ተቦርነ በየነ “አንተ አልክ?” – ቴዲ አፍሮን ክንፉ አሰፋ

እንዲህም ሆነ። የይሁዳ ገዥ የነበረው ጲላጦስ ክርስቶስን አስጠርቶ “አንተ የአይሁድ ንጉስ ነህን?” ሲል ጠየቀው። ክርስቶስም መልሶ “አንተ አልክ?”  አለው። ሰማይን ያለ ምሰሶ ያቆመው ክርስቶስ “ጥፋ” የምትል ቃል ብቻ ከአንደበቱ ቢያወጣ ኖሮ ፒላጦስ አይደለም መላው ቂሳር ክምድረ-ገጽ በጠፉ ነበር።

ታዋቂዎች በአዋቂዎች ላይ የሚቀልዱበት ይህ የገሃዱ አለም እውነታ ግብረ-ገብ ወደ ግብግብ በተቀየረበት በዚህ ዘመን ባሰበት እንጂ አልጠፋም። ጥንት አንቺ-ትብሽ ፣አንተ-ትብስ ይባል የነበረው ብሂል አሁን በ”አንቺ ብስብስ አንተ ብስብስ” ተቀይሯል ሲል አንዱ አጫወተኝ። ከቶውንም ስድብን እንደ ስንቅ በከረጢት ቋጥረው በሚጓዙበት የፌስ ቡክ ዘመን መስመር የመልቀቁ ነገር አዲስ ሊሆን አይችልም።  “አንተ አልክ?” ብሎ ማለፍ ምን ይጎዳል?

ብላቴናው ላይ አንዳች እንከን ሲያጡ፣ የጠወለገን የጥላቻ ህያሴ ለማንጠባጠብ የሚሞክሩትን እንዲህ ማለቱ ይበጅ ይመስላል፤ “አንተ አልክ?”። እንግሊዞች “Cover before you discover”  ይላሉ። “አወቅኩ ከማለትህ በፊት፣ እወቅ” እንደማለት ነው። በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አንደራደረም ከሚሉ ወገኖች ያልሆኑትን- እነሱ ልንላቸው ነው።   ከእኛ ሳይሆን ይልቁንም ከነሱ ወገን፣  አንገት አርዝመው፤ ምላስ አሹለው የቴዲን ስራ ለማጣጣል ብቅ ያሉ  ሃያሲ ተብየዎች ግራ ቢገባቸው፣ “ቴዲ ስለ አባይ ስላልዘፈነ ግብጻዊ ነው” ሲሉ አስደምመውናል።  “ህዝቤ እውቀት ከማጣት የተነሳ ጠፍቷል” ይላል ቃሉ።  “ስለ አባይ ስላልተቃኘ ግብጻዊ ነው!” የሚለውን የድንቁርና ዝባዝንኬ ሲቀባጣጥሩ፣  የ”ፈለገ ግዮን” ምስጢራዊ ቅኝት ሊገባቸው አይችልምና እንደነዚህ አይነቱን ለማስረዳት መጣር ግዜ ማባከን ይሆናል።  አባይ  የወንዞች ሁሉ ታላቅና ንጉስ ስለሆነ፣ በታላቁ መጽሃፍ ፈለገ-ግዮን በሚል ስም ይጠራል።

እርግጥ ነው። ቴዲ አባይን ያየበት መንገድ ከባህላዊው ቅኝት ትንሽ ለየት ይላል። ስለ አባይ ያነሳው ቅኝት ለጸጸት፣ ለቁጭት እና ለፕሮፓጋንዳ ከተነሱት ዘፋኞች ሁሉ የላቀ ነው። ስለ አባይ ብዙ ተዘፍኗል። አንዳንዶች ግጥምን ከጉልት እንደሚሸመት ሸቀጥ እየገዙ አዚመውታል።  ይኽኛው ከነዚያ ስራዎች ጋር የሚነጻጸር አይደለም። በረቀቀ መልኩ “…ፈለገ ግዮን ያንቺ ስም ሲጠራ” ሲል በእናትነት፤ ከፍ ሲል ደግሞ ከሃገር ጋር አቆራኝቶ ተቃኝቶለታል።

ስለ ወዳጃችን ተወልደ/ተቦርነ በየነ የከተፋ ወግ ከመግባቴ በፊት በቴዲ አምስተኛው የአልበም ስራ የተሰማኝን ልግለጽ። አትሌት ሃይሌ ገብረ ስላሴ ይህንን ስራ በአንድ መስመር ሲያስቀምጠው፣ “እኔ ማለት ምችለው ቴድሮስ ካሳሁን / ቴዲ አፍሮ / ዘፋኝ ብቻ ሳይሆን የጠፋውን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የመለሰ ልብ አስታራቂ ልጅ ነው።” በማለት ነበር።

የሃይሌ ገብረስላሴን ገጽ ያነበበ ሁሉ በእርግጥ “የኢትዮጵያዊነት መንፈስ” ጠፍቶ ኖሯል የሚል ጥያቄ ማንሳቱ አይደንቅም። የኢትዮጵያን ባንድራ እያውለበለቡ ስምዋን በአለም መድረክ የሚያስጠሩም ሳይቀሩ ኢዮጵያዊነታቸው በሰላቢዎች ተሸልቶ የበጠፋበት ግዜ መሆኑ ግን ያስደነግጣል። በእናት እየመሰለ የተቀኘላት ይህች ሃገር የሚያቆስሏት እንጂ የሚቆስሉላት በጠፉ ግዜ፣ የሚጮሁባት ሳይሆን የሚጮሁላት በመነመኑበት ግዜ፣ በድብቅ ሳይሆን በገሃድ የ”እናፍርሳት” አፈርሳታ የሚዶልቱ በበዙበት በዚህ ዘመን፣ እናቱን ከነ ችግርዋ የሚወድዳት፣ በሲቃና በደስታ መሃል የተቀኘላት የጠላት፣ የሚጠላትን ደግሞ በድፍረት የሚረግም ጀግና ብቻ ነው።

ከ”ሰምበሬ” …እስከ “ናት ባሮ”  እናትን እናይበታለን፤ ከቴዎድሮስ እስከ አደይ ኢትዮጵያን እንቃኝበታለን።

“አደይ”ን እያሰማን ከመረብ ወንዝ በላይና ታች አድርጎ ታቹን በጀግናው አጼ ቴዎድሮስ ወደ ጎንደር ያስገባናል፤ ከዚያም “ማሬ” እያለ በጎጃም አውርዶ ወሎ እና ሸዋ ላይ ያወጣናል።  “ኦላን ይዞ” እያለን ወደ ደቡብ ይወስደንና “በአና ኛቱ” ምስራቅንና ምእራብን ያስጎበኘናል።  በሙዚቃው ቅኝት ኢትዮጵያን ከጫፍ እስከጫፍ የማስጎብኘት ጥበብን መሰለኝ ሃይሌ ለማንሳት የፈለገው።  ይህ የድምጻዊነት ደረጃውን ጣራ ያደረሰው ብቻ ሳይሆን፣ የተነጠቀን ኢትዮጵያዊነት የማስመለስ ምትሃት ይመስላል። ይህ ስራ በውቀት ሚዛን ላይ ሲቀመጥ ልቆ የሚገኝ ስለመሆኑ ሚሊዮኖች መስክረዋል። ሚሊዮኖች  “ኢትዮጵያ” እያሉ አብደዋል።

የቴዲ ስኬት ያሳበዳቸውም አልጠፉም።

አንድን ስራ ስነ ምግባር መተሞላ መልኩ መተትች አንድ ነገር ነው። በሙያው የተካኑ ይህንን ቅንብር ቢተቹ ጥቅም እንጂ ጉዳት አይኖረውም። ከግል ጥላቻ ብቻ ተነስቶ ይህንን ድንቅ ስራ ጥላሸት ለመቀባት መሞከር ደግሞ ሌላ ነገር ነው። ስኬቱ ያበገናቸው ሁሉ ዘልለው የማይይዙትን ተራራ ለመንካት ከቁመታቸው በላይ መንጠራራትን ይዘዋል።

ተቦርነ በየነ የኢሳት ራዲዮ ላይ ስለ “መተቸት መብት” ይናገራል። መብትም እኮ “መብት” ስለሆነ ብቻ ፋይዳ አለው ማለት አይደለም። አጋጣሚ እየፈለጉ እንደ Crusades የማያቋርጥ ማጥላላትን በአንድ ብላቴና ላይ ማናፈስ ግን መብት አይደለም፣ ፍጹም ጭፍን የሆነ ጥላቻ እንጂ። ጥላቻና ማን-አለብኝነት ደግሞ የደካማነት እንጂ የጥንካሬ ምልክት አይደለም። ለሃገር ቆምኩ የሚል ሰው በሃገር ጉዳይ ላይ አይደራደርም።  ለነገሩ እንጂ “ሺ ዝንብ መሶብ አይከፍትም” እንዲሉ፣  እነዚህን በእውቀት እና በጥበብ ከፍታ ላይ የተሰሩ ስራዎች የማውረድ አቅም ያለው ሊኖር አይችልም።

ይህች ሀገር አሽቃባጭ እና ጥሩምባ ነፊ አላጣችም።  ሊያጠፉዋት የሚዶልቱትን እንኳ ሳይቀር በአንዲት ዜማ ማስመለስ የሚችሉ፣ ከችሎታው በላይ ደግሞ ዝምታን ደፍረው የሚሰብሩ ናቸው ኢትዮጵያ የሚያስፈልጉዋት።  ይህንን ቴዲ ሲያደርግ አልጋ ባልጋ ሆኖ አይደለም። ከሚነደው እሳት ጥግ ሆኖ ወላፈኑ እየገረፈው ይህንን አደረገ። ከውጭ ሆናችሁ ሌላ እሳት መለኮስ የምትሹ ሁሉ፤ እባካችሁ ተወት። ወላፈኑ ይበቃዋል።

ተወልደ/ተቦርነ በየነ በቴዲ ስራዎች ላይ ያሻውን የማለት መብት አለው። በአመክንዮ ሳይሆን በጥላቻ ስራውን ለማጥላላት እንደሚሞክረው OMN ቲዩብ ማለት ነው።  ተቦርነ ቲዩብ ብሎ መልቀቅም ይችላል። ኢሳትን ምርኩዝ አድርጎ ሲሰራው ግን የ”ትችቱ” ትርጉም ይቀየራል። “ቀላል ይሆናል” ይላል ቴዲ – ነገሮች መስመር ሲስቱ። ይህ ዘመቻ-  የ”ሙዚቃ ሃያሲ”ው ትራስ እያደረገ የሚነሳበት ተቋም ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ ግን “ቀላል አይሆንም”። የኢትዮጵያን ማልያ ለብሶ ለ OMN መጫወት ይመስላል። አንድ ግለሰብ ከሚሊዮኖች ጋር ለመላተም ከቶውንም አይደፍርም። አእምሮውን ቆልፎ ይህንን ድፍረት የሚሰጠው ትራስ ካልተማመነ በስተቀር።… አካሄዱ “ሹሩባ ልትሰራ ሄዳ ጠጉሩዋን ተላጭታ መጣች”  እንዳይሆን ነገሩ የገባው ሁሉ ይወቅበት።

አዎ ቴዲ ስለጎንደር የተቃኘውን ስራ “የይርጋ ዱባለ ሰራ ነው” ሲል ተቦርነ አሹፎበታል። “የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ” እንዲሉ ከዚህ ቀደም እንደሚለው “ለምን ይዋሻል”ን አልጨመረበትም እንጂ ሙዚቃው ከሌላ ድምጻዊ እንደተወሰደ በድፍረት ተናግሯል። በኢሳት ራዲዮ  የተናገረው ቃል በቃል እንዲህ ይላል።

“በቴዎድሮስ ካሳሁን አዲሱ ኢትዮጵያ የሚዚቃ አልበም ውስጥ የአንጋፋውን የባህል ድምጻዊ የይርጋ ዱባለን ጎንደር የተሰኘ ስራ ጨምሮ 14 ያህል የሙዚቃ ስራዎች ተካትተዋል።”

ከዚያም ይደግምና “ከአንጋፋው ይርጋ ዱባለ ጎንደር የተሰኘው ስራ ውጭ ሌሎች አስራ ሶስት የሙዚቃ ስራዎች ግጥም እና ዜማ ድርሰቶች የድምጻዊ  የቴዎድሮስ ካሳሁን ናቸው።” ይለናል።

አልበሙ ላይ የምናየው የዚህ ስራ ግጥም ጸሃፊ “በቴዎድሮስ ካሳሁን” ይላል። በዜማው ላይ ጎንደርኛ  ቅኝት የቀባበት መሆኑንም በግልጽ አስቀምጦታል።   ቴዲ በጠራራ ጸሃይ ሊዋሽ እንደማይችል ግልጽ ነው።  ለከተፋው ይህ ስራ የተመረጠበት ምክንያትም፣ ሙዚቃው በህዝብ ልብ ውስጥ እጅግ ዘልቆ መግባቱ ይመስላል።

የሚደንቀው ደግሞ የቴዲን አልበም ሽያጭ ለማኮሰስ ሲል የተጠቀመበት የንጽፅር መነጽሩ ነው። የአልበም ሽያጭ ሰልፉን ከሌሎች ድምጻውያን ሰልፎች ጋር ለማወዳደር የሞከረበት መንገድ ቴዲን ሳይሆን ይልቁንም አድማጩን ሕዝብ የመስደብ ያህል ነው። ከጅምሩ ይህ አልበም ከሌሎች ድምጻውያን አልበም ጋር  ለንፅፅር መቅረብም የለበትም።  በሚሊዮን አይደለም በመቶ ሺዎች ያሳተመ ድምጻዊ በኢትዮጵያ ታሪክ አልነበረም፣  የሚዚውቃ ሲዲ እንደ ቀበሌ ስኳር በሰልፍ እና በሽሚያ የተገዛበት አጋጣሚም የለም፤ አዟሪዎች ሲዲን በእጥፍ የሽጡበት ወቅት አላየንም። እስከዛሬ በማንም ድምፃውያን ያልተከሰተን ነገር ነው ለንፅፅር ሊያቀርብ የሞከረው።

ለወንድሜ ተቦርነ የምለው አንድ ነገር ብቻ ነው። ልቦና ይስጥህ። በጥላቻ እና በትችት መሃል ያለን ልዩነት መቀበል እና ማመን ይገባሃል። ጥላቻ ደግሞ እንዲሁ አይመጣም። ምክንያቶች አሉት። ግላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ባህላዊ እና ማህበራዊ ምክንያቶች። ጥላቸው ከየትም ይምጣ ከየት – ግን አንድ የምመክረው

ነገር አለ። አበው እንደሚመክሩት “ቆዳ ሲወደድ በሬህን እረድ።”  እጅህን ከቴዲ አንሳ!

posted tigi flate

Advertisements

አብዮታዊ ዲሞክረሲ… የማያቋርጥ ሰቆቃ እንቅስቃሴ – ታሪኩ አባዳማ

ሐምሌ 2008

ቃላት ይናገራሉ ፣ ተፈጥሮን ይገልፃሉ ፣ የሀሳብን ጥልቀት እና የጉዞን አቅጣጫ ያመለክታሉ — አብዮታዊ ሆኖ ዲሞክረሲያዊ – ሁለት ሸጋ ቃላት ፣ ሁለት ተፃራሪ የፖለቲካ ንግድ ማራመጃ ማድመቂያ ቃላት። ሁለተኛውን ቢጥሉት ሌላው ቀዳሚውን ራቁት ያስቀራል – ስለዚህ አብዮት የሚለውን ቃል ዲሞክረሲ የሚሉት ካባ ያጠልቁለታል – ተኩላን የበግ ለምድ አልብሶ ከበግ መንጋ እንደ መቀላቀል…

አብዮት ሲሉ የነበረውን እንዳልነበር አድርጎ መቀየር ማለት ነው። የነበረው እንዳልነበር የሚሆነው ህብረተሰብ ነው ፣ አገር ነው ፣ ህዝብ ነው… አብዮት በተመሰቃቀለ እና ህገ ወጥ በሆነ እርምጃ ስልጣን መቆጣጠር ማለትም ነው። አብዮት ግርግር ነው ፣ ምስቅልቅል ነው። የታመቀ ብሶት ገንፍሎ ግድቡን በመጣስ በስልጣን ላይ ያለውን አፋኝ ስርአት ሲያጥለቀልቀው ፣ ሲውጠው ፣ ሲሽረው አብዮት ተካሄደ ይባላል። አብዮት እንደ እሳተ ገሞራ ነው…

የታመቀ እሳተ ገሞራ ይፈነዳል ፣ ያካባቢውን መልክአ ምድር ይቀይራል – ሜዳው ኮረብታ ይሆናል ፣ ጫካው በድንጋይ ቋጥኞች ይተካል ፣ ሸንተረር እና ገደል ይፈጠራል… እሳተ ገሞራ የሚፈነዳው አንዴ ነው ፣ እዚያው ከደገመም ጉልበቱ ሀይሉ እንደ መጀመሪያው አይሆንም – ተነፈስ ብሏላ። የታመቀው እቶን ተንፈስ ሲል እሳቱ ይጠፋል ፣ አፈሩ ይቀዘቅዛል – አዲስ የተከሰተው መልካ ምድር የተፈጥሮን ህግ ተከትሎ ኡደቱን ይቀጥላል… የእፅዋት አእዋፍ ዘር ይራባበታል – የሰው ዘር ይሰፍርበታል… ይረጋጋል።

እንደ እሳተ ገሞራው ሁሉ አብዮት የሚፈጥረው ምስቅልቅል ካንድ እርከን ላይ ሲደርስ መገታት አለበት። ህብረተሰቡ ሲመሰቃቀል መኖር ፈልጎ አብዮት አያቀጣጥልም – እርጋታ ይፈልጋል ፣ ህግ ይፈልጋል ፣ ስርአት ባለው እና በረጋ ግንኙነት ህይወቱን መቀጠል ይሻል። የወያኔን አብዮታዊ ዲሞክረሲ ሰነድ በጥሞና ከፈተሻችሁት ግን መሬት ላይ በህዝብ ላይ የሚፈፅመውን ያላቋረጠ ግፍ ስታጤኑ አብዮት ልጓም የሌለው የማይዳፈን የማያቋርጥ ምስቅልቅል መፍጠር ማለት ሆኗል።

ይህ እንዲሆን አስገዳጅ የሆነው ዋንኛው ሰበብ የወያኔ የራሱ ተፈጥሮ ነው። የዘረኝነት ተፈጥሮ ፣ ሌላውን አግልሎ በግል እና ጠባብ አመለካከት ላይ የተመሰረተ አገዛዝ ብሎም በዚያ ጎዳና ገደብ የለሽ ዘረፋ እና ግድያ ማራመድ። ተፈጥሯቸውን ‘አብዮታዊ’ እናም ደግሞ ለምድ አጥልቀው ‘ዲሞክረሲ’ ብለውታል። ተፈጥሯቸው ዘረኛ ስለሆነ ዘረ ብዙ በሆነቸው አገር ውስጥ ተረጋግተው ስልጣናቸውን ማቆየት አይችሉም። ስለዚህ ሁሌም እንደባነኑ ፣ ሁሌም እንደደነበሩ ፣ ከራሳቸው ዘር በስተቀር ሁሉንም እንደጠረጠሩ ፣ እንደገነፈሉ ይኖራሉ። ተፈጥሯቸው ለተረጋጋ ህይወት ዋስትና አይሆንም – በመደናበር እና በማደናበር በሚያሰፍኑት ምስቅልቅል ውስጥ ዕድሜያቸውን ማራዘም ግባቸው ነው። ያንን ነው አብዮት የሚሉት…

ግርግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ በፈጠሩት የማያቋርጥ የምስቅልቅል እንቅስቃሴ ውስጥ ገደብ የለሽ ሀብት ዘረፋ ያካሂዳሉ። ግርግር ከሌለ ፣ አብዮት ከሌለ ዘረፋ ማካሄድ አይቻልም… አገር ከረጋ ፣ ህግ የበላይ ይሁን ከተባለ ፣ ተጠያቂነት እና ግልፅነት ይረጋጋጥ ከተባለ ዘረፋ (ኪራይ ሰብሳቢነት ይሉታል) ይቆማል። ሰው በዘሩ ሳይሆን በብቃቱ እና ችሎታው ይመዘናል። ይህ መልካም የግርግር ዘመን ከሰከነ ያግበሰበሱት እና የሚያገበሰብሱት ሀብት ብቻ ሳይሆን ህልውናቸውም ፈተና ላይ ይወድቃል። አብዮት የማያቋርጥ እንቅስቃሴ ፣ የማያቋርጥ ግርግር ነው… እናም ያገሪቱን ጥሬ የተፈጥሮ ሀብት ላገኙት የባዕድ ቱጃር ይቸበችባሉ – ይጣደፋሉ ፣ ፋታ የላቸውም ሩጫው ከጊዜ ጋር ነው – እንቅስቃሴው ፈጣን ነው…

እስከ አሁን ድረስ ድሀው ህዘብ ላይ የሚዘንበውን የግፍ ውርጅብኝ ፣ ማፈናቀሉን ፣ ወህኒ ማጎሩን ፣ ቶርቸሩን ፣ አሸባሪ ብለው ያገቱትን ዜጋ ጥፍር እየነቀሉ ማሰቃየቱን… አረ ስንቱን… አስተውሉ… በማያቋርጠው አብዮታዊ እንቅስቃሴ የሚለበለው ዜጋ መድረሻ ጠፍቶት መፈጠሩን ከሚረግምበት ደረጃ ደርሷል። ወያኔዎቹ እያመሰቃቀሉ ፣ እያደናገሩ ፣ እያፈናቀሉ ፣ ወህኒ እያጎሩ ፣ እየገደሉ ካልሆነ አንድ ጀምበር ማደር አይቻላቸውም። ያንን የማያቋርጥ ምስቅልቅል ፣ ያንን የማያባራ ግርግር በዲሞክረሲ ለምድ ጀቡነውታል – መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ… አብዮታዊ ዲሞክረሲ ብለውታል። ‘አብዮት የማያቋርጥ እንቅስቃሴ ነው…’ የማያቋርጥ ምስቅልቅል

አብዮታዊ ዲሞክረሲ – ወያኔ ሁለቱንም ቃላት ይወዳቸዋል። እንቅስቃሴውን የሚመሩት ዘረኛ ነብሰ በላዎች የብሔረሰቦች ተቆርቋሪ እና ጠበቃ ያውም አብዮተኞች መሆናቸውን ይሰብካሉ። ለሚፈፅሙት ማናቸውም ወንጀል የሚጠየቁት በህግ ሳይሆን በአብዮታዊ ሂስ ብቻ ነው – አብዮተኞች ስለሆኑ ከህግ በላይ ናቸው። አብዮተኞች ስለሆኑ በፈለጉት ያገሪቱ ክልል ያሻቸውን ዜጋ ማሰር ፣ መግደል ፣ ንብረቱን መቀማት ፣ ከይዞታው ማባረር ማፈናቀል ይችላሉ… ጥፍሩን እየነቀሉ ያልፈፀመውን ሀጢያት ተናዘዝ ይላሉ… ብልቱን እየቀጠቀጡ ‘ዘር ማንዘርህን እናኮላሻለን’ ይላሉ… አረ ስንቱ።

ወቅቱ ስለ ዲሞክረሲ መኖር አለመኖር ሳይሆን ስለ አብዮቱ አለመቋረጥ ፣ ስለ ምስቅልቅሉ አለመገታት ነው። ባንድ ጀምበር ሰላሳ ሺህ ዜጎች ካንድ መንደር ሲፈናቀሉ አብዮቱ አለማቋረጡን ፣ ምስቅልቅሉ መቀጠሉን ፣ መንግስታዊ ህገ ወጥነት በህልውና መስፈኑን ያረጋግጣል —

እንግዲህ አብዮትን ከዲሞክረሲ ባህሪ ጋር አዳቅሎ ማራመድ የሚቻለው እንዴት ነው? ህግ የለም እንዳይባል የሆኑ ሸጋ አንቀፆች የታጨቁበት ሰነድ ያሳያሉ – ህጉን ግን የማያቋርጠው አብዮት እንደ አመቺነቱ ይተረጉመዋል ፣ ይሸረሽረዋል ፣ ይመደምደዋል። አብዮተኞቹ ሁልጊዜም ከዚያ ህግ በላይ ናቸው – ዜጎችም ከህግ ፊት እኩል በመሆን ሳይሆን በአብዮት ፊት ታማኝ በመሆን እና አለመሆን ፤ ለአብዮተኞቹ ቅን ታዛዥ እና ታማኝ ከመሆን አለመሆን አንፃር ይፈረጃሉ። ፀረ-አብዮታዊ ዲሞክረሲ የሆኑ ዜጎች አሸባሪ ተብለው በዚያ አብዮቱ በፃፈው ልዩ ህግ ለፍርድ ይቀርባሉ… ይጋዛሉ ፣ ወህኒ ይወረወራሉ – በአብዮታዊ ዲሞክረሲ ካራ ይቀላሉ…

 

ህግ አለ መስሏቸው ‘በህገ መንግስቱ እንደተፃፈው’ የሚሉ ቅን ዜጎች በዚያው ለምድ ባጠለቀው ህገ መንግስት ተፈርዶባቸው ወህኒ ይማቅቃሉ…

 

ዲሞክራሲያዊ ስርአት ለማምጣት አብዮት ማካሄድ አንድ ነገር ነው – አብዮት የአጭር ጊዜ

ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ከመሆን የሚያልፍ ነገር አይደለም። ዲሞክረሲ ደግሞ ዘላቂ የፖለቲካ ህይወት ነው። የህግ በላይነት ፣ የሰብአዊ መብቶች መረጋገጥ ፣ በነፃ የህዝብ ምርጫ ስልጣን ላይ መቀመጥ የመሳሰሉትን ያመለክታል። የዲሞክረሲ ባህል ግንባታ በአይምሮው የጎለመሰ ፣ በስነ ምግባር የተኮተኮተ ፣ አገሩን እና ህዝቡን የሚወድ እና የሚያከብር – በአስተዳደር ጥበብ ሁነኛ ተሞክሮ ያለው አስተዳደር ይጠይቃል። ከፍየል እረኝነት ወደ ህወሃትነት ብሎም ወደ መንግስት ስልጣን እና ሀላፊነት መሸጋገር

 

እርግጥ ነው ሌኒን ነበር ‘አብዮት የማያቋርጥ እንቅስቃሴ ነው…’ ያለው። መፈክሩን በተግባር የተረጎመው ደግሞ ሌላ ሳይሆን ስልጣኑን ከሌኒን የወረሰው ጆሴፍ ስታሊን ነበር። ስታሊን ስልጣን ላይ በቆየባቸው ሁለት አስርት ከግማሽ ዘመን በማያቋርጠው አብዮት ስም እየተገዘተ ያገሩን ህዝብ የደም እንባ አስለቅሶበታል – ተቀናቃኝ መስለው የታዩትን የራሱን የቦልሼቪክ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ሳይቀር በመረሸን ፣ የደረጁ ገበሬዎችን አፈናቅሎ በቅጣት ወደ ማጎሪያ ሰፈሮች በማጋዝ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ አብዮት ‘የማያቋርጥ እንቅስቃሴ’ መሆኑን ሲያስመሰክር ቆይቷል። ይሁንና ስታሊን በአብዮት ስም የአገሩን ዳር ድንበር ለማንም አልሸጠም – ፓርቲው በዘር እና ጎጥ ላይ የተገነባ ባለመሆኑ አገራዊ ብሔራዊ ክብር እንዳይደፈር በጀግንነት ተዋድቋል። በዚህ ረገድ ከወያኔ ፍፁም የተለየ ያደርገዋል። ተፈጥሯቸው ለየቅል በመሆኑ በሁሉም ነገር አይመሳሰሉም።

 

ወያኔ ከስታሊን የወረሰው መንፈስ ‘አብዮት የማያቋርጥ እንቅስቃሴ’ ፣ የማያቋርጥ ምስቅልቅል መሆኑን ብቻ ነው። ለወያኔ ህልውና የሚጠቅመውም ይህ ብቻ ነው። ይህን የሚጠራጠር ካለ ሀያ አምስት አመታት ወደ ሁዋላ ሄዶ እነ መለስ ዜናዊ ስለ ጆሴፍ ስታሊን አብዮታዊ ተግባራት ይሰብኩ የነበረውን ማንበብ ይችላል። አዎ ሀያ አምስት አመታት ሙሉ ሳያቋርጡ ድሀን ማስለቀስ የማያቋርጥ የአብዮተኞች እንቅስቃሴ ነው። ለነሱ ድሀውን በማያቋርጥ ግርግር ካላዋከቡት ለከት የለሽ የዘረፋ ጥማቸው አይረካም። ስለሆነም በህግ ዳኝነት ሳይሆን በግርግር ይመነጥሩታል ፣ በወከባ ያስለቅሱታል ፣ በጥይት እሩምታ ይረፈርፉታል – ያንንም አብዮት ነው ይሉታል… የማያቋርጥ እንቅስቃሴ ፣ የማያቋርጥ እንባ ፣ የማያቋርጥ የጥይት እሩምታ… አዲስ አበባ ፣ ጋምቤላ ፣ ኦሮሚያ…

 

ወያኔ የዲሞክረሲ ለምድ የለበሰ ተኩላ መሆኑን አፍቃሪ የሆኑ ምዕራባውያን ጭምር የሚስቱት አይደለም። ተኩላው ለምድ የለበሰው እነሱን ለማደናገር መሆኑም ጠፍቷቸው አይመስለኝም። ከወቅቱ አለም አቀፍ ቀውስ አንፃር የምዕራባውያንን ብሔራዊ ጥቅም ለመጠበቅ ተኩላም ቢሆን ጠቃሚ ሆኖ ከተገኘ ይታገሱታል… ተኩላው ቀን የጎደለበት ቀን ግን ተኩላውን አያድርገኝ… በመዝገብ ቤታቸው ያከማቹትን የሰብአዊ መብት ረገጣ ታሪክ ፣ የታዘቡትን ፣ የመከሩትን ሁሉ አደባባይ ያወጡታል… ስንት ጉድ እንሰማ ይሆን?

 

በቅርቡ ይፋ በሆነ ሰነድ የዞን 9 ጦማሪዎች ያጠናቀሩት የእስረኞች ሰቆቃ ጥናታዊ ሰነድ (ከዞን ዘጠኝ ወይንም ጎልጉል ድረ-ገፅ ላይ ታገኙታላችሁ) ከብዙ በጥቂቱ እንደሚያሳየው የወያኔ የማሰቃያ ተቋማት በየዕለቱ የሚፈፅሙት ግፍ ለጆሮ ይቀፋል። ከትግራይ መንደሮች ተመልምለው የመጡ ፍየል እረኞች መርማሪ ሆነው የነገሱበትን የማዕከላዊ እስር ቤት ምርመራ በጨረፍታ ያሳየናል።

 

ከትግራይ መንደሮች ተመልምለው በመርማሪነት የሰለጠኑት ሰቆቃ ፈፃሚዎች አንድን ዜጋ (በነሱ እምነት የአብዮታዊ ዲሞክረሲ ጠላት) አሰቃይቶ እንዴት ያልዋለበትን ፣ ያልፈፀመውን ሁሉ እንዲያምን ማድረግ መቻል እንዳለባቸው ያምናሉ። የመርማሪዎቹ አብዮታዊነት የሚለካው ወያኔ ጠላት ብሎ በፈረጀው ዜጋ ላይ በሚያወርዱት አበሳ ነው ፤ እርግጫው ፣ ጥፊው ፣ ስየሉ ፣ ጋጠ ወጥ ስድቡ… እዚህ ለመጥቀስ እጅግ አሳፋሪ የሆኑ ድርጊቶችን በእህቶቻችን እና ለጋ ወጣቶች ላይ የሚያደርሱት… አረ ስንቱ።

 

እንዳልኩት እነኝህ የማዕከላዊ መርማሪዎች ፣ የወህኒ ዘበኞች እና አዛዦቻቸው… ሁሉም አንዳችም የበቃ የትምህርት ብቃት ሳይኖራቸው ያው እንደ ሚኒስትሮቹ ፣ መምሪያ ሀላፊዎቹ ፣ ኮርፐሬሽን አስተዳዳሪዎቹ ሁሉ በድርጅታዊ ታማኝነት መለኪያ ብቻ የተቀጠሩ ወያኔዎች ናቸው። ህወሃት ለተዋጊነት ይመለምላቸው የነበሩ ፍየል እረኞች ዛሬ ለመርማሪነት ሰልጥነው ክቡር የሆነውን ሰብአዊ ፍጡር እንደ አውሬ ሲዘለዝሉት ማየት ያሳዝናል።

 

እነኝህ የወያኔ መርማሪዎች ‘በሰማዕታት መስዋዕትነት’ የተጎናፀፉትን ከፍየል እረኝነት ወደ መርማሪነት ያሸጋገራቸውን ስራቸውን ሊያጡና ወደ ፍየል እረኝነት ሊመለሱ የሚችሉት በሁለት ምክንያት ብቻ መሆኑን ያውቃሉ – አንድ ወያኔ ባስቀመጠው የጥራት ደረጃ ስራቸውን ማከናወን ካልቻሉ ፤ ማለትም ማናቸውንም አይነት የማሰቃያ ስልት ተጠቅመው እስረኛው ያልፈፀመውን ፣ ያልዋለበትን ሁሉ ማድረጉን አምኖ እንዲፈርም ማድረግ ካልቻሉ። የህወሃት መርማሪዎች ግምገማ አልፈው በመርማሪነት ስራ ለመቆየት ግፍ መፈፀም አለባቸው – የስራ ዋስትናቸው ሰቆቃ መፈፀም ብቻ ነው – ሌላ ዋስትና የላቸውም። አጋዚ የሚሾመው የሚሸለመው ለወያኔ ስልጣን ሲል ንፁሀን ዜጎችን በጭካኔ ለመግደል የማያመነታ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ብቻ እንደሆነ ሁሉ…

 

ሁለተኛው ስራቸውን የሚያሳጣ ሰበብ ወያኔ ከስልጣን ከተወገደ ብቻ ይሆናል። ይኼ ሁለተኛ ሰበብ የመርማሪነት ስራ ከማጣታቸውም በላይ ሌላ መዘዝ አለው ፣ ተጠያቂነት።

 

ከፍ ብዬ የጠቀስኩትን የዞን ዘጠኝ ጥናታዊ ሰነድ በቅጡ ካነበባችሁት የምትገነዘቡት ነገር አለ…. ባልተለመደ ሁኔታ አንድ እስረኛ ለምርመራ ሲጠራ አይኑ ይታሰራል። መርማሪዎቹ ሲደበድቡት ፣ ሲያዳፉት ፣ ቃሉን ሲቀበሉ ወይንም ሲያስፈርሙት ሁልጊዜም አይኑ ጥፍር ተደርጎ ታስሮ ነው። በዚህ ላይ መርመሪዎቹ ስማቸው እንዳይታወቅ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋሉ ፤ ልክ አለቆቻቸው የታጋይ ስም እንዳላቸው ሁሉ የወያኔ መርማሪዎች የመርማሪ ስም ለራሳቸው ያወጣሉ። የትግል ስም የመርማሪ ስም… ይኼ ለምን ሆነ ብላችሁ እንደኔ ታሰላስሉ ይሆናል። መልሱ አጭር ነው – ይኸውም የወያኔ መርማሪዎች ለፈፀሙት ሰቆቃ ሁሉ አንድ ቀን ተጠያቂነት መኖሩ የማይቀር መሆኑን በደመ ነብስ ይገምታሉ።

 

አይን በማሰር እና ስማቸውን በመቀየር በነሱ ቤት የዛሬ ሰቆቃ ተቀባይ ነገ አንድ ቁጥር መስካሪ ሆኖ ዳኛ ፊት ሊመሰክርባቸው የሚችልበትን ዕድል ማጥበባቸው ነው። ስም በመደበቅ እና አይን አስሮ በመግረፍ ከህግ ፊት ማምለጥ ይቻል እንደሆነ ግን ወደ ፊት የምናየው ይሆናል።

 

እንቅስቃሴው የማያቋርጠው የወያኔ አብዮት አንቀላፍቶ አያውቅም – መንደሮቸን ያተራምሳል፣ ድሀ ዜጎችን ያፈናቅላል ፣ ቱጃሮችን ባንድ ጀምበር ይፈጥራል… ይተክላል (ቱጃሮቹን ታወቋቸዋላችሁ) ፣ ባንኮችን ያራቁታል ፣ መሬቶችን ይወራል ፣ የፀሀፊዎችን ብእር ብቻ ሳይሆን ጣት ይቆርጣል ፤ ደግሞ ህግ አለ ይላል ወዲህም አብዮት የማያቃርጥ እንቅስቃሴ ነው ይ። ዳኞችንም ይሾማል ፣ በአብዮታዊ ዲሞክረሲ አቅጣጫ ይበይናል። በህግ አምላክ ለማለት የከጀላቸውን ዳኞች በብቃት ማነስ ያባርራል ፣ ግፍ እና ሰቆቃ መፈፀም ያልቻሉ መርማሪዎችንም ያሰናብታል…

 

ሰቆቃ ፈፃሚ መርማሪዎች የሚታደጉበት ፣ ፍትህ አዛብተው የሚበይኑ ዳኞች ሸንጎውን የተቆጣጠሩበት ፣ በሙስና የተዘፈቁ ሹማምንት ትከሻ የደነደነበት ድህነትን ሳይሆን ድሆችን እየጠራረገ በመራመድ ላይ ነው… የወያኔ አብዮታዊ ዲሞክረሲ… የማያቋርጥ እንቅስቃሴ…

https://www.facebook.com/plugins/like.php?app_id=&channel=http%3A%2F%2Fstaticxx.facebook.com%2Fconnect%2Fxd_arbiter.php%3Fversion%3D42%23cb%3Df10795773057d88%26domain%3Dwww.zehabesha.com%26origin%3Dhttp%253A%252F%252Fwww.zehabesha.com%252Ff422600ed753c4%26relation%3Dparent.parent&container_width=0&href=http%3A%2F%2Fwww.zehabesha.com%2Famharic%2Farchives%2F62761&layout=button_count&locale=en_US&sdk=joey&send=false&show_faces=false

Share3

የትግሬው ፋሽስት ቡድን መላውን ዐማራ አሸባሪ ብሎ በግልጽ አወጀ! – ሙሉቀን ተስፋው

ከማናቸውም ውጫዊ ኃይል ነጻ ነው!

ዛሬ ማምሻውን ፋሽስታዊ ሥርዓቱ በሚቆጣጠራቸው የዜና ማሰራጫዎች የወልቃይት ዐማሮችንን ጥያቄ ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት አላቸው፤ እነርሱም አሸባሪዎች ናቸው ሲል አውጇል፡፡ የአርማጪሆን ድንበር ጠባቂዎች ባለፉት ጥቂት ወራት ሽፍቶችና ወንበዴዎች ሲል መከራረሙ የታወቀ ቢሆንም አሁን ሁሉንም ዐማራ አሸባሪ ነው ብሎ ማወጁ ሥርዓቱ የገባበት ጭንቅ ማሳያ ነው፡፡

በ85/86 ዓ.ም. የዘመን መለወጫ ወቅት አደባባይ ኢየሱስ ላይ የጨፈጨፋቸውን ዐማሮች እንዳሁኑ ሁሉ የከንቲቫ ጽ/ቤቱን ለመዝረፍ የመጡ ሽፍቶች ብሏቸው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ዐማራን ለማጥፋት ማናቸውንም ዓይነት መወንጀያ ምክንያት ከመጠቀም ወደ ኋላ እንደማይሉ ግልጽ ነው፡፡

ወያኔዎች ያላወቁት ነገር ቢኖር ዐማራ ትግስተኛ መሆኑን ነው፤ ትግስት ፍርሃት እንዳልሆነ አልገባቸውም፡፡ የዐማራ ሕዝብ ለሃያ አምስት ዓመታት የተሸከማቸው ለአገር አንድነት ሲል ነበር፡፡ አሁን ግን አገር የለችም፤ በአናሳ ጠባብ ብሔርተኞች አገር በካርታ ላይ ብቻ ቀርታለች፡፡ የዐማራ ሕዝብ ራሱን ለማዳን ማንኛውንም መስዋትእነት ይከፍላል፤ እንኳንስ ለጠባብ አናሳ የትግሬ ቡድኖች ቀርቶ ጣሊያንንም መክቷል፡፡

በዚሁ አጋጣሚ መላው ዐማራ የሚያደርገው ትግል ግንቦት 7ን ጨምሮ ማንኛውንም ኃይል የማይወክልና ራሱን ከጭቆና ለማላቀቅ የሚደረግ መሆኑን ብቻ ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ ማንኛውም የዐማራው እልቂት የሚያሳስበው ወጣት ሁሉ በኮሎኔል ደመቀ ሥር ሆኖ መንቀሳቀስ አለበት፡፡

በመጀመሪያው መጨረሻም፤

ደጉ አንዳርጋቸው እንደሚታሰር ከተለያየ አቅጣጫ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ ገዱ እንደሚባለው እውነተኛ የዐማራ ተቆርቋሪ ከሆነ የክልሉን ልዩ ኃይልና ፖሊስ ይዞ የትግሬን መከላከያ ይገጥማል፤ ያን ካደረገ መላው ዐማራም ከጎኑ ይሠለፋል፡፡ ካልሆነ ግን ከንቱ ማዘናጊያ እንዳትሆን ስጋት አለን፡፡ የጎንደር ዐማሮችን ለማገዝ ከየቦታው የመጣችሁ ዐማሮች የብአዴን አመራሮች ለማረጋጋት በሚል የሚሰጧሁን ምክር መቀበል ሞኝነት መሆኑን እንድታውቁት እንወዳለን፡፡ ብአዴን ጥርስ የሌለው ውሻ ነው፤ ተረጋጉ ቢልም ነገ የሕወሓት ደኅንነት በየቤትህ እየመጠረ ሲወስድህ ተው እንኳ ብሎ መጠየቅ የሚችል አይደለም፡፡

የዐማራ እግሮች ሁሉ ወደ ጎንደር ያመራሉ!!

posted by tigi flate

የግንቦት ሰባት አመራር አድርገዉኝ አረፉት – ግርማ ካሳ

ተከሳሽ በሚጠቀምበት ማሀበራዊ ድህረ ገጽ በተለይም ፌስ ቡክ አድራሻዉን ተጠቅሞ በዉጭ አገር ከሚገኝ የሽብር ቡድኑ ግንቦት ሰባት አመራር እና አባል የሆነው ግርማ ካሳ ተብሎ የሚጠራ ግንኙነት በመፍጠር በሽብር ቡድኑ የተሰጠዉን ተልእኮ በማስፈጸም በቀን 27/2/2007 ዓ/ም፣ በ28/2/2007 ዓ/ም፣ በ10/6/2007 ዓ/ም፣ በ11/06/2007 ዓ/ም፣ በ18/06/2007 ዓ/ም፣ በ01/07/2007 ዓ/ም እየተገናኙ ስለ ግንቦት ሰባት እና አሸባሪ ተብለው የተከሰሱትን ቤተሰቦቻቸው እንዴት ሊደገፉ እንደሚችሉ የሚገልጽ የተለያዩ ይዘት ያላቸው መረጃዎች የተለዋወጡ በመሆኑ በዝርዝር ያደረጉት ንግግር በክሳችን በተጠቀሰው ማስረጃ የቀረበ በመሆኑ”…

ጋዜጠኛ ጌታቸውን ከከሰሱበት ፍሬከርስኪ ክሶች መካከል የተወሰደ ነው። የአንድነት ፓርቲ እውቅናዉን ከተነፈገ በኋላ የአንድነት ደጋፊዎችና ለሎች አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፣ የእስረኞች ኮሚቴ አቋቁመን፣ መጠነኛም ቢሆን የሕሊና እስረኞች ቤተሰቦችን (ኢኮኖሚካሊ ችግር ላይ ያሉትን) ለመደገፍ ጥረት ስናደርግ ነበር። በቂ ነበር? በቂ አልነበረም። ካደረገነው የበለጠ ማድረግ እንችል ነበር ? በሚገባ። ግን ትንሽም ብትሆን ከምንም ይሻላል።

አሁንም ያ ጥረት እየቀጠለ ነው። የአንድነት እስረኞችን ብቻ ሳይሆን፣ የመድረክ፣ የሰማያዊ፣ የመኢአድ፣ ጋዜጠኞና በዉሸት ክስ በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከሰው የተፈረደባቸውንም ሳይቀር። የትም ድርጅት ይሁኑ ሁሉም የታሰሩት ለአገርና ለሕዝብ ነውና የሕሊና እስረኞች ናቸው። ጀግኖቻችን ናቸው።

በዚህ ረገድ የምናደርገው እንቅስቃሴን ነው እንግዲህ “ሽብርተኝነት” ተደርጎ ለክስ እያቀረበ ያለው። በዉሸት ክስ መከሰሳቸው ሳያንሳቸው፣ እስረኞችን ኢሰብዓዊ ጭካኔ እየፈጸሙ መደብደባቸው ሳያንሳቸው፣ የነርሱን ልጆች ለመዝናናት በፓሪስና በዱባይ እየላኩ የሌሎች እስረኞችን ልጆች ያስራቡት ሳያንሳቸው ፣ አሁን ደግሞ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ለእስረኞች ቤተሰቦች ድጋፍ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ “ሽብርተኝነት ነው” ይላሉ። ከዚህ የበለጠ ጭካኔ፣ ከዚህ የበለጠ አሪዮስነት ምን አለ ?

በዚህ ጉዳይ ላይ ትንሽ አይምሮ አለን የምትሉ የኢሕአዴግ ደጋፊዎች እንድትጽፉና የምትደግፉት ድርጅት አመራሮች ላይ ግፊት እንድታደርጉ በአክብሮት እጠይቃለሁ። ይኸው 25 አመት ደፈናችሁ። ምንድን ነው እየሆናችሁ ያላችሁት። በጫካ ከነበረችሁበት ጊዜ ሁሉ የባሰ አዉሬዎች እየሆናችሁ ነው ? እንዴት ነው ሳንወድ በግዳችን፣ የምንቃወመዉን ደርጅት እንድነቀላቀል ነው እንዴ የምትፈልጉት? እኛ የግንቦት ሰባት አካሄድ አያዋጣም እያልን እየተከራከርን፣ መልሳችሁ እኛን ” የግንቦት ሰባት አመራር አባል” ብላችሁ ስትሰይሙን እንደው አታፍሩም?

ለማጠቃለል ትንሽ ስለ ጌቾ ልጻፍ። ጌታቸው ሽፈራው ጋዜጠኛ ብቻ ሳይሆን ለተቸገሩ የሚራራ፣ በተለይም ለእስረኞችና ለቤተሰቦቻቸው ትልቅ ሸክም የነበረው ትልቅ ሰው መሆኑን ነው በቀረበበት ክስ ከሳሾቹ ለአለም ሁሉ የነገሩለት። እኛ በፊት እናውቀዋለን። አሁን ግን ማንን እንዳሰሩ ሁሉም አወቋል። ጌታቸው የእስረኞች ጉዳይ በጣም ይከነክንው የነበረ ነው። የእስረኞች ወዳጅ ነው።

አሁንም እኛ ከመቼዉም ጊዜ በላይ አጋርነታችንን ለጌታቸውና ለሌሎች አሁንም በወህኒ እየተሰቃዩ ላሉ የበለጠ ማሳየት ይጠበቅብናል። በተለይም የእስረኞች ልጆች ፣ አረጋዊያን እናቶቻቸውና አባቶቻቸው ዳቦ ማጣት የለባቸውም።

posted tigi flate

በፌስቡክ ምክንያት በርካታ ሶማሌያውያን የኖርዌይ ዜግነታቸውን ተነጠቁ

የኖርዌይ ፓስፖርት

ከረጅም ዓመታት በፊት በፖለቲካ ምክንያት በሶማሊያ መኖር እንዳልቻሉ በመግለጽ በኖርዌይ ያቀረቡት የጥገኝነት ጥያቄ ተቀባይንት አግኝቶ ፤ የመኖሪያ ፈቃድ እና ዜግነንት ተሰጥቷቸው የነበሩ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ሶማሌያውያን የኖርዌይ ዜግነታቸውን ተነጠቁ። ለዚህ ሁሉ የዳረጋቸው ደግሞ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ስለራሳቸው የሚያወጡት መረጃ ጥገኝነት ካቀረቡበት ታሪካቸው ጋር ስለማይመሳሰል ነው።

ከ1992 ዓ.ም እስከ 2000 ድረስ ባለው ጊዜ በተለያየ መንገድ ኖርዌይ ገብተው የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው የነበሩ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ሶማሌያውያን ናቸው፤ በኖርዌይ ያገኙትን ዜግነት የተነጠቁትና የመኖሪያ ፈቃድ አግኝተው የነበሩትም እንዳይታደስላቸው እግድ የተጣለባቸው።

የኖርዌይ መንግሥት የአብዛኞቹን የፌስቡክ ገጾች ሲመረምር ግለሰቦቹ የጥገኝነት ጥያቄያቸውን አቅርበው በነበረበት ወቅት የሰጡት መረጃ እና ስለ እራሳቸው አሁን የሚለጥፉት መረጃ የተለያያ ኾኖ እንዳገኘውና ይህንንም መሠረት አድርጎ ተጨማሪ ማጣራት ሲያደርግ ዋሽተዋል ብሎ በማመኑ ዜግነታቸውን እንደነጠቃቸው አስታውቋል።

በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ምክር ቤት ተመራጭ የኾኑት አቶ በሻህ ሙሴ መሐመድ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፤ ግለሰቦቹ ለኖርዌይ መንግሥት ያቀረቡት የጥገኝነት ጥያቄ፤ ሶማሌያ ውስጥ በተፈጠረው አለመረጋጋት መኖር ባለመቻላቸው መሰደዳቸውን በማስረዳት ነው። ይህ ጥያቄያቸውም ተቀባይነት አግኝቶ አንዳንዶቹ ዜግነታቸውን ካገኙ 16 ዓመታት አስቆጥረዋል። አንዳንዶቹ ደግሞ የመኖሪያ ፈቃድ አግኝተው ኑሮአቸውን ቀጥለዋል።

የኖርዌይ የፍልሰተኛ ጉዳዮች መሥሪያ ቤት፤ እነዚህ ዜጎች የዜግነቱንም ኾነ የመኖሪያ ፈቃዱን ያገኙት በሐሰት ላይ በተመሰረተ መረጃ እና ማስረጃ ነው የሚል ጥቆማ ስለደረሰው ለሁለት ዓመት ምርመራ አድርጌያለሁ ማለቱን አቶ በሻሕ ሙሴ ይናገራሉ።

“የኖርዌይ መንግሥት መረጃዎቹን አሰባሰብኩ ካለበት መንገዶች አንዱ የሰዎቹን የፌስቡክ ገፆች ነው። መንግሥቱ የአብዛኞቹን የፌስቡክ ገጾች ሲመረምር ግለሰቦቹ የጥገኝነት ጥያቄያቸውን አቅርበው በነበረበት ወቅት የሰጡት መረጃ እና ስለ እራሳቸው አሁን የሚለጥፉት መረጃ የተለያያ ኾኖ እንዳገኘውና ይህንንም መሠረት አድርጎ ተጨማሪ ማጣራት ሲያደርግ ዋሽተዋል ብሎ በማመኑ ዜግነታቸውን እንደነጠቃቸው አስታውቋል”

አቶ በሻሕ አያይዘው፤ የኖርዌይ የፍልሰተኛ ጉዳዮች መሥሪያ ቤት አገኘሁት ባለው የምርመራ ውጤት፤ አንዳንዶቹ ሶማሌያውያን ነን ከሞቃዲሾ ነው የመጣነው ብለው ጥገኝነት ጠይቀው ፌስቡካቸው ላይ የጅቡቲ እና የሌሎች ጎረቤት ሀገር ዜጎች መኾናቸውን የሚያሳይ ፎቶ ግራፍና ቪዲዮ ለጥፈዋል።

ከጓደኞቻቸውና ቤተሰቦቻቸ ጋር የተነሷቸ ፎቶዎች፣ የሚለዋወጧቸው መልዕክቶች ፈጽሞ ካቀረቡት ታሪክ ጋር እንደማይሄድ ተነግሯል። አንዳንዶቹ ደግሞ መኖር አልቻልንም ወዳሉት ሀገር ተመልሰው መሄዳቸውን መኖሪታ ቤትና ንግድቤት

መስራታቸውን የሚያሳዩ ምስሎች እና አስተያየቶች ማስፈራቸው የኖርዌይ የፍልሰተኞች ጉዳዮች መሥሪያ ቤቱ ደርሼበታለሁ ይላል።

መሥሪያ ቤቱ ይህንኑ በፌስ ቡክ ላይ የሰፈረ መረጃ ተከትሎም ምርመራ ሲያደርግ አንዳንዶቹ በጭራሽ ሶማሌኛ ቋንቋ የማይችሉና ሶማሌያ ከምትባለው አገር ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው የጎረቤት ሀገር ዜጎች ናቸው። አንዳንዶቹ ደግሞ ከሌላ ሶማሌኛ ቋንቋ ተናጋሪ ከኾኑ ጎረቤት አገራት የመጡ ናቸው። ለዚህ ደግሞ ያደረጓቸው የመልዕክት ልውውጦች እና ወደ ቤተሰቦቻቸው የላኩት ገንዘብ በማስረጃ ተያይዞባቸዋል ተብሏል።

አሁን አሁን አገራት እንደ ፌስቡክ ባሉ ማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ የሚውጡ ታሪኮችን እንደ የጀረባ ታሪክ ማጣሪያ መንገድ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ። የዩናይትድ ስቴትስ የሠራተኛ አስተዳደር ጉዳዮች ቢሮ የተቀጣሪ ሠራተኞቹን የደህንነት ዳራ ፍተሻ ለማጥራት አዲስ ለሕዝብ ክፍት የኾኑ ማኅበራዊ ድረ ገፆች ላይ የጀመረውን ዘዴ በድረ ገጹ ላይ አስፍሯል።

አቶ በሻህ ሙሴም የኖርዌይ የፍልሰተኞች ጉዳዮች መሥሪያ ቤት ሌላ እያጣራቸው የሚገኙ ሰዎች እንዳሉ ተናግሯል። በዚህ ምክንያት ብቻ የኖርዌይ ዜግነታቸው መነጠቃቸው፣ የመኖሪያ ፈቃዳቸው እንዳይታደስ መከልከሉ እና ወደየ አገራቸው ይመለሳሉ መባሉን በመቃወም ፊርማ አሰባስበው አቤቱታቸውን ሊያቀርቡ ነው ብለዋል።

 

እሁድ እረፋድ | ታሪኩ ደሳለኝ

አባት ከ 7 አመት ልጁና ከ3 አመት ሴት ልጁ ጋር ግቢ ውስጥ እየተጫወተ ነው በዚህ መሀል የግቢው በር ይንኳኳል ሴት ልጁን አቅፎ ወደ በሩ ሲያመራ ወንድ ልጁ ሱሪውን ይዞ ተከተለው። በሩን ሲከፍት መሳሪያ የደቀኑ ወታደሮች ከቀበሌው ሊቀመንበር ጋር ቆመው አገኛቸው። አባት ሴት ልጁን ጠበቀ አድርጎ እያቀፈ ወንዱን ልጅ ወደ ኃላ ሸሸት አደረገው። አንደኛው ወታደር ያያዘውን ወረቀት ሰጠው በስጋት ተቀብሎ ተመለከተው “ሀገር የመክዳት ወንጀል የፈፀመ” ይላል ። ወታደሩ በመሳሪያው ጫፎ ወደ ቆመው ፓትሮል መኪና እንዲሄድ መልክት አሳየው ልጆቹን በሩ ላይ ጥሎ ወደ መኪናው ገባ ። መኪናው ሞተሩን አስጩሆ ሲሄድ ጎልቶ የሚሰማው የሞተሩ ድምፅ ሳይሆን የልጆቹ የለቅሶ ድምፅ ነው።

ይህ ክስተት የተፈፀመው ከ 5 ወራት በፊት በጎንደር ከተማ ነበር።

ሐሙስ ከሰዓት

በአካባቢው ሰው የተወደደ ጉልማሳ ነው። የራሱን ሚኒባስ መኪና ነው የሚያሽከረክረው።የተጣላን አስታራቄ ለተቸገረ ቀድሞ ደራሽ ። በሱ ሚኒባስ የተሳፈሩ እናቶችና አባቶች አቅመ ደካሞች አይከፍሉም ማለት የቻላል። ሀሙስ ከሰአት ገቢያተኞችን ጭኖ እንደወትሮው እየሳቀና እየተጫወተ ሲሄድ የትራፊክ ፖሊስ እንዲቆም ምልከት አሳየው። መኪናው ዳራ እያሲያዞ እያቆመ በውስጥ መስታወት ትርፍ ሰው አለመጫኑን ከረጋገጠ በኃላ ከነፍገግታው ከመኪናው ወረዳ። በአካባቢው ቁጥቋጦ ውስጥ ተሸሽገው የነበሩት ወታደሮች ጠመንጃቸውን እንደ ወደሩ ከበቡት። ግራ ተጋባ ሽፎቶቸ ናቸው እንዳይል ትራፊክ ፖሊሱን ለ3 አመታታት ያህል ያቀዋል። አንደኛው ወታደር የያዘውን ወረቀት ሰጠው ተቀብሎ ተመለከተው “ሀገር የመክዳት ወንጀል የፈፀመ” ይላል። እጁን እረጋ ብሎ ሰጣቸው። ከፊት አስቀድመውት ሲሄዱ ሚኒባስ ውስጥ ያሉት ተሳፋሪዎች የሚደረገውን ነገር በቁጣ እየተመለከቱ ነበር።
ይህ ድርጊት የተፈፀመው ከአንቦ ወደቶኪ በሚወስደው መንግድ ላይ ከ 2 ወራት በፊት ነው።

ለማሳያ ያህል ከላይ ስለገለፅኳቸው ሰዎች ጉዳይ መንግስት ሲናገር “አሰልጥኜ፣ ቃል ኪዳን አስገብቼ መሳሪያ ያስታጠኳቸው ወታደሮች ነበሩ ሆኖም ለሀገር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰው መሳሪያቸውን ጥለው ማንነታቸውን ለውጠው ግዲታቸውን ሳይፈፅሙ የከዱ ወታደሮች ናቸው” ይላል። የከዱ የተባሉት ወታደሮች ደግሞ ይህን ያላሉ “ለሀገራችን የደምም የአጥንትም መሳዋትነት ከፍለናል፣ የበረሃው ሀሩር ሳይበግራን የወይን አደጋው በርድ ሳያሸንፈን በዱር በግድሉ በየ ግንባሩ ተፋልመናል። ሆኖም በሚገባን ጊዜ ማረግ ልናገኝ ይቀርና ባለ ማአረግ ይጎትተናል፣ የውል አበላችንም ሆነ ደሞዛችን በወራት ነው ይምናገኘው፣ የሠላም ማስከበር ስራ ለመስራት ወደ ሌሎች ሀገራት ለመሄድ በሁሉም መስፈርት ብቁ ብንሆንም ከመሀላችን ተመርጠው ነው ሌሎች የሚሄዱት በዚህ ላይ የሀገር ወታደር እንደሆንን እንዲሰማን አያደርጉንም። ታዲያ ማነው የተከዳው?” ይላሉ።

የሆነው ሆኖ መንግስት ከ2005ዓ.ም ጀምሮ የ1990 ዓ.ም ዘማቾችን፣ የ1994ዓ.ም ዘማችን እና ከዛ በኃላ ውትድርናን ተቀላቅለው ከድተውኛል የሚላቸውን እያፈሰ በፌደራሉ የሸዋ ሮቢት እስርቤት ማጉር ከጀመራ ሦስት አመት ሆኖታል።
ይበልጥም ህዝባዊ እንቢተኝነት በኦሮሚያና በጎንደር መታየት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አሰሳውና አፈሳው ተጠናክሮል።

እንዚህ መንግስት ከድቷናል የሚሉ ወገኖች መሳሪያ መተኮሱንና ማስተኮስ የሚችሉ፣ ጥቃትን እንዴት ይፈፀማል ጥቃትንስ እንዴት መመከት ይቻላል የሚሉትን ነገሮች ጠንቅቀው የሚያውቁ በዚህ ላይ ከመሀበረሰቡ ጋር ተግባብተው የሚኖሩ መሆናቸው በአሁን ሰዐት የመንግስት ትልቁ እራስ ምታት እንዲሆኑ አስችሎቸዋል። ለዚህ ነው መንግስት አይኑንም እጁንም እነሱ ላይ ያደረገው። በብዛት በመሀበረሰቡ ውስጥ የሚገኙት ተክደናል የሚሉት ወገኖች ህዝባዊ እንቢተኝነትን ከተቀላቀሉ ምን ይከሰት ይሆን?
(በሸዋ ሮቢት የፌደራሉ እስር ቤት ከሚገኙ ተማኝ እስረኞች ከሚባሉት ጋር የተደረገ ወግ)

posted by tigi flate

 

 

 

 

 

 

 

ሕወሓቶች የወልቃይት ጸገዴን ሕዝብ መስለው ሰልፍ ወጡ

(ዘ-ሐበሻ) “በመላዋ ኢትዮጵያ ሰልፍ መውጣት ወንጀል በሆነበት በዚህ ወቅት በትግራይ ክልል ግን ይፈቀዳል:: የሕዝብ እኩልነት ይህ አይደል?! ከሁለት ሳምንት በፊት የወልቃይት ጸገዴን ማንነት ለማስረዳት ወደ አዲስ አበባ የመጡት ተወካዮች መታሰራችው ይታወሳል::” ያሉን አንድ አስተያየት ሰጪ የሕወሓት መንግስት ዛሬ በጸገዴ ወረዳ አስደረጉት ስላለው ሰላማዊ ሰልፍ ሲያስረዱ “የጸገዴ ሕዝብ የአማራ ህዝብ መሆኑን ያውቃል; አውቆም ተቀብሎታል.. ዛሬ የራሱን የሕወሓት አባላትን ከየቦታው ሰብሰቦ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የብሄርን ግጭት ከማባባስ የባሰ ምንም ፋይዳ የለውም” ይላሉ::

መንግስታዊው ራድዮ ፋና “በትግራይ ክልል የፀገዴ ወረዳ ነዋሪዎች የማንነት ጥያቄያችን ተመልሷል አሁን ላይ ይህን የሚያነሱ እኛን አይወክሉም በማለት ሰልፍ ወጡ” ሲል ያስነበበው ዜና መነጋገሪያ ሆኗል:: የወልቃይት ጸገዴ ማንነት ጥያቄን የሚያነሱትን እና እኛ አማራ ነን በግድ ወደ ትግራይ ክልል እንድንጠቃለል ተደርገናል በሚል ተቃውሞ ሲያነሱ የነበሩትንም እንደተለመደው ሰልፈኞቹ “የጸረሰላም ሃይሎች ናቸው” ብለዋቸዋል ይለናል::

በጸገዴ ሕዝብ ስም ዛሬ ሰልፍ የወጡት የሕወሓት አባላት ይህን ሰልፍ የጠሩት አንድም የገቡበትን ውጥረት ለማብረድ በሌላ በኩልም ሕዝብን ለማናከስ እንደሆነ ማንም ያውቃል:: እንደፋና ዘገባ እነዚህ ሰልፈኞች “የፀረ ሰላም ሃይሎች የጀመሩት ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት ዓላማ በጥብቅ እንደሚቃወሙ ሰልፈኞቹ ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ ከዓመታት በፊት የተመለሰውን የህዝብ የማንነት ጥያቄ እና አብሮና ተስማምቶ የሚኖርን ህዝብ ለማጋጨት በአሁኑ ወቅት እንደ አዲስ እያነሱ የሚገኙትን የፀረ ሰላም ሃይሎች እንቅስቃሴን በጥብቅ እንደሚቃወሙም ነው ዛሬ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ የገለፁት።”

የሕወሓት መንግስት ለሌላው ኢትዮጵያዊ የከለከለውን ሰላማዊ ሰልፍ የመውጣትና ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት በጸገዴ ሕዝብ ስም ለወጡት አባላት መፍቀዱ የሚያስደንቅ ባይሆንም ይህ ሰልፍ እንዲህ ባለው ሁኔታ መደረጉ ይበልጥ የወልቃይት ጸገዴን ሕዝብ እንደሚያነሳሳው አስተያየት ሰጪዎች በማህበራዊ ድረገጾች ሃሳባቸውን እየገለጹ ነው::

posted by tigi flate

በጋምቤላ በተቀሰቀሰው ግጭት የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ

Written by አለማየሁ አንበ

በጋምቤላ ክልል በኑዌርና በአኝዋክ ብሔሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት የክልሉ የፀጥታ  ሃይል አባላትን ጨምሮ የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በርካቶች በቦንብ ፍንዳታ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
የከተማዋ ነዋሪዎች ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ በግጭቱ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን ከትላንት በስቲያ ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ ባንኮችና የንግድ ተቋማት የተዘጉ ሲሆን ትናንት ረፋድ ላይም በከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች ግርግር ተከስቶ እንደነበር ታውቋል፡፡
ለቀናት በዘለቀው ግጭት የክልሉ የትራንስፖርት ቢሮ ም/ኃላፊን ጨምሮ 8 ሰዎች መሞታቸውንና በከተማዋ ሁለት ቦታ በፈነዳ ቦንብም በርካቶች መቁሰላቸውን የጠቆሙት ምንጮች፤ የክልሉ ልዩ የፖሊስ ኃይልን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት ግጭቱን ለማረጋጋት ጥረት ማድረጋቸውን ጠቅሰው በትናንትናው ዕለትም ከተማዋ በውጥረትና ግርግር ስትዋከብ መዋሏን ገልፀዋል፡፡
የግጭቱ መነሻ ከ15 ቀናት በፊት በክልሉ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ም/ዲንና በክልሉ ም/ፕሬዚዳንት ሹፌር መካከል በመኖሪያ ቤት መሬት ጉዳይ በተፈጠረ የግል ፀብ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቻችን፤ ጠቡን ተከትሎ ም/ዲኑ የአኙዋክ ተወላጅ ሹፌሩን እጁ ላይ በጥይት መተው ማቁሰላቸውን ገልፀው በዚህም ሳቢያ ጉዳዩ የብሄር ግጭት መልክ እንደያዘና ወደ ተማሪዎች የቡድን ፀብ እንደተዛመተ አስረድተዋል፡፡
ግጭቱ ከእለት እለት እየተባባሰ ቀጥሎም አንዲት የኑዌር ተወላጅ ተማሪ በግጭቱ ጉዳት ደርሶባት ህክምና እየተከታተለች ሳለ ህይወቷ በማለፉ ግጭቱ መካረሩን የጠቆሙት ምንጮች፤ የኑዌርና የአኙዋክ ብሄር ተወላጅ ተማሪዎች የእርስ በእርስ ግጭት መፍጠራቸውን ገልፀዋል፡፡
የክልሉ ልዩ ሃይል ግጭቱን ለማርገብ ሙከራ ሲያደርግ ቢቆይም ሁኔታው ባለመረጋጋቱ የመከላከያ ሰራዊት በትናንትናው እለት በከተማዋ ተሰማርቶ ግጭቱን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ መሆኑን ነዋሪዎች ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ ከክልሉ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ም/ኃላፊ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም በትናንትናው ዕለት ኃላፊው አዲስ አበባ መምጣታቸውን ገልፀው፤ “መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ ገልፀውልናል፡፡

posted by tigi flate

የሰሞኑ ‹‹የኦሮምያ ግርግር›› ግራ ገብቶኛል – መስፍን ወልደ ማርያም

በሁለት ደረጃ የሚቀርቡ ጥያቄዎች አሉኝ፤–
አንድ፡– ግርግሩ የኦሮምያ ነው? ወይስ የኢትዮጵያ? ወይስ ኦሮምያ ከኢትዮጵያ ተለይቷል?
ሁለት፡– የኢትዮጵያ የመሬት ጉዳይ ኦሮሞዎችን ብቻ የሚመለከት ነው? ወይስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ?

አንደኛ፣ ግልጽ ከሆነው እውነት እንነሣ፤ ኦሮምያ ከኢትዮጵያ አልተለየም፤ ስለዚህም ግርግሩ የኢትዮጵያ ነው እንጂ የኦሮምያ አይደለም፤ ጥንቱኑ ለማጋጨት የተሰጠውን ስያሜ በስምነቱ ከማጽደቅ በላይ ለታቀደው ዓላማ አመቺ መሣሪያ ማድረግ ነው፤ ይህ ደግሞ በቅድሚያ መሸነፍን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ከወያኔ በቀር ደጋፊ ያለው አይመስለኝም፤ ቁርጠኛ ትግል ቁርጠኛ ዓለማና ቁርጠኛ ስልት ያስፈልገዋል፤ ስለዚህም ቁርጠኛ መሪ ያስፈልገዋል፤ የሕመሙን መርዝ እየተጎነጩ ከሕመሙ ፈውስ ለማግኘት አይቻልም፤ ግርግሩ የኦሮሞ ከተባለ ሁለት ውጤቶች ይከተላሉ፤ አንዱ ውጤት ከኦሮሞ በቀር ሌላውን ሕዝብ አያገባውም ማለት ይሆናል፤ ሁለተኛው ውጤት የልየነቱ በላቤቶችና ተፋላሚዎች ኦሮሞዎችና ወያኔዎች ብቻ ናቸው ማለት ነው፤ ይህ ትልቅ አደጋ አለበት፡፡
አደጋው ወደሁለተኛው ጥያቄ ይመራናል፤ ገብቶኝ እነረደሆነ የግርግሩ ምክንያት ሁለት ናቸው፤ አንዱ ከቤት-ንብረት መፈናቀል ነው፤ የዜግነት መብትና መገለጫ የሆነውን መሬት ማጣት ነው፤ ሁለቱም መሰረታዊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነትን የዜግነት መብቶች ሚደፈጥጡ ናቸው፤ ልብ በሉ የኦሮሞን የዜግነት መብቶች ይደፈጥጣል አላልኩም፤ የኢትዮጵያውያንን ሁሉ መሠረታዊ መብቶች የሚደፈጥጥ ነው፤ ይህ የማያጠራጥር እውነት ነው፤ ይህንን ከተቀበልን ጉዳዩ የኦሮሞ ብቻ አይደለም፤ ግርግሩም የኦሮሞ ብቻ አይደለም፡፡
ትልቁ አደጋ ያሁንን ግርግር የኦሮምያ ብቻ ካደረግነው ወደፊት ያው ጉዳይ በሌሎች ጎሣዎች መሀከል ሊነሣ ነው፤ ሌሎች ግርግሮች ሊያስፈልጉ ነው፡፡
ጉዳዩ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሆነ ትግሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ነው፡፡

posted by tigi flate

“በአማራ ብሄር ተወላጅ ወገኖቻችን በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እየደረሰባቸው ያለው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ኣጥብቄ እኮንናለው” አምዶም ገብረሥላሴ

ይህ ዜጎች ባገራቸው ይህ የመሰለ ጭፍጨፋ መካሄዱ እጅጉን የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ሰብኣዊነት የጎደለው ተግባር ነው።
መንግስት ለዚህ ኣስደንጋጭና ዘግናኝ ተግባር ሃላፍነት በመውሰድ ወንጀሉ በኣስቸኳይ እንዲያስቆመውና ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ ኣለበት እላለው።

ዜጎቻችን በስደት ሳውዲ ዓረብያ፣ የመን፣ ደቡብ ኣፍሪካ፣ ሊብያ፣ ደቡብ ሱዳንና ቤሩት የመሳሰሉ ሃገራት፤ በቀይ ባህር፣ ሜድትራንያን ባህር፣ በሲናይና ሰሃራ በረሃዎች እየደረሰባቸው ያለው መቅዘፍት ሳይበቃ በገዛ ሃገራቸው ይህን የመሰለ ሰቅጣጭ ጭፍጨፋ ሊደርስባቸው ኣይገባም።
ሃገራችን 15 ማልዮን በኣስከፊ ረሃብ በያዘበትና ሂወቱ እያጣበት ባለበት ግዜ ይህን መሰል ወንጀል መፈፀሙ የሚዘገንን ብቻ ሳይሆን የሚያሳፍር ወንጀል ነው።
ብኣዴንም እወክለዋለውና ኣስተዳድረዋለው የሚለው ህዝብ ኣስከፊ ወንጀለ እየተፈፀመበት እያየ የሰው መሰውያ እንደለመደ ጣኦት ምንም ሳይል ደማቅ በዓል እያሳለፈ መሆኑ ያስገርማል።
የኢህኣዴግ መንግስትም እንደዚህ ዓይነቶች ወንጀሎች የሚፈፅሙ ወንጀለኞች ይዞ ለፍርድ የማያቀርብ ከሆነ ኣስፍኘዋለው የሚለው ሰላም ከመደፍረሱ በላይ የወንጀሉ ተባባሪና ቁጥር ኣንድ ተጠያቂ ያደርገዋል።
መንግስት ወንጀለኞች ባስቸኳይ ለህግ ያቅርብልን !
soeruc zehabesha

posted tigi flate