዘዴያቸው ይኸው ነው።
~~~~~~~~~~~
፨Actions to take፨
1. Contact and expose the foreign agency. The info is attached.
2. Consult with all agencies including the U.N. working on ethnic cleansing
3. Form a special professional group to work on this and similar cases.

posted by tigi flate

 

በማዕከላዊ ያለው የወጣት አወቀ አባተ የእጅ ጣቶች ተሰባብረዋል

(ብራና ሚዲያ) የለውጥ ሐዋሪያ በሆኑት በዐማራ ወጣቶች ላይ የሚደርሰው ቶርቸር እጅግ ጭቃኔ የበዛበትና ለሚሰማውም አስደንጋጭ ነው፤ በአቶ ማሙሸት አማረ በሚመራው መኢአድ የአዲስ አበባ ቀጠና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና በአገር አቀፍ የላዕላይ ምክር ቤት አባል በሆነው በወጣት አወቀ አባተ ከጳጉሜ 5 ቀን ጀምሮ በማዕከላዊ በደረሰበት ቶርቸር የአካል ጉዳተኛ መሆኑን አብረውት ታስረው በነበሩ ሰዎች በኩል የወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወጣት አወቀ አባተ በወይዘሪት ንግሥት ይርጋ የሽብርተኝነት የክስ መዝገብ ሥር ከተከሰሱት ወጣቶች መካከል አንዱ ሲሆን የተመሠረተበትን የፈጠራ ክስ እጣቶቹ በመሰበራቸው ምክንያት መርማሪዎቹ የተሰበሩ እጣቶቹን ይዘው እንደፈረሙበት ነው የተነገረው፡፡ በወጣት አወቀ አባተ ላይ እስካሁን ድረስ የትግሬዎች የቶርቸር ሰለባ ቢሆንም ከመስከረም 3-18 ቀን 2009 ዓ.ም. በየቀኑ የደረሰበት ስቃይ ለአካል ጉዳቱ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

ወጣት አወቀ በአሁኑ ሰዐት ከሁለቱም እጆቹ እጣቶች መሰባበር በተጨማሪ የጀርባው ሰርሰር (ስፓይናል ኮርድ) በብረት በደብደቡ ምክንያት በትክክል መራመድ አይችልም፤ የግራ ጆሮው መስማት ተስኖታል፡፡ ወጣት አወቀ ሽንት በሚሸናበት እና በሚጸዳዳበት ጊዜም ከፍተኛ መጠን ያለው ደም እንደሚፈሰው ነው የነገሩን፡፡ ወጣት አወቀ በአፋጣኝ ሕክምና ካላገኘ በሕይወት የመቆየት እድሉ አሳሳቢ እንደሆነ ነው መረጃውን የሰጡን ሰወች የነገሩን፡፡

ወጣት አወቀ በአዲስ አበባ አየር ጤና አካባቢ የራሱ ጣውላ ቤት የነበረው ቢሆንም እሱ በመታሰሩ ቤተሰቦቹም እንዳያስቀጥሉት ጫና በመኖሩ ምክንያት ድርጅቱ ተዘግቷል፡፡ ወጣት አወቀ ቀደም ባሉት ዘመናት ከሁሉም የዐማራ አካባቢዎች በተለይ ደግሞ የመኢአድ አባላት ከሁሉም አካባቢ በቃሊቲ፣ ሸዋ ሮቢትና ዝዋይ ሲታሰሩ ቤተሰቦቻቸውንና እስረኞችን በገንዘብና በቁሳቁስ በግንባር ቀደም ሲረዱ ከነበሩት መካከል አንዱ ነው፡፡ ሆኖም አሁን ላይ የወጣት አወቀ ቤተሰቦች በአሁኑ ሰዐት ችግር ላይ መሆናቸውን ጭምር ነው የትግል ጓዶቹ የነገሩን፡፡

ወጣት አወቀ አባተ አሁንም ድረስ በዐማራነቱ እየደረሰበት ያለው ስነ ልቦናዊ ጉዳት በአካል እየደረሰበት ካለው ሁሉ የሚልቅ ነው ብለውናል፡፡ መረጃውን የሰጡን ሰዎች በወጣት አወቀ ላይ የደረሰው ግፍ በጽሑፍ የማይገለጽ ብዙ ጉዳይ እንዳለውና የዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ ሕይወቱን ለማትረፍ ጥሪ እንዲቀረብ ሁሉ ተናግረዋል፡፡

posted by tigi flate

ሜጀር ጄነራል አበበ ተ/ሃይማኖት ኢሕአዴጎችን “አጫፋሪ በሆኑ ትምክህት፣ ጥበት፣ አክራሪነት በሚባሉ ቅርንጫፎች ላይ አንተንጠልጠሉ” አሉ

በሕወሓት ክፍፍል ወቅት ከአየር ኃይል አባልነታቸው የተባረሩት ሜጀር ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጻፉት ጽሑፍ ለሥርዓቱ መልዕክት አስተላለፉ:: ሜ/ጄነራሉ “አገራዊ መግባባት ለብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ወሳኝ ዕርምጃ ነው” በሚል በሪፖርተር ጋዜጣ በኩል በላኩት ጽሁፋቸው አገዛዙ “የችግሩን ሥረ መሠረት ትቶ አጫፋሪ በሆኑ ትምክህት፣ ጥበት፣ አክራሪነት በሚባሉ ቅርንጫፎች ላይ ተንጠላጥሎ የሚመጣ ለውጥ ሊኖር እንደማይችል መረዳት አለበት።” ብለዋል::

ጽሁፉን እንደወረደ ያንብቡትና እንወያይበት:

የችግሩን ሥረ መሠረት ትቶ አጫፋሪ በሆኑ ትምክህት፣ ጥበት፣ አክራሪነት በሚባሉ ቅርንጫፎች ላይ ተንጠላጥሎ የሚመጣ ለውጥ ሊኖር እንደማይችል መረዳት አለበት።

ባለፉት ሁለት ዓመታት የነበረው ሁኔታ ከፍተኛ ፖለቲካዊ ውጥረትና ሁከት የታየበት፣ የአጭር ጊዜ፣ መካከለኛና ስትራቴጂካዊ የረዥም ጊዜ የመፍትሔ አቅጣጫ ማስቀመጥ ባለመቻሉ ፖለቲካዊ ችግሩ ሄዶ ሄዶ ወደ ደኅንነት ችግር (Security Problem) ተሸጋግሮ አገራችን በአስቸዃይ ጊዜ አዋጅ እየተዳደረች ትገኛለች፡፡ ለዚያውም ስድስት ወራት ያልበቃው አራት ወራት ጭማሪ የጠየቀ ክስተት ሆኖ እናገኘዋለን። ይህ ማለት የገጠመን ችግር አገርን ሊበትን የሚችል፣ የግዛት አንድነቷንና የሕዝቦቿን ሉዓላዊነት አደጋ ውስጥ ሊጥል የሚችል የደኅንነት ችግር ነው ማለት ነው።

 

ጉዳዩን እንዲህ ባለ ከፍታ አጉልተን ስናይ ነው ለመፍትሔው የምናደርገው እንቅስቃሴ እርባና የሚኖረው። በሰላም ወጥቶ በስላም መመለስ ያለመቻል፣ ስለነገ ውሎ እርግጠኛ መሆን የማይቻልበት የሥጋት ኑሮ፣ ኢንቨስትመንትና የሕዝቦች ሀብት በአድማ እሳት የሚበላበት፣ በአንድ ቀን በርከት ያሉ ፋብሪካዎች የሚወድሙበት፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አገልግሎቶች መውደምና መሽመድመድ፣ ሥራና የቀን ተቀን ግብይት መቆምና የትራንስፖርት ዘርፍ መቆራረጥ ማለት የአንድ አገር አጠቃላይ ደኅንነት አደጋ ውስጥ ወድቋል ማለት ነው።

ሕዝቦች እርሰ በርስ የሚጠራጠሩበትና አንዱ ሌላው ላይ የሚያቄምበት አዝማሚያ የፖለቲካ ችግር ተብሎ በቀላሉ የሚወሰድ ሳይሆን፣ አጠቃላይ የአገርና የሕዝቦች ድኅንነት አደጋ ላይ ወድቋል ማለት ነው። ልማትና ዴሞክራሲ እክል ገጥሞታል ማለት የደኅንነት ችግር ገጥሞናል ማለት ነው። ስለዚህ ፖለቲካዊ ችግሩ ወደ ደኅንነት ችግር ልቆ ተሻግሯል ማለት ነው። የኢትዮጵያ ሁኔታም ከዚህ አኳያ ነው መታየት ያለበት።

ሰሞኑን መንግሥት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ለማሻሻል እንቅስቃሴ መጀመሩ እየተነገረ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ገዥው ፓርቲና ተቃዋሚዎች ለውይይትና ለድርድር ተቀምጠዋል፡፡ አካሄዳዊ (Procedural) ጉዳዮችን አጠናቀው አሁን የውይይት አጀንዳዎችን በመቅረፅ ላይ እንዳሉ በመገናኛ ብዙኃን እየሰማን ነው፡፡ ፖሊሲውን የማሻሻል ሒደትና የፓርቲዎች ውይይትና ድርድር ለየቅል የሚሄዱ ሒደቶች ናቸው እንዴ? ፓርቲዎች የሚደራደሩበት ዋነኛው አጀንዳ ምን መሆን አለበት? በዝርዝር ጉዳዮች ወይስ የፖሊሲዎች ቁንጮ በሆነው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ? በሌላ አነጋገር ከሕገ መንግሥቱ ቀጥሎ ከፍተኛ ጠቀሜታ ባለው የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ወይስ በቅርንጫፍ ችግሮችና መፍትሔዎች ላይ ነው መወያየት ያለባቸው? ወዘተ. የሚሉ ጥያቄዎችን መዳሰስ ተገቢ ነው፡፡

ፓርቲዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉዋቸው ውይይቶችና ድርድሮች በብሔራዊ ደኅንነት መግባባትን ለመፍጠር ከሆነ ይዘቱ ብቻ ሳይሆን ሒደቱ ጭምር በጣም ወሳኝ ነው፡፡ በአንድ በኩል ጥናትና ምርምርን መሠረት ያደረገ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሒደቱ አሳታፊ (Participatory)፣ እንዲሁም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት (Stakeholders) የሚያቅፉ (Inclusive) እንዲሆን ምን መደረግ አለበት? የሚለው መመለስ አለበት፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያን የማዳን ድርድር ከሆነ መግባባት የሚያስፈልገው በተጋረጠብን ከፖለቲካዊ ችግር በላይ ጎልቶ በወጣው የደኅንነት ሥጋታችን ላይ መሆን ያለበት ይመስለኛል።

ከጥቂት ዓመታት በፊት “የኢትዮጵያ የውጭና ብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ግምገማ” የሚል የውጭ ጉዳይና ብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሱን የሚዳሰስ ጽሑፍ አቅርቤ ነበር፡፡ የፖሊሲው መሠረታዊ ጥንካሬዎችና ድክመቶች ምን መደረግ አለባቸው? የሚለውን ንድፍና ጽንፈ ሐሳባዊ ማዕቀፎች (Concepts and Theories of Security) መሠረት አድርጎ የተጻፈ ነበር፡፡ አሁን ካለው ሁኔታ ጋር አዛምዶ ለጋዜጣ በሚሆን መልኩ ያለኝን አስተያየት ለመዘርዘር ነው፡፡ የደኅንነት ጉዳይ ከፖለቲካ በላይ ቁንጮ በመሆኑ ለፓርቲዎች ብቻ የሚተው አይደለም፡፡ መላው ኢትዮጵያውያን እንደየአቅማችን እንድንሳተፍ ይጠይቃል፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዓላማም በጉዳዩ ዙሪያ የግል አስተያየት በመሰንዘር ሌሎችም እንዲሳተፉ ለመጋበዝ ነው፡፡

ጽሑፉ አገራዊ መግባባት ስንል ምን ማለታችን ነው? በሚለው ይጀምርና የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ለምን የሁሉም ፖሊሲዎችና ሕጎች ቁንጮ እንደሆነ ያብራራል (ከሕገ መንግሥቱ በመለስ):: ቀጥሎም የ1994 ዓ.ም. የውጭ ጉዳይና ብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ይገመግማል፡፡ በመጨረሻም ምን መደረግ አለበት? የሚለውን የግል አስተያየት ያስቀምጣል፡፡ የሕዝቦቻችንና የአገራችን ደኅንነት የሚጠበቀው ፈጣን ልማት ሲረጋገጥና የዴሞክራሲ መስተዳደር በቀጣይነት መሠረት ሲጥል ነው፡፡ ከዚህም ተነስቶ ዋናው የደኅንነት አደጋ የዴሞክራሲ እጥረት ነው ይላል፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ትምክህት፣ ጠባብነት፣ ወዘተ. የሚሉት ቅርንጫፎችና አጫፋሪዎች ችግሮች ቢሆኑም ከዋናው ችግራችን ማለት ከዴሞክራሲ እጥረት ሊያዛንፉን አይገባም፡፡

መሠረታዊ ችግሮቻችን ሕገ መንግሥታችን በግልጽና በተሟላ መንገድ ያስቀመጠውን የሦስት ትውልድ መብቶች (Three Generations Of Human Rights) አለመተግበር ነው፡፡ መላውን ኅብረተሰብ የሚመለከት ቢሆንም ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ልዩ ቦታ አላቸው፡፡ ትምክህትና ጠባብነት ማምለጫ መሆን የለባቸውም፡፡ በ1990 የኤርትራ መንግሥት ባልተዘጋጀንበት ለምን እንደወረረን ሌሎች ምክንያቶች ቢኖሩም፣ በዋናነት የተደራጀ የደኅንነት ፖሊሲና አስተዳደር ባለመኖሩ መሆኑን አጠር ባለ መንገድ ያስቀምጣል፡፡ በ2008 ዓ.ም. የተከሰተው አመፅ ለምን እንደ አገር ዱብ እዳ ሆነብን? አመፅ እየመጣ መሆኑን ከወዲሁ ለመገመት ለምን አልቻልንም? በ2008 ዓ.ም. ኅዳር አካባቢ የተከሰተው የኦሮሞ ተቃውሞ እንዴት የመጀመርያ ዙር መሆኑን ለማወቅ ተሳነን? እንዴት አመፅ ከመምጣቱ በፊት ልንከላከለው አልቻልንም? አሁንስ እንደዚያ ዓይነት ነገር አመፅ እንዳይከሰት መሠረታዊ መፍትሔዎች አስቀምጠናል ወይ? በሒደት ይዳሰሳሉ፡፡

አገራዊ መግባባት ስንል?

ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ስንል በውሳኔ አሰጣጥ ባለድርሻ አካላት በአገሪቱ ዋና ዋና ጉዳዮች (በየደረጃው) በፖሊሲ ሕግ በይዘቱ ይሁን በውሳኔ አሰጣጥ ሒደት የሚመለከት ነው፡፡ ሕዝቦች በቀጥታ ይሁን የሚወክላቸው አደረጃጀት (ፍላጎታቸውን) የሚያንፀባርቁና የሚገልጹዋቸው (Articulate) የሚያደርጉባቸው ፓርቲዎች፣ ማኅበራት፣ ወዘተ. ፖሊሲው ሕጉን እንዲያውቁትና እንዲተቹት፣ ሐሳባቸውን የሚያሳርፉበት፣ በቀጣይነት ተሳትፏቸውን የሚያረጋግጡበት ሒደት መግባባትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ሒደቱ ከይዘቱ አይተናነስም የሚባለውም ለዚህ ነው።

የፖሊሲ/ሕጉ አመንጪዎች (ከፍተኛ አመራር) ጭምር በመግባባት የሚጀምር የአብላጫው ሐሳብ ብቻ ሳይሆን፣ የውህዳን ድምፅ (Minority’s Voice) በሚገባ የሚሰማበት ሒደት ነው:: በፖሊሲው/ሕጉ የተወሰነ አንቀጾች ልዩነት ቢኖርም አጠቃላይ ይዘቱና በውሳኔ አካሄዱ ዴሞክራሲዊ ከሆነ ሁሉም በየኔነት ስሜት ለተግባራዊነቱ የሚረባረቡበትና መሻሻል ያለባቸው ላይ ቀጣይ ትግል እንደሚያስፈልገው አምነው፣ ባለድርሻ አካላት መንቀሳቀስ ሲጀምሩ ብሔራዊ መግባባት ደረጃ በደረጃ እየተረጋገጠ ነው እንላለን፡፡ በብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ብሔራዊ መግባባት ለምን አስፈለገ የሚለውን ቀጥሎ እናየዋለን?

ብሔራዊ የደኅንነት ፖሊሲ የሁሉም ፖሊሲዎች ቁንጮ ነው ለምን?

በተለምዶ አስተሳሰብ ብሔራዊ ደኅንነት ማለት በዋናነት ውጫዊና ወታደራዊ አድርጎ ማሰብ የተለመደ ነው፡፡ ሉዓላዊነት (Sovereignty) እና የግዛት አንድነት (Territorial Integrity) በውጭ ሥጋት የሚሽከረከር እንደ ታሪካዊ ጠላቶችን ዓይነት አስተሳሰብ ገዥ ሐሳብ አድርጎ ቆይቷል፡፡ ባደጉ አገሮች አሁንም ወሳኝ አስተሳሰብ ነው፡፡ ያደጉ የምዕራብ አገሮች በብዙ ምዕተ ዓመታት የአገር ግንባታ ሒደት (State Building Process) የሕዝባቸውን መሠረታዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፍላጎቶች አሟልተናል ስለሚሉ፣ በሌላ በኩል ዴሞክራሲ በማረጋገጥ የአገርና የባንዲራ ፍቅር እንደ መንግሥት ያላቸው እምነት ጥሩ ነው ብለው ስለሚያስቡ፣ ከውስጥ የሚነሳ አደገኛ የሕዝብ ተቃውሞ አይኖርም ብለው ስለሚያምኑና ከግሎባላይዜሽን የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆንና ተፅዕኖቻቸውን ለማሳደግ ዋናው የደኅንነት ሥጋት ከውጫዊ አድርገው ያስቀምጡታል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በተለይ በሦስተኛ ዓለም አገሮች ይህ የተለምዶ አስተሳሰብ እንደገና ከሁኔታቸው ጋር አዛምደው ማየት የሚያስገድድ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በሽግግር ላይ ያሉና የተከፋፈለ ኅብረተሰብ (Divided Society) ያላቸው አገሮች ዋናው የብሔራዊ ደኅንነት ሥጋት ውስጣዊና ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መዋቅር (Structure) የፈጠረውና በኅብረተሰቡ ኋላቀር አስተሳሰብ የሚታጀብ በተለይ ብቃት ባለው የዴሞክራቲክ አስተዳደር እጥረት የሚነሳ ነው፡፡ ስለዚህ በዋናነት ውስጣዊ ነው፡፡

የውጭ ጠላቶች ይህን ተንተርሰው የራሳቸውን ፍላጎት ለመጫን መሞከራቸው አይቀሬ ነው፡፡ ከውጭ የሚገኘውን በጎ ዕድል (Opportunity) ለመጠቀምና ሥጋት (Threat) ለመከላከል ከፍተኛ ሥራ መሥራት ቢኖርብንም፣ ዋናው ዕድልና ለደኅንነት የሥጋት ምንጭ ግን የውስጣችን ሁኔታ ነው፡፡ እኛ ስንደክም ነው የውጭ ጠላቶችም ለማጥቃት የሚቃጡት፡፡ በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የመጀመርያው ክፍል በዋናነት የሕዝቦቻችን ስስት ትውልድ ሰብዓዊ መብቶች ዕውቅና ሰጥቶ በግልጽና በተሟላ አኳኋን ያስቀምጣል፡፡ ሁለተኛው ክፍል እነዚህን መብቶች ለማረጋገጥ አገር (State) እና መንግሥት (Government) እንዴት መደራጀት እንዳለበትና ተዛማጅ ፖሊሲዎችና ሕጎችን ያስቀምጣል፡፡ በሌላ አገላለጽ አገር/መንግሥት በዚያ መልክ እንደ ደረጃ የተደረገው የሕዝቦቻችን የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ መብቶች ለማረጋገጥ ነው፡፡ ከዚያ የዘለለም ከዚያም ያነሰም ዓላማ የለውም፡፡

በሕገ መንግሥቱ የተቀመጡትን የኢትዮጵያ ሕዝቦች ፍላጎቶች የአገራችን ጥቅሞችና ያሉንን ሰብዓዊና ተፈጥሯዊ እሴቶችን አጣምሮ ሰላምና ልማት፣ ዴሞክራሲ ለማረጋገጥ ከውስጥ ሆነ ከውጭ የሚገኙትን ዕድሎች/ፀጋዎች በሚገባ አጢኖ፣ የሕዝቦችን ሰላም፣ ልማት፣ ዴሞክራሲ ለማደፍረስ ከውስጥ ሆነ ከውጭ የሚገኘውን ሥጋቶች አንጥሮና ቀምሮ የአገራችን፣ የአካባቢያችንና ዓለም አቀፋዊ አካባቢውን በጥናት አረጋግጦ እንዴት ሥጋቶችን መቀነስ እንደሚችልና መከላከል የሚያስችል ስትራቴጂዎችን ያቀፈ በመሆኑ፣ ከሕገ መንግሥቱ ቀጥሎ ለሁሉም የአገራችን እንቅስቃሴዎች አቅጣጫ የሚያስቀምጥ በመሆኑ ነው የውጭ ጉዳይና ብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ የፖሊሲዎች ሁሉ ቁንጮ የሚያስብለው፡፡ ለፖለቲካዊ፣ ለኢኮኖሚያዊና ለማኅበራዊ እንቅስቃሴዎችም አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ፖሊሲ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የብሔራዊ ደኅንነት ጉዳይ በጥቂት ጄኔራሎች፣ የደኅንነት ባለሙያዎች (Experts) እና በሥልጣን ላይ ባሉ ፖለቲከኞች ብቻ ሳይሆን የመላው ኅብረተሰብና የኅብረተሰብ የተለያዩ አመለካከት የሚያንፀባርቁና የሚገልጹ ፓርቲዎች፣ ሲቪልና ፕሮፌሽናል ማኅበራት ጉዳይ የሚሆነው፡፡ በብሔራዊ የደኅንነት ፖሊሲ መግባባት ማለት የአገራችንን ዕድሎችና ሥጋቶች መሠረት አድርጎ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ የወታደራዊና የደኅንነት ክፍል እንዴት መመራትና መደራጀት እንዳለበት በአጠቃላይ መስማማት ማለት ነው፡፡ ፖለቲካዊ የኛው የሁላችን፣ ኢኮኖሚያዊ የኛው የሁላችን፣ ወታደራዊና ደኅንነት ክፍሎች የኛው የሁላችን ናቸው ብለን በአጠቃላይ ተስማምተናል ማለት ነው፡፡ የሚያለያዩን ጉዳዮች መኖራቸው አይቀርም፡፡ የሚታዩት ግን በዚህ ማዕቀፍና የተመቻቸ ሁኔታ ስላለ በሰላምና በሰላም ብቻ ለመታገል የምንችልበት የጋራ አስተሳሰብ አለ ማለት ነው፡፡ ከፅንፈኞች በስተቀር፡፡

የ1994 ዓ.ም. ፖሊሲ የአመለካከት አቅጣጫ ለውጥ

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይና ብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ አገር በቀልና ከደኅንነት አኳያ ያሉት በቂ ዕድሎች/ፀጋዎችና ሥጋቶች ዋናዎቹ ውስጣዊ መሆናቸውንና ድህነትና ኢዴሞክራሲያዊነት የአገሪቱ ህልውና ከሚፈታተኑን ሥጋቶች ዋናዎቹ መሆናቸውን በማያሻማ መንገድ ያስቀምጣል፡፡ የአገርና የሕዝብ ፍላጎትን አስተሳስሮ የአገር የመበታተን አደጋ የሚያጋጥመው በዋናነት በውስጣችን ባሉት ችግሮች መሆናቸውን ይገልጻል፡፡ ደኅንነት ጥቂቶች ባለሥልጣናት/ጄኔራሎች የደኅንነት ባለሙያዎች ብቻ አለመሆኑናቸውን የመላው ሕዝቦች አጀንዳ ሆኖ እንደ ፖሊሲ ያላስፈላጊ ሚስጥርነት ድባብ ያገለለ (በሚስጥር የሚጠበቁ እንዳሉ ሁሉ) መለያው ነው፡፡ የደኅንነት የድብብቆሽ ሥራን ድባቅ የመታ ለውጥ ነው ያሳየው።

የደኅንነት ጽንሰና ንድፈ ሐሳባዊ ማዕቀፎችን በዓለም ዕውቅ ከሆኑ አስተምህሮዎችን (Schools of Thoughts) ቀደም ብሎ በዘውዳዊ ሥርዓትና በወታደራዊ አገዛዝ ሥርዓት ከነበሩት ፖሊሲዎች አንፃር ሲታይ፣ መሠረታዊ የአቅጣጫ ለውጥን (Paradigm Shift) የሚያመላክት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ፍላጎትና ተስፋ ከፈጣን የኢኮኖሚያዊ ዕድገት ተጠቃሚ መሆን ማለትም ከደኅንነት፣ ከኋላቀርነት፣ ከመሃይምነትና ከበሽታ የፀዳ ሕይወት መኖር ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ያላትን ኢትዮጵያ በመፍጠር የቡድንና የግለሰቦችን መብት ማስከበር፣ መልካም አስተዳደርን ማረጋገጥና ለኑሮና ለሥራ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ነው ብሎ ያስቀምጠዋል፡፡ የብሔራዊ ጥቅም (National Interest) በማያሻማና በተሟላ መንገድ እንዲህ ያቀርበዋል፡፡ “ብሔራዊ ጥቅም ማለት የሁሉም ሕዝብ ጥቅም ማለት ነው፡፡ ከዚህ ያነሰም የበለጠም ማለት አይደለም” (16) ትንተናው ልዑላዊነትና የድንበር አንድነት (Sovereignty and Territorial Integrity) ከሕዝቦች ፍላጎትና ጥቅም ጋር ብቻ አቀናብሮ ያየዋል፡፡ ከእነዚህ ጽንሰ ሐሳብ ውጫዊ አመለካከት ቋንቋዎች (External-looking Orientations) ይለያል፡፡ ፖሊሲው እየደጋገመ እንደሚያሰምረው ፈጣን የኢኮኖሚ ልማትን፣ ዴሞክራሲና ሰላምን ማምጣት በከፍተኛ ድህነትና ኋላቀርነት ለምትገኝ አገር መሠረታዊ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡

በአጠቃላይ የፖሊሲው ስትራቴጂዎች ከላይ የተጠቀሱትን ወሳኝ የደኅንነት አካባቢ መፍጠር ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ብሔራዊ ኩራትን (ነፃነታችን ጠብቀን መኖራችንን) እንደ አንድ እሴት፣ ድህነታችን (Poverty) እንደ አሳፋሪ ታሪክ አስቀምጦ፣ የተለዋዋጩ ምሥራቅ አፍሪካ ቀንድ እንደ መልካም ዕድልና ሥጋት፣ ሉላዊነት (Globalization) ለልማትና ለዴሞክራሲ ግንባታ ያላቸውን ተፅዕኖ እንደ መልካም ዕድልና የሥጋት ምንጭ በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ መካከለኛው ምሥራቅን በተመለከተ ፖሊሲው እንዲህ ይላል፡፡ “መካከለኛው ምሥራቅ በእኛ ሰላምና ደኅንነት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በእኛ ኢኮኖሚ ላይ በእጅጉ ተፅዕኖ ያደርጋል፣ ለዚህ ነው የመካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ በእኛ በኩል ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡” (ኢውጉብደፓ፡ 46)

የመከላከያ መዋቅርን (Military Establishment) በተመለከተ ስትራቴጂዎችን ሁሉን አቀፍና የተቀናጀ (Comprehensive and Coherent) ሆኖ የአገሪቱን የልማት እንቅስቃሴ መሠረት አድርጎ የሚገነባና በጥልቅ የአደጋ ትንተና ላይ የተመሠረተ አቅም ግንባታ ላይ ሲሆን፣ ብቃት ያለውና ዘመኑ የደረሰበት የመረጃ መረብ ዕድገትን በማቋቋምና የሰው ልማት ላይ በማተኮር የሚታነፅ መሆን አለበት ይላል፡፡ ይህ ማለት በሁለት ተመሳሳይ የቴክኖሎጂ አቅም ያላቸው ኃይሎች መካከል ጦርነት ቢነሳ ወሳኝ ልዩነት የሚፈጥረው ሰው ነው፡፡ (ኢውጉብደፓ፡ 43) በሚል ነው፡፡ የአፍሪካን ትልቁ ሠራዊት ከመገንባት የደርግ እብደትና ድንፋታ ተወጥቶ ከአገሪቱ አጠቃላይ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ተዛምዶ በልክ (Right Size) ሠራዊት ለመገንባት የሚቀነቅነው ሐሳብም ሌላው የአቅጣጫ ለውጥ ነው፡፡ ፖሊሲው የፋይናንስ ሀብትን በጥንቃቄ መጠቀምን በኢኮኖሚያዊና በመከላከያ ወጪ መካከል ቁርኝትን፣ የሠራዊቱና የውጭ ጉዳይ ዲፕሎማቶች አቅም ግንባታ ከኢኮኖሚ ልማት አንፃርና ከአደጋዎች ጋር ያለውን ትስስር በሚገባ ያስቀምጠ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በጠመንጃ ወይም ቅቤ (Gun or Butter) ያለውን ግጭት ለመፍታት የታሰበለት አማራጭ ያስቀመጠ ይመስላል፡፡

ፖሊሲው ስለጠንካራ የማስፈጸም አቅም ግንባታ በሚመለከት “በትክክል የተቀረፀ የውጭ የአገር ውስጥ ፖሊሲዎች ዓላማዎች፣ ግቦች ፕሮግራሞች ስትራቴጂዎች በአግባቡ ተግባር ላይ ካልዋሉ የትም ሊያደርሱ አይችሉም፣ ለዚህም ነው ውጤታማ የማስፈጸም ብቃት እንደ መሠረታዊ ስትራቴጂ የሚታየው፤” (ኢውጉብዴፓ፡ 49):: ይህ አንድ ቁልፍ ነገር ነው። ፖሊሲው ከዘውዳዊውናና ከወታደራዊው አገዛዝ በተለየ ከበባ አስተሳሰብ (Siege Mentality) ወጥቶ “ታሪካዊ ጠላቶቻችን” የሁሉም ችግሮቻችን ምንጭ እንደሆነ በቀጣይነት ከማላዘን አልፎና በተቻለ መጠን የሥጋት ምንጮችን በመቀነስና ትብብርን የማስፋት አቅጣጫ ተከትለዋል፡፡ “የትኞቹ ጥቅሞቻችን አስፈላጊ እንደሆኑና የትኞቹ ኃይሎች ፍላጎታቸውን ለማስጠበቅ እንደሚፈልጉ በሚጠቅም አቅምና ኃይል ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ ከግንዛቤ በመነጨ አደጋዎችን መጋፈጥና በትብብርና ገንቢ በሆነ መንገድ የሥጋት ምንጮችን ማስወገድ አስፈላጊ ነው፤” ይላል የፖሊሲ ሰነዱ በገጽ 33፡፡ በአጠቃላይ ፖሊሲዎቻችን ጥልቅ በሆነ ጥናትና ምርምር መቅረፅ እንዳለባቸው እያስቀመጠ እየተመላለሰ አጽንኦት የሚሰጠው ግን፣ “ለእኛ ዋነኛው የደኅንነት ሥጋት ምንጭ ውስጣዊ ነው፡፡ የድህነት መስፋፋት የአገሪቱ ህልውና አደጋ ሊሆን ይችላል፡፡ የመልካም አስተዳደር ዕጦት የዴሞክራሲ አለመኖር ወደ ደም መፋሰስና ጥፋት ሊከተን ይችላል፤” (91)፡፡ ሆኖም ፖሊሲው አጠቃላይ የአቅጣጫ ለውጥ የሚያመለክት ቢሆንም ቀጣይነት (Consistency) እና ሙሉዕነት (Comprehensiveness) ይጎድለዋል፡፡

ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትና ኅብረ ብሔራዊነት እንደ መልካም ዕድል በሚገባ አያስቀምጥም፡፡ የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት እጅጉን መሠረታዊና ፋውንዴሽናል (Very Basic and Foundational) የግጭቶች መሠረታዊ የአፈታት አቅጣጫዎች በመተንተን ውስጣዊ ደኅንነት የሚረጋገጥበት ሁኔታን አመቻችተዋል፡፡ በተሟላ ሁኔታ መብቶችን በማወቅ ሕገ መንግሥቱ አንድነት ማራኪ ያደረገ ብቻ ሳይሆን፣ አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ማኅበረሰብን የመፍጠር ሒደትም አመቻችቷል፡፡ በዚህ ሁኔታ ማኅበራዊ ቡድኖች (Societal Groups) ተጨባጭ የሆነ ፍላጎታቸውን ለማጠናከርና ተጨባጭ ያልሆኑትን ሊሟሉ የማይችሉ ፍላጎቶች መሆኑን ለመገንዘብ የሚያስችል ሒደት አቀናጅቷል፡፡

ፖሊሲው ለደኅንነት አካባቢ (Security Environment) ሕገ መንግሥታዊ ዓውደ ጽሑፍ (Context) ከማስቀመጥ አኳያ የሰጠው ትኩረት አነስተኛ ነው፡፡ ብዝኃነት በአጠቃላይ የኅብረ ብሔራዊነት እሴት በተለየ፣ በዋጋ የማይተመን ሀብት መሆኑንና ለአገር ግንባታ ሒደትና ሁሉን አቀፍ ልማትን ለማፋጠን ያሉትን አዎንታዊ የልማት፣ የዴሞክራሲና የሰላም ሐሳቦች፣ መልካም ዝንባሌዎች የጋራ ልምዶች የግጭት መቆጣጠርና የአስተዳደር ዘዴዎች እንደ ዋነኛ አቅም አድርጎ አያስቀምጥም፡፡ ከዓለም አቀፍ የሚገኘውን የቴክኖሎጂና የቁስ ድጋፍ በከፍተኛ ድጋፍ ደረጃ ሲያደንቅና አስፈላጊነቱን ሲያስረግጥ፣ ብዝኃነትንና ኅብረ ብሔራዊነትን የመሳሰሉ ፀጋዎችን በመርሳት “የኢትዮጵያ ሕዝቦች” የሚለውን ጽንሰ ሐሳብ ወደ ጎን በመተው፣ “የኢትዮጵያ ሕዝብ” የሚለውን ሐሳብ ሲያራምድ ከላይ የተገለጸውን የአቅጣጫ ለውጥ ስንኩል ያደርገዋል፡፡ ይህ የቃላት ጨዋታ ሳይሆን የራሱ ጥልቅ ፖለቲካዊ ትርጉም ያለው ነገር ነው። የ1994 ዓ.ም. ፖሊሲ መሠረታዊ የሆነ ከውስጥ የሚነሱ ፀረ ዴሞክራሲ ሥጋቶችን ችላ ያለ ነው፡፡ የአገራችን ደኅንነት ዋናው ውስጣዊ ነው ብሎ ለሚነሳ አስተሳሰብ የዴሞክራሲ ግንባታ በድህነት ማስወገጃ ትግል ሒደትን ሊያኮላሹ የሚችሉትን በውስጥ ተቋማት፣ ኃይሎችና ዝንባሌዎች ምንም ነገር ሳይል ማለፍ የሚያስገርም ነው፡፡ ዴሞክራሲን ለመገንባት በሚደረገው እንቅስቃሴ የውስጥ ተቋማት፣ ኃይሎችና ዝንባሌዎች በአዎንታዊ ይሁን በአሉታ ውስጥ መሆንን እንደታወቀ ያለመጥቀሱ አሁንም ያስተዛዝባል፡፡ በመንግሥት ይሁን በኅብረተሰቡ ሁልጊዜ በከፍተኛ ውጥረት (Tension) የሚኖሩት የፍፁም አንድነትና የመበተን ኃይሎች (Centripetal and Centrifugal Forces) መሳሳብ ቀጣይነት ያለው የደኅንነት ሥጋት መሆናቸውን የተገነዘበ አይመስልም፡፡

የፌዴራሊዝም ሥርዓት መሠረታዊ የደኅንነታችን ዋስትናና መሠረት ቢሆንም፣ እንደ ማናቸውም ሥርዓት የራሱ ተግዳሮቶች ያሉት አደረጃጀት ነው፡፡ ማይክል በርጊስ የተባለ ምሁር የፌዴራል መዋቅርን አስቸጋሪነት በጽሑፍ “In Seymour and Gugnoned” (2012፡24) እንዲህ ሲል ያብራራል፡፡ “የፌዴራል አገር ግንባታ በተፃራሪዎች ችግሮችና አደጋዎች የተሞላ በመሆኑ ከመጀመርያው በጭንቀትና በውጥረት የተሞላ ሊሆን ይችላል፡፡ “በመቀጠልም ትራዱን (1968፡12) በመጥቀስ “እንደ የራስ ዕድልን በራስ የመወሰን ሐሳብ ፌዴራሊዝም እንዲኖር ቢያስገድድም እዚያ ሳለ የፌዴራል ሥርዓቱን ያልተረጋጋ ያደርጋል፤” ይላል፡፡ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔርና ብሔረሰቦች ከሰላም፣ ከልማትና ከዴሞክራሲ መሠረታዊ ጥቅሞቻቸው የሚረጋገጥ ቢሆንም፣ ተጨባጭ ሁኔታው ግን የተለያየ ትርጉምና አመለካከት (Perceptions) እንዲኖር ሊያደርግ ይችላል፡፡ ከፈጣን የኢኮኖሚ ልማት የሚያገኙት ድርሻ በተግባርም ይሁን በአስተሳሰብ የተለያዩ ባህሎችና የሕዝብ ብዛት ላላቸው አካሎች የተለያዩ ትርጉም ያለው ነው ወይም ሊኖረው ይችላል፡፡ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ብሔሮች ወይም ብሔረሰቦች በሕገ መንግሥታዊ ዲዛይን፣ በምርጫ ሥርዓቱና በመንግሥት ተቋማት አወቃቀር፣ በተለይም በሥራ አስፈጻሚና በደኅንነት ኃይሎች ብሔራዊ ተዋጽኦ (National Composition of the Executive, Military and Security Forces) ላይ ቅሬታ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ የታላላቅ ብሔሮች ልሂቃን (Elites) ባለው የፖለቲካ ሥርዓት ያልተሟሉ ፍላጎቶች ሊኖራቸው ሲችል፣ ትንንሽ ብሔሮች መሬታቸውን፣ ሀብታቸውንና ማንነታቸውን የማጣት ሥጋት ሊያድርባቸው ይችላል፡፡

እነዚህ ክስተቶች ቀጣይነት ባለው ሰፊ ጥናትና ምርምር መሠረት አድርጎ በሕዝቦች መካከል ቀጣይነት ያለው ሰፊ ዴሞክራሲያዊ ውይይት በማድረግ መስተካከል ያሉበትን በወቅቱ መሟላት፣ የማይቻለውን በማስረዳት የሕዝቦች አንድነት ብሎም የአገሪቱ ደኅንነት ማረጋገጥ ይጠይቃል፡፡ ትምክህትና ጠባብነት ከሚባሉ አጫፋሪ ሐሳቦች በየጊዜው መውደቅ ያባብሰው እንደሆነ እንጂ የሚፈይደው የለም፡፡ አሁንም መፍትሔው ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር በማጠንከርና የሕዝቦችን ሁለንተናዊ መብቶች በማስከበር ሁለንተናዊ ጥቅሞቻቸውን ማረጋገጥ ነው፡፡ በ1994 ዓ.ም. ፖሊሲ እነዚህ ተግዳሮቶችን በዝምታ ለምን እንዳለፍናቸው ለመረዳት ያስቸግራል፡፡

ከደኅንነት አንፃር ወደብ የለሽዋ ኢትዮጵያ ሊያጋጥሟት የሚችሉ የደኅንነት ተፅዕኖዎችን የ1994 ዓ.ም. ፖሊሲ በዝምታ ነው ያለፈው፡፡ ነገር ግን ዘመናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ፈጣን፣ አስተማማኝ፣ ብቃት ያለውና ወጪ ቆጣቢ ዓለም አቀፍ ግብይትን ይጠይቃል፡፡ የባህር በር ዕጦት የኢኮኖሚ ብሎም የደኅንነት ማነቆ ሊሆን ይችላል፡፡ ግጭት በማይጠፋበትና ራሳቸውን ለመቻል በትግል ላይ ያሉ መንግሥታት ባሉበት የአፍሪካ ቀንድንና ቀይ ባህርን ለመቆጣጠር ላይና ታች የሚሉት የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ቀጣይ እንቅስቃሴ ባለበት ሁኔታ፣ የባህር በር ዕጦት የሚፈጥረውን ሥጋት ቸል ማለት አይገባም፡፡

አጥንትና ሥጋ እንጂ ደም የሌለው ፖሊሲ

ፖሊሲው አገር በቀል የመሆኑን ያህል አዲስ የአቅጣጫ ለውጥ በማምጣት በደኅንነት ዙሪያ መሠረታዊ የአመለካከት አረጋግጧል፡፡ ሆኖም የአቅጣጫ ለውጡ ቀጣይነት ባለው መልኩ የተተነተነ ባለመሆኑ ከላይ የተገለጹትን መሠረታዊ ድክመቶችም ያዘለ ነው፡፡ ፖሊሲው በሰፊ ጥናትና ምርምር እንዲታጀብ በቂ አቅም በመፍጠር አስፈላጊነትና አገራዊ መግባባት እንዲኖር ቢያውጅም ይህን ለማስፈጸም የሚችለው የተሟላ የደኅንነት አስተዳደር (Security Governance) በሚመለከት ዝምታን መርጧል፡፡ አንድ ፖሊሲ የተሟላ ቢሆንም ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር በጥበብ አዛምዶ ለመተግበርና ለማበልፀግ፣ ጉድለቶች ካሉትም ለማረም የግድ ጠንካራ አስተዳደር ያስፈልገዋል፡፡ ቀጣይነት ያለውና የተሟላ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ የሚከሰቱትን ዕድሎችና ሥጋቶች ቀጣይነትና ሰፊ በሆነ ጥናትና ምርምር ለማጎልበት የተደራጀ የደኅንነት አስተዳደር ያስፈልጋል፡፡

ለዚህ ጽሑፍ ሲባል አጥንትና ሥጋ የምንለው የደኅንነት አካባቢ (Security Environment) እና Hardware ጨምሮ አጠቃላይ የደኅንነት ቅርፅ (Security Posture) ሲሆን፣ “ደም” ደግሞ የፖሊሲው ስስ ‹Software› ነው፡፡ የደኅንነት ቅርፅ ያለ “ስስ” ደም የሌለው አጥንትና ሥጋ ይሆናልና፡፡ እንደ ታዋቂዎቹ የደኅንነት ምሁራን አዘርና ሙን (Azar and Moon 1988) ገለጻ፣ “የደኅንነት አካባቢ ሥጋቶችና ዕድሎችን ከቁሳዊ አቅሞች (ወታደራዊ ኢኮኖሚያዊ ኃይል) እና ተጨባጭ የፖሊሲ መሠረተ ልማት፣ ወታደራዊ ዶክትሪን የኃይል አወቃቀር (Force Structure)፣ መረጃ (Intelligence)፣ የመሣሪያ አመራረጥ፣ ወዘተ. የሚያካትተው የደኅንነት ቅርፅ (Security Posture) “ደም” (Software) ከመጨረሻው የፖሊሲ ውጤቶችና አጠቃላይ የፖሊሲ አፈጻጸም የሚያስተሳስር ነው፤” ይላል። በሌላ አገላለጽ የፖሊሲው ዶክመንት ወደ ተግባር/መሬት ለማውረድ የሚያስችል “ለአጥንቱና ሥጋ” ሕይወት የሚዘራ ደም ነው ሶፍትዌር የሚባለው፡፡

የደኅንነት አስተዳደሩ ፖሊሲው የተሟላና ዘላቂ ቅቡልነት (Legitimacy) እንዲያረጋግጥ፣ የሁሉም ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ኃይሎችና የደኅንነት ክፍሎች ቅንጅት/ውህደት (Integration) እንዲኖር የሚያረጋግጥና የፖሊሲው አቅም በቀጣይነት ለመገንባት የሚያስችል ነው፡፡ ፖሊሲው በትክክል ያነጠረው የአገሪቱ ህልውና ዋናው ሥጋቶች ድህነትና የዴሞክራሲ እጥረት መሆኑን አስቀምጧል፡፡ በሌላ አገላለጽ ፈጣን ልማትና የዴሞክራሲ ግንባታ ባረጋገጥን ቁጥር የአገራችን ህልውና የሚያስተማምን መሠረት እየተጣለ ይሄዳል ማለት ነው፡፡

ቅቡልነት ለማረጋገጥ “የመጀመርያ ቅቡልነት” (Prema-facie Legitimacy) ማንፀባረቅን ይጠይቃል፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናት ብሔራዊ ተዋጽኦ፣ የአመራሮቹ ብቃት፣ የሕዝብ ባህል/ወግ የማክበርና አመርቂ ሕገ መንግሥትን ይጠይቃል፡፡ ቅቡልነቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሕገ መንግሥቱን የመተግበር ህያው ፖለቲካ ለመምራት የሚወጡት ፖሊሲዎችና ሕጎች ጥራትና የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ፣ ሥርዓቱ እኛን ይወክላል፣ ፍላጎታችን ቀስ በቀስ እያሟላ ይሄዳል፣ በአገራችን ጉዳይ እኩል እየተሳተፍን፣ ወዘተ. የሚል አመለካከት (Perception) ካለ “አጥንቱና ሥጋ” ነፍስ ለመዝራት ህያው ሆኖ እንዲተገብር የመጀመርያው ፈተና አልፏል ማለት ነው፡፡ ቅቡልነት የሚባል ደም፡፡

በእውነትም ይሁን በተሳሳተ መንገድ “የአንድ ብሔር የበላይነት አለ”፣ “የሚገባን ሥልጣን እያገኘን አይደለም”፣ “በበጀት አድልኦ አለ”፣ “ፍትሕ የለም” የሚባል ሰፊ አስተሳሰብ ካለ ሕይወት የሚዘራ ደም መሆኑ ቀርቶ “አጥንትንና ሥጋውን” የሚፈጅ እሳት ይሆናል፡፡ ሕግ ካልተስተካከለ አገሪቱ ባልፈነዳ እሳተ ጎመራ ላይ እንደተቀመጠች ሊቆጠር ይችላል፡፡ ስለዚህ አቅም ያለው የደኅንነት አስተዳደር ካለ ቀጣይ በሆነ ጥናት እያካሄደ ቅቡልነት የሚያሰጡ እውነተኛ ምክንያቶችን ያለማወላወል በማስተካከል፣ በተሳሳተ አመለካከት (Perception) በግልጽ ከሕዝቦች ወኪሎች ጋር እየተወያዩ ረመጡን በጊዜው በማጥፋት ቅቡልነት እንዲጠናከር ያደርጋል፡፡ በሌላ በኩል ውህደት (Integration) የሚባለው “ደምም” በብዛትና በጥራት መገኘት ይኖርበታል፡፡ በአገራችን ሁኔታ ዴሞክራሲ ያለ ፈጣን ልማት፣ ልማት ያለ ዴሞክራሲያዊ ምኅዳር መረጋገጥ አይችሉም፡፡ ልማቱን እናፋጥነው ዴሞክራሲው ቢቆይም ቀስ ብሎ ይደርሳል ማለት የዋህነት ነው፣ ወይም ደግሞ አውቆ አጥፊነት ነው፡፡ የፈጣን ልማት ጉዞና ዴሞክራሲያዊ ግንባታ መዋሀድ ይኖርበታል፡፡ ፖለቲካው ከኢኮኖሚ፣ የውጭ ሥጋት ከውስጥ፣ ሲቪል አስተዳደሩ ከወታደሩ፣ ፌዴራል መንግሥቱ ከክልል ካልተዋሀደና መነጣጠል ከመጣ፣ የተለያዩ ማኅበራዊ ኃይሎችን ወደ አንድ ፖለቲካዊ አቅጣጫ ለመምጣት ካልተቻለ የአደጋ ምልክት ነው፡፡ የፖለቲካው መበታተን በአገር አደጋ እንዲያንዣብብ ያደርጋል፡፡ የውህደት ደሙ ካልደረቀ ወይም መሳሳት ካሳየ፣ ወይም ከቆሸሸ አጥንቱ ይጎብጣል ሥጋው ይበሰብሳል፡፡

የፖለቲካዊ ሥርዓቱ ቅቡልነትና ውህደት እየተረጋገጠ ሲሄድ (ሕገ መንግሥቱን መሠረት ያደረገ) የዴሞክራሲ ትውልድን ዕድገት ያፋጥናል፡፡ አንዳንድ የኦሮሞ ምሁራን እንደሚሉት የ“ቁቤ ትውልድ” (Qubee Generation) የኦሮሞ ሕዝብ ትግልን ውጤት መሠረት አድርጎ አዲስ ታሪክ በመጻፍ፣ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በመሆን ዴሞክራቲክ ሥርዓትን ለመገንባት ወይም በትግራይ እንደሚባለው “ሳልሳይ ወያኔ” ትውልድ ማለት የሁለተኛው ወያኔ ድል መሠረት አድርጎ አመራሩን በመንጠቅ፣ ፖለቲካዊ መንሸራተቱን ከሌሎች ወጣቶች ሆነው ለመፍታት የሚሞክር በሌሎች ሕዝቦችም ተመሳሳይ ምሳሌዎች ሊጠቀሱ ይችላል፡፡ ተቀባይነትና ውህደት ለማረጋገጥና የግድ ፖሊሲውን የማስፈጸም አቅም (Policy Capacity) ይጠይቃል፡፡ አቅም ለመገንባት የጠራ አቅጣጫ ያስፈልጋል፡፡ ተቀባይነትና ውህደት እያረጋገጠ የሚገነባ አቅም፡፡ የዴሞክራሲያዊ ትውልዱ፣ የቴክኖሎጂ ትውልድ፣ የአፍላ ጉልበት ትውልድ መሠረት አድርጎ መገንባት ይጠይቃል፡፡

ከፌዴራል ጀምሮ እስከ ቀበሌ ፖለቲካዊ ሳይንቲስቶች፣ ኢኮኖሚስቶች፣ የፀጥታ ባለሙያዎች. . . ወዘተ. ማእከል ያደረገ የአገራችን የውስጥ ዕድሎችንና ሥጋቶች ከአፍሪቃ ቀንድ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅና ከግሎባላይዜሽን ጋር አስተሳስሮ ፖሊሲው ያስቀመጠውን አቅጣጫ በተሟላ መንገድ የሚረዳና የሚያጎለብት፣ አጥንቱና ሥጋው ከበቂ የደም ጥራት ጋር አዋህዶ የደኅንነት አቅሞችን በከፍተኛ ደረጃ ተጠቅሞ ሥጋቶችን በቀጣይነት በመቀነስ፣ በፈጣን ዕድገት ዴሞክራሲያዊ ምኅዳሩ እየሰፋ የተረጋጋች አገራችንን የሚገነባ አቅም መፍጠር ያስፈልጋል፡፡ የተሟላ የደኅንነት ቅርፅ (Security Posture) እንዲኖር ተቀባይነት፣ ውህደትና የፖሊሲ አቅም እያዳበረ እንዲሄድ የሚያስችል አደረጃጀት ያስፈልገዋል፡፡ በተለምዶ የብሔራዊ ደኅንነት ካውንስል (National Security Council) እየተባለ የሚጠራውና በሥሩ በጣም ጠንካራና የተሟላ የደኅንነት ሴክሬተሪያት (Secreteriat) እንዲኖር የግድ ነው፡፡

የ1994 ዓ.ም. ፖሊሲ ስለ ካውንስሉና ሴክሪታሪያቱ ዝምታ መርጧል፡፡ የብሔራዊ ደኅንነት ካውንስል ደኅንነትን የሚመለከት ከፍተኛው የሥራ አስፈጻሚው አካል ሲሆን፣ በየጊዜው እየተሰባሰበ ወሳኝና ስትራቴጂካዊ ውሳኔዎችን የሚያሳልፍና ተግባራዊነቱ በሴክሬታሪያቱ በኩል የሚከታተል ነው፡፡ ሴክሪታሪያቱ በቁጥር ሆነ በብቃት ከሁሉም ዘርፍ የተውጣጡ በቂ ባለሙያዎችን ያካተተ ሆኖ በራሱ ዘርፈ ብዙ ጥናት የሚያካሄድ መሆን አለበት፡፡ የመከላከያና የውስጥ ደኅንነት ጥናቶች፣ መረጃዎችና የአገሪቱ ከፍተኛ የትምህርትና የዲፕሎማሲያዊና ፕሮፌሽናል ተቋማትን ተጠቅሞ የውስጥም ሆነ የውጭ ሥጋቶችንና ዕድሎችን መሠረት አድርጎ የተለያዩ ቢጋር/ቢሆኖች (Scenarious) በማደራጀት፣ ለውሳኔ ወደ ካውንስሉ የሚያቀርብና ተግባራዊነቱን የሚከታተል ነው፡፡

የብሔራዊ ደኅንነት ካውንስል ይሁን ሴክሪታሪያት ተቀባይነትን (ውህደትን) አቅሙን በሚያረጋግጥበት መንገድ መዋቀር ይኖርበታል፡፡ ብሔራዊ ተዋጽኦ አገሪቱን የሚያንፀባርቅ፣ በተለምዶ ደኅንነት (ወታደራዊ ደኅንነት) የሚባሉትን ብቻ ሳይሆን ዋናው ሥጋት ድህነትና የዴሞክራሲ እጥረት በመሆኑ የኢኮኖሚያዊ፣ የማኅበራዊና የዴሞክራቲክ ተቋማትን ጭምር በማሳተፍ ውህደት የሚያረጋግጥ፣ በከፍተኛ ደረጃ ሁሉን አቀፍ ባለሙያዎችን (በተለይ ሴክሪታሪያቱ) መሠረት ያደረገ አቅም ፈጣሪ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህ ካውንስልና ሴክሪታሪያት በማናቸውም አደረጃጀት ሊተካ አይችልም፡፡ የመከላከያ ተቋም ዋናው ተልዕኮ አገሪቱን ከውጭ ጥቃት መከላከል ነው፡፡ የውስጥ ደኅንነት ክፍሉ በውስጥ ፀረ ኢትዮጵያና ሽብርተኛነትን ተከታትሎ የሚያድን እንጂ፣ አጠቃላይ ከድህነትና የዴሞክራሲ እጥረት የሚነሱት ሥጋቶችን ለመከታተል የተደራጀ አይደለም፡፡ ስለዚህም ይህ ቀዳዳ ካልተሞላ እስካሁን የከፈልነው ሳይበቃ ከውስጥም ከውጭም ለከፍተኛ ጥፋት ልንዳረግ እንችላለን፡፡

በጠንካራ ሴክሪታሪያት እየታገዘ የሚንቀሳቀስ ካውንስል መኖሩ ፖለቲካዊ ትርጉሙ ከፍተኛ ነው፡፡ የሲቪሎች አመራር (Civilian Administration) ወሳኝነት በመከላከያና የውስጥ ደኅንነት ክፍል የሚያረጋግጥበት መንገድ ጭምር ነው፡፡ የብሔራዊ ደኅንነት ካውንስሉ እንደተቋቋመ ይታወቃል፡፡ መሪነቱን እስከምን ድረስ እያረጋገጠ ነው? የሚለው በጥናት የሚታይ ነው፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ የሚመራ ቡድን በጣም ጥቂት አባላት ቢኖሩትም፣ የሴክሪታሪያት ሚና ለመጫወት ይችል ይሆን እንዴ? እያሉ የደኅንነት ባለሙያዎች ጥያቄዎች እያነሱ እያለ፣ በ2009 ዓ.ም. በተደረገው አዲስ የመንግሥት አደረጃጀት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማካሪዎች ቡድን ሲፈርስ የደኅንነት አማካሪ ቦታ በተለይ መልሶ ሳይደረግ ቀሩ፡፡ ከድጡ ወደ ማጡ ይሏል ይኼ ነው!

የጠራ የደኅንነት ፖሊሲ ባለመኖሩ፣ እንዲሁም ተቀባይነት፣ ውህደትና የፖሊሲ አቅም የተላበሰ የብሔራዊ ደኅንነት ካውንስልና ሴክሪታሪያት ባለመኖሩ በ1990 ብዙ ምልክቶች እያሉም የኤርትራ መንግሥት ስትራቴጂካዊ ድንገተኝነት አግኝቶ አገራችንን ወረረ፡፡ መጨረሻው በኢትዮጵያ አሸናፊነት (ከዚያ በላይ ድሉ ሊሰፋ ይችል ነበር ወይ? የሚለውን ለጊዜው ትተን በተለይ አሁን ካለው ‹ወይ ሰላም ወይ ጦርነት› ካለመኖር ጋር ተያይዞ) ቢረጋገጥም፣ የከፈልነው መስዕዋትነት በሰው ሕይወትም በንብረትም ከፍተኛ ነበር፡፡ ከዚህ በላይ አገራችን ተያይዛ ከነበረው የልማትና የዴሞክራሲ ግንባታ ለጥቂት ዓመታት ቢሆንም ያደረሰው ኪሳራ ከፍተኛ ነው፡፡ ከኤርትራም ሆነ ከሌሎች አገሮች ጋር የሚኖረን በፖሊሲ ለውጥ በአዋጅ እናጠናዋለን እየተባለ ሳይሆን፣ የካውንስሉ ሴክሪታሪያት ዋናውና በቀጣይነት የሚሠራ ነው መሆን የነበረበት፡፡ የ1994 ዓ.ም. ፖሊሲ ማሻሻል ከተፈለገ ጊዜያዊ ኮሚቴ በማቋቋም ሳይሆን፣ ከምንም ረቂቅ አዘጋጅቶ ለባለድርሻ አካላት ለውይይት ማቅረብ ይገባ ነበር፡፡ ያ ተቋም ወሳኝ ነው፡፡ የ2008 ዓ.ም. ግርግርና ጥፋት፣ እሱ ተከትሎ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድህነትና የዴሞክራሲ እጥረት አገራችንን ወደ መበታተን ሊያደርሱ የሚችሉ ወሳኝ ሥጋቶች ናቸው የሚለውን በተግባር ያሳየን ሁነት ነው፡፡ ኃይላችንን ሳንበታትን በእነሱ ላይ በመረባረብ የተረጋጋ ሰላም፣ የበለፀገችና ዴሞክራሲያዊት አገር እንገንባ፡፡ ይህን ለማድረግ በብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲና አመራሩ መግባባት ይፈጠር፡፡

በተለይ የዴሞክራሲያዊ ምኅዳር እየጠበበ መሄድ ከሁሉም በላይ የሚያሳስብ ነው፡፡ ምኅዳሩ የመጥበብ ጉዳይ የጥቂት ፓርቲዎች መሳተፍ አለመሳተፍ፣ የጥቂት ሰዎች የመጻፍና ያለመጻፍ ጉዳይ አይደለም፡፡ የሞት የሽረት ጉዳይ ነው፡፡ የዴሞክራሲ ምኅዳሩን እንዴት እናስፋው? ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥቱን ብቻ ማዕከል አድርገው እንዴት በተግባር ይዋሉ? የሥራ አስፈጻሚውን አምባገነንነት እንዴት እንቆጣጠር? ፓርቲ፣ መንግሥት (Government)፣ አገር (State) በተመለከተ የሚታየውን መዘባረቅ እንዴት እንቀንሰው? በአጠቃላይ ሕገ መንግሥታችን በፖለቲካው የበላይት የሚያገኝበት፣ ብሎም ግልጽነትና ተጠያቂነት የነገሠበት ምኅዳር ለማንገሥ መረባረብ ይኖርብናል፡፡ የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ትምክህትና ጠባብነት ከድህነትና ከዴሞክራሲያዊ እጥረት የሚመነጩ በፈጣን ዕድገትና ዴሞክራሲያዊ ግንባታ ብቻ የሚሸነፉ ናቸው፡፡

በተለይ ትምክህትና ጠባብነት የሚባሉ ጉዳዮች ዴሞክራሲን ማዕከል በማድረግ ካልታዩ አደገኞች ናቸው፡፡ የአመራሩ ራሱን ከተጠያቂነት ለማዳን የጎንዮሽ ግጭት (Horizontal Conflict) የማስፋትና የትችት ትኩረትን ወደ ውጭ የማዞር (Externalization) ሥልት ሊሆን ይችላል፡፡ ኅብረተሰቡ ወደ ላይ አንጋጦ በአመራሩ ያለውን ችግር እንደ ዋነኛ አድርጎ እንዳይረባረብ እርስ በርሱ እንዲገማገም ለማድረግ የታሰበ እንዳይሆን፡፡ እስኪ ይግረማችሁ አስተማሪ በሙያው ሳይሆን እርስ በርሱ በትምክህትና በጠባብነት ሲገመገም፣ ድስት ስታቁላላ ወጥ ያረረባት ሠራተኛ የማረሩ ምንጭ በትምክህትና በጠባብነት ምክንያቱ እየተፈለገ ነው፡፡ በኪራይ ሰብሳቢነት ሆነ በመልካም አስተዳደር ችግሮች ወይም በጠባብነትና በትምክህት በላይኛው አመራር ላይ ስለተወሰደ ዕርምጃ የምናውቀው የለም፡፡ የተሰጠን መልስ ማስረጃ የለም ነው፡፡ ፖለቲካዊ ሙስና ባለበት ሁኔታ የገንዘብ/ኢኮኖሚ ሙስና እንዴት ማስረጃ ሊገኝበት ይችላል?

በተለይ ጠባብነትና ትምክህት የሚባሉት የአጫፋሪ ቃላት አባዜ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እየታየ ያለውን የብርሃን ጭላንጭል እንዳይገድለው መጠንቀቅ ይገባናል፡፡ ብቃት ያለው ካቢኔ ለመመሥረት “የኢኮኖሚክ አብዮት” መጀመርና በራሱ ተማምኖ መወሰን (Assertiveness) የጠንካራ ክልላዊ መንግሥት ምልክት እያየን ነው፡፡ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ በቅርቡ ባላሀብቶችን ሰብስበው ሲያናግሩ፣ “የምንወስንባቸውና ልንወስንባቸው የማንችልባቸው ሥልጣኖች አሉን፣ የተገደበ ሥልጣን ነው ያለን፣ እኔ በግልባጭ አልወስንም፤” ብለው የፀና ፌዴራሊስት አቋማቸውን ገልጸዋል። ይበል የሚያስብል ነው። ጠንካራ የኦሮሞ ክልላዊ መንግሥት መኖር ለጠንካራ ኢትዮጵያ መሠረት ስለሆነ በጉድለቶቹ ላይ ተንተርሰን ደካማ ጎን እየፈለግን አናራግበው፡፡

ምክር ቤቶቻችን በትምክህትና በጠባብነት ምክንያት አልተሽመደመዱም፣ ፍትሕ የታጣው በትምክህትና በጠባብነት ምክንያት አይደለም፡፡ በ2008 ዓ.ም. የነበረው ተቃውሞ በዋናነት ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ ነው (ጠባብነትና ትምክህት ቢያጅበውም)፡፡ ወጣት ፖለቲካል ሳይንቲስቱ ናሁሰናይ በላይ አስገራሚ ሐሳብ አለው፡፡ እንዲህ ይላል፡፡ “በዲሞክራሲ ዕጦትና በኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳስብና ተግባር መካከል ያለው መስተጋብር ልክ እንደ ዝንብና ቆሻሻ አድርገህ ማየት ይቻላል፤›› ይላል፡፡ በመቀጠልም፣ ‹‹ቆሻሻ (የዴሞክራሲ እጥረቱ) በሌለበት አካባቢ አንድ ሁለት ዝንቦች (የኪራይ ሰብሳቢነት፣ ትምክህትና ጠባብነት አስተሳሰብና ተግባር) ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ድምፅ ካልሰማህ መኖራቸውን አታውቅም፡፡ ከዝንብ ነፃ የሆነ አካባቢ ያለህ ይመስልሃል፡፡ ከፍተኛ ቆሻሻ በሚከማችበት ግን የዝንብ መዓት አያስቀምጥህም፤›› በማለት የሁለቱን ምክንያታዊ ጥምረት ያብራራል፡፡ በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ረገድ ችግር በሚኖርበት ጊዜ እነዚህ ለግል ጥቅማቸው የሚሯሯጡ ልሂቃን ያለምንም ከልካይ ወይም ሃይ ባይ ወለል ያለ ሜዳ ስለሚያገኙ እንደፈለጉ ይጋልቡበታል ማለት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ሁኔታዎች ሁሉ አደገኛ ይሆናሉ፡፡ መፍትሔውም ዝንቦች (የኪራይ ሰብሳቢነት፣ ትምክህትና ጠባብነት) ከማስወገድ በላይ፣ ቆሻሻውን ማስወገድ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ማለት ነው፡፡ ፀረ ዴሞክራቲክ አስተዳደር የሚባል ቆሻሻ፡፡

ማጠቃለያ

አገራችን የገጠማት ችግር ተራ ፖለቲካዊ ቀውስ ሳይሆን፣ እንደ አገር ቆሞ የመቀጠልን ሥጋት የጋረጠ ከፍተኛ የደኅንነት አደጋ መሆኑን ዓይተናል። ለዚህም ሲባል አገራዊ ችግራችን በአገራዊ መግባባት መፍታት ካለብን፣ መወያያትና መነጋገር ያለብን ከሕገ መንግሥቱ በታች የፖሊሲዎች ቁንጮ በሆነው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ (ኢውጉብደፓ) ዙርያ ነው፡፡ ገዥው ፓርቲም ጥልቅ ተሃድሶ ሲል የፓርቲ ተሃድሶ ነው? ወይስ የመንግሥታዊ መዋቅር ተሃድሶ? የሚባለውን በቅጡ ለይቶ መንቀሳቀስ አለበት። የደኅንነታችን ዋና የሥጋትም የኩራትም ምንጭ ውስጣዊ የዴሞክራሲና የልማት ሁኔታ መሆኑ በመገንዘብ፣ የችግሩን ሥረ መሠረት ትቶ አጫፋሪ በሆኑ ትምክህት፣ ጥበት፣ አክራሪነት በሚባሉ ቅርንጫፎች ላይ ተንጠላጥሎ የሚመጣ ለውጥ ሊኖር እንደማይችል መረዳት አለበት። እያጠናሁት ነው የሚለው የፖሊሲ ክለሳም ሆነ ጥልቅ ተሃድሶ የአገሪቱን መሠረታዊ ችግር የሆነውን የድህንነት ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ አካሄድ መከተል አለበት። ይዘቱ ብቻ ሳይሆን ሒደቱም ለአገራዊ መግባባት ወሳኝ ነው፡፡ የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ያሉንን አቅሞች አሟጦ፣ ድህነትና የዴሞክራሲ እጥረት እንደ ዋነኛ የውስጥ ሥጋት አድርጎ፣ አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት እንዴት የአገራችን ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ እናረጋገጥ? የሚለው አጥንትና ሥጋ ከደም ጋር አዋህዶ የሚያስተማምን ፖሊሲ መቅረፅ የግድ ነው፡፡ ፖሊሲው በኢሕአዴግና በኢሕአዴግ ዙሪያ ባሉት ሰዎች ብቻ ተረቆና ውይይት ተደርጎበት መፅደቅ የለበትም፡፡ የፖለቲካዊ ፓርቲዎች፣ የሲቪልና የሙያ ማኅበራት፣ የክልል ምክር ቤቶች፣ ወዘተ. ተሳትፎና የተለያዩ አስተያየቶች ተጨምሮበት መሆን ይገባዋል፡፡ ባይሳካም ደቡብ ሱዳንን በተመለከተ ከጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ የሰማሁትን ላካፍላችሁ፡፡

የብሔራዊ ደኅንነት ፖሊሲ ለማርቀቅ አንድ ኮሚቴ ተቋቋመ፡፡ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች ተሰጠው፡፡ በመጀመርያ ረቂቅ ተዘጋጀ፡፡ ከፖለቲካዊ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ተደረገበት፡፡ ከዚያም ወደ አሥሩ ክልሎች ኮሚቴው ተሰማርቶ፣ የየክልል ሕገ አውጭንና ሕግ አስፈጻሚውና ሲቪል ማኅበረሰቡ የመጀመርያው ረቂቅ ቀርቦለት ለየብቻ ሰፋፊ ውይይት ተደረገበት፡፡ ብዙ ግብዓት ተገኘበት፡፡ ኮሚቴውም ግብረ መልሶችን እንደ ግብዓት በሚገባ አሰባሰበ እንደገና መሥራት ጀመረ፡፡ ይዘቱም ዳበረ፡፡ በመሀል ግርግሩ ተፈጠረ፡፡ ከሁሉም በላይ ግን የኅብረተሰብ ወኪሎች በስፋት መሳተፋቸው የፈጠረው የእኔነት ስሜት በብሰባው ይታይ ነበር፡፡ ውጤቱን ለማየት አልታደሉም፡፡

ኢውጉብደፓ ከውጭ ወደ ውስጥ ይመለከት የነበረው የደኅንነት አስተሳሰብ በግልጽ አሳይቶታል፡፡ አልቀጠለበትም እንጂ፡፡ አሁንም ስላልረፈደ አሳታፊ በሆነ መንገድ ሁሉም ኃይሎች የሚሳተፉበትና የእኔነት ስሜት በሚፈጥር መንገድ ዴሞክራሲና ፈጣን ልማት የዋስትናችን መሠረቶች መሆናቸው በተግባር መግባባት ግድ የሆነበት ሰዓት ላይ መድረሳችን ታውቆ፣ ዕርምጃችን በዚህ ቅኝት ቢሆን መልካም ነው እያልኩ ጽሑፌን በዚህ ልቋጨው።

posted tigi flate

 

አገር የሚያፈርስ ማን ነው? – የጉድ ሐገር

(ከአቶ ግርማ ሰይፉ ገፅ የተገኘ አሳዛኝ መረጃ)

ዛሬ ጠዋት ከቤቴ ወጥቼ ልጆች ትምህርት ቤት ካደረሰኩ በኋላ የተገኘሁት ቦሌ ክፍለ ከተማ ዐቃቢ ህግ ቢሮ ነበር፡፡ አብሮኝ የሸዋስ አሰፋ ነበር፡፡ ያጎደልኩት ካለ ይጨምርበታል፡፡ የተጋነነ የለውም፡፡ የሄድንበት ምክንያት ወደጆቻችን ኤሊያስ ገብሩ እና ዳንኤል ሸበሺ ለረጅም ጊዜ በእስር በመቆየታቸው ፋይላቸው በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጉዳያቸውን እየተመለከተው ይገኛል ከሚባለው ዐቃቢ ህግ ሃላፊ ጋር ለመነጋገር ነበር፡፡ ሃላፊው አቶ ዘለቀ ይባላል፡፡ ጠዋት ከቢሮ ብንገኝም አቶ ዘለቀ ለአራት አስር ጉዳይ ሲል ወደ ቢሮ ገቡ፡፡ ማርፈዳቸው ቢገባቸው ብዬ ይቅርታ ገና ከመግባቶ የመጣነው ውጭ ትንሽ ሽለቆየን ነው በማለት ሰላምታ ተለዋወጥን፡፡ ማርፈዳቸው ምንም ግድ አልሰጣቸውም፡፡ ያለምንም ቢሮክራሲ ቢሮ ገብተን ማናገር ጀመርን፡፡ ምንም ቢሮክራሲ የማያውቁት አቶ ዘለቀ ላቀረብንላቸው ጥያቄዎችም አንድም የሲቪል ሰርቪል ደንብና ህግ፣ የአገልጋይነ መንፈስ የለባቸውም፡፡ ዐቃቢ ህግ የሚለው ነገር ትርጉም ካልተቀየረ በስተቀር ለህግ ልዕልና የሚቆም ባለሞያ የሚሰጠው ስለ ሰው ልጅ ስብዓዊ መብት ግድ የሚሰጣቸው ሆኖ አላገኘኋቸውም፡፡ ዝርዝሩን ልነግራችሁ አልችልም ብዙ ነው፡፡ ለማሳያ ያክል ላካፍላችሁ፡፡

ለአቶ ዘለቀ የመጣንብተን ጉዳይ አስረዳናቸው፡፡ እነዚህ ልጆች በእስር ስድስት ወር ሊሞላቸው ነው፡፡ ወይ ፍርድ ቤት አልቀረቡም፤ ወይም እንደሌሎች ስልጠና ወስደው አልተለቀቁ እና ጉዳያቸው ምን እንደደረሰ ለማወቅ እና አፋጣኝ መፍትሔ እንዲያገኙ እንዲያግዙን ነው፡፡ አልኳቸው፡፡ የአቶ ዘለቀ መልስ “ለምን ይፈጥናል እነዚህ እኮ ሀገር ሊያፈርሱ የነበሩ ናቸው፡፡” ብለው በግል ጠብ ያላቸው የሚያስመስል ነገር ነገሩኝ፡፡ እነርሱ ባስነሱት ጦስ “ሀገር ልትፈርስ ለጥቂት ነው የዳነችው” ብለውኝ አረፉት፡፡ አለቆቻቸው የሲኒ ማዕበል ነው ሲሉ እርሳቸው ደግሞ ሀገር ልትፈርስ ለጥቂት መዳኗን፣ የዳነችውም እነ ኤሊያስ ገብሩ በመታሰራቸው እንደሆነ እና አገር የሚፈርሰው እነዚህ ልጆ በፌስ ቡክ ላይ በሚለጥፉት ፅሁፍ መሆኑ ገረመኝ፡፡ አቶ ዘለቀን አግባብቶ ወደ ቁም ነገሩ ለመውሰድ ብዬ፡፡ መቼም ይህ የሚነግሩኝ ጉዳይ ለጫወታ ሊሆን ይችላል፤ እነዚህ ልጆች ጥፋተኛ ከሆኑም ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሰጥ ፋይላቸው ፍርድ ቤት መቼ እንደሚቀርብ ማወቅ ፈልገን ነው የመጣነው አልናቸው፡፡ “ምን ያሰቸኩላል እያጣራን ነው ስንጨርስ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡” አሉን፡፡ በዚህ መሃክል ቤተሰብ ይፈርሳል፣ ጥፋተኛ ካልሆኑ ደግሞ ፍትህ ይዛባል ሰለዚህ እንዲፋጠን የፈለግ ነው ለዚህ ነው ብለን ሃሳባችንን ሳንጨርስ፤ “ይፍረሳ (ቤተሰቡ ማለታቸው ነው)፤ እነርሱ አኮ ሀገር ለማፍረስ እንጨት ይዘው ሲጎረጉሩ ነበር፡፡” በማለት ሀገር የሰጋቱራ ክምር ይመስል በእንጨት ጉርጎራ የምትፈረስ አደረጉና ግራ አጋቡን፡፡ አቶ ዘለቀ ሀገር እኮ የቤተሰብ ድምር ነው ብዬ ጣልቃ ስገባ፤ “እሱን አላጣሁትም፣ አገር ከሚፈርስ ግን አንድ ቤተሰብ ቢፈርስ ችግር የለውም ነው የምልህ፡፡” ብለው አስረግጠው ደገሙልኝ፡፡

ተመሳሳይ መልሶችን ለሌሎችም እንደሰጡ ተረድቻለሁ፡፡ እነዚህ ልጆች በጣቢያ በእስር ቤት ውስጥ ሆነው ሁሉ የሚሰሩትን እንደሚያውቁ፤ በኢሣት እና በቪኦኤ በፌስ ቡክ ስለነሱ ብቻ እንደሚወራ እንደሚያውቁ፤ መግለጫ ሰጡን፡፡ ይህን ፅሁፍ የፃፍኩትም አንባቢ ከእነ ኤሊያስ እና ከአቶ ዘለቀ አገር የሚያፈርስ ማን ነው? ብዬ ለመጠየቅ ነው፡፡ ለረጅም ጊዜ በመንግሰት መስሪያ ቤት አገልግያለሁ፣ በዚህ ደረጃ ለተገልጋይ መልስ የሚሰጥ በኃላፊነት ደረጃ ያለ ሰው ገጥሞኝ አያውቅም፡፡ በዚህ ደረጃ ሃላፊነት ያለበት ሰው የተጠየቀውን ጥያቄ የግል ሰሜቱን ዋጥ አድርጎ የስራ ሂደቱን በመንገር መረጃ ከመስጠት ሃልፎ አንድን ቤተሰብ ቢፈርስ ግድ እንደማይሰጠው ሲነግረኝ መስማት ያሳምማል፡፡ አንድ መስሪያ ቤት የያዘውን ጉዳይ መቼ ጀምሮ መቼ እንደሚጨርስ የሚቀመጥ ጊዜ በመኖሩ ይህ ጊዜ ካልተቻለ ደግሞ ምክንያቶች መግለፅ እንደሚቻል ማንም ያውቃል፡፡

ለማነኛውም በእኔ እምነት ይህች አገር የምትፈረሰው ኤልያስና ዳንኤል ፅፈው በሚለጥፉት መልዕክት ክፋትና መጥፎነት ሳይሆን የመንግሰት የሃላፊነት ቦታዎች በተለይ ደግሞ በህግ ሊመሩ የሚገባቸው ዓቃቢ ህጎች ዓቃቢ ፖለቲካ ከሞያቸው ይልቅ ካድሬነታቸው ሲያመዝን ነው፡፡ እነ ዘለቀ የጥልቅ ተሃድሶ ውጤት ከሆኑ፣ የወረድንበትን ዝቅጠት ጥልቅነት ለመገንዘብ ይቻላል፡፡ የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት አሠጣጥ እዚህ ደረጃ መውረዱ ያሳዝናል፡፡ በፌስ ቡክ ስለ እነ ኤሊያስ ብቻ ይወራል ያሉት አቶ ዘለቀ ደስ ይበላቸው ይኽው ስለ እርሳቸውም አወራን፡፡

posted tigi flate